“እኔኮ አፌ እንጂ ልቤ ንጹሕ ነው…” የምንል ብዙዎች ነን —ጀብድ እንደኾነ ነገር፤ መርዘኛ ምላስ ከክፉ ልብ ይቀልል ይመስል ነገር።
“እኔ ሲፈጥረኝም መደባበቅ አላውቅም፣ ሲፈጥረኝም
ግልጽ ግልጹን ነው የማወራው” እያልን ሰው የምናቆስል አለን። ግልጽነትን መረን ከመኾን ለመለየት ዕድሜና ብስለት ያልሰጠን —ስናሳዝን።
ሰው ግን በልቡ ከሞላው በቀር በአፉ ሊወጣ የሚችል ምንም ነገር የለም ከልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።”ማቴዎስ 12፥34
እርግጥ ነው አንዳንዴ ሰው በብስጭት ከአፉ ያልተገቡ ቃላት ሊወጡ ይችላሉ። ደጋግሞ ደጋግሞ የታቀደ በሚመስል መልኩ ሰውን የሚሰብር ሰው ግን “እኔም ሰው ነኝ” ብሎ ሊመሳሰል አይችልም።
“ይቅርታ” ማጣፊያው ሲያጥረን የምንመዘው ራስን የመከላከያ መሣሪያ አይደለም። “ይቅርታ” ማለት ድጋሚ ያንን ጥፋት ላለማድረግ መወሰን እንጂ፤ “የቀደመ ጥፋቴን እርሱልኝ” የሚል የብልጣ ብልጦች ይግባኝ ሊኾን አይገባም። ብዙዎች ግን ያለ ምንም ማመዛዘን ከአፋቸው አጥንትን የሚሰብር ቃል እያወጡ ደግመው ደግመው “ይቅርታ” በማለት የቃሉን ጉልበት ይፈትናሉ።
ይቅርታ” ማለት ግን “ቀጣይ በደንብ አስቤ አወራለኹ” ማለት ጭምር ነው። ይቅርታ ማለት ግን “ቀጣይ በቂ መረጃ ሳይኖረኝ አላወራም” ማለት ጭምር ነው። ይቅርታ ማለት ግን “የማወራው ነገር የሚያመጣውን ቅጣትና ወቀሳ ሙሉ ለሙሉ እቀበላለኹ” ማለት ነው። ካልኾነ ግን “ይቅርታ” የፍቅር መግለጫ፣ የሕግ ፍጻሜ የኾነውን ያሕል … የክፉ ሰዎች መሹለኪያ መንገድ እና የተደጋጋሚ ጥፋቶች ማምለጫ ሆኖ ይቀጥላል።
—————————
ይቅርታ ከብዙ በሽታዎች የሚፈሰው መድኃኒት ነው፡፡ ራሳችንን ከመመረዝ ነጻ ማውጣት የምንችለው በይቅርታ ነው፡፡ ይቅርታ ልክ የተቀደደ ልብስን እንደሚሰፋ የሚያውቅ መርፌ ዓይነት ነው። በየቀኑ የይቅርታን መድኃኒት እየዋጥን መፈወስ ስንችል ለምን ይሆን ራሳችንን የምንመርዘው?
© አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ።"
አባ ኤፍሬም አረጋዊ
ከአበው መነኮሳት አንዱን "ትሕትና ምንድር ነው?" ሲሉ ጠየቁት። እርሱም ሲመልስ "የጎዳህ ወንድምህ ወደ አንተ መጥቶ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ይቅር ካልከው እርሱ ትሕትና ነው።" አላቸው። ለካስ ይህም ትሕትና ነው!!!
╔═ኦ══════════ር══╗
💚 @Ethiopian_Ortodoks💚
╚═ቶ══════════ዶ══╝
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ