ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


🥰 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግነው።
መዝ. ፻፶ ፡ ፮
❝በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው?
1.ጴጥ 3፡13

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል?

🍂"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡

🍂እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድ የለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?

🍂አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።

🍂እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ_ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ_የተረጎመው
ሼር🔺 >
@Ethiopian_Ortodoks @Ethiopian_Ortodoks


ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ እንደምን ከረማችሁልኝ እህት ወንድሞቼ በቃ ሰው ሲጠፋ አትፈልጉም አይደል🤔
ለማንኛውም በቅርብ ቀን ምርኩዜ በተሰኝ ተከታታይ እውነተኛ ታሪክ ፅሁፍ ጠብቁኝ

2.1k 0 0 12 138

ምክር ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የምንወደው ጓደኛችን ቢሞትብን ለቀናት ሐዘን እንቀመጣለን። ብር ቢጠፋብንም እንዲሁም እንቆጫለን። ዕለት ዕለት ሐጢአት ስንሠራ ግን ጥቂትስ እንኳ አናስብም ። መቼ ይሆን የምንነቃው?

ልብስ የተሰጠን ከብርሃናዊ ልብሳችን ስለተራቆትን ነው /ዘፍ. 3፥20/። ታድያ በኃጢአታችን ምክንያት በተሰጠን ልብስ ልባችንን ከፍ ከፍ የምናደርገው ስለምንድ ነው?

ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከእኛ መካከል የሚኖርበትን ቤት በቆሸሸ ቁጥር የማያጸዳው ማነው? ታድያ የእግዚአብሔር ማደርያ የኾነው ሰውነታችንን በንስሐ መወልወያ የምናጸዳው መቼ ነው?

ልጆቼ ንስሐ ግቡ እንጂ በኃጢአታችሁ ምክንያት በፍጹም ተስፋ አንዳትቆርጡ። ወዳጄ ሆይ! ማፈር የሚገባህ ኃጢአት ስትሰራ እንጂ ንስሐ ስትገባ አይደለም። ኃጢአት ሕመም ነው። ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው። ከኃጢአት ቀጥሎ ህፍረት አለ ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ። ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን።
@Ethiopian_Ortodoks
  @Ethiopian_Ortodoks




ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም።
እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምኞት ይረሳል።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✍

3.7k 0 22 2 128

ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ

እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው ።”
                                 መዝ. 33 ፡ 8 ።

በጣም ደግ የሆኑ ሰዎችን እናውቃለን ። ሰው በልቶ የጠገበ የማይመስላቸው ፣ ያንተ እጅ አያጠግብህም በእኔ እጅ ጉረስ እያሉ በላይ በላዩ የሚያበሉ ሰዎች በዙሪያችን አሉ ። ሰለጠኑ የሚባሉት እንኳን በሰው እጅ ሊጎርሱ የራሳቸውንም እጅ ማመን አቅቷቸው ምግባቸውን ወደ አፋቸው የሚያደርሱት በማንኪያ ፣ በሹካና በቢላዋ ነው ። እንብላ ማለትንም እየረሱ ነው ። ሁሉንም ነገር ስሌት ውስጥ እየከተቱት ነው ። ባልና ሚስትም የየግላቸውን ይከፍሉ ይሆናል እንጂ አንዱ ባንዱ ገንዘብ ማዘዝ አይችልም ። በኅብረት ውስጥ ያለ ግለኝነት እንደ መሰልጠን እየታየ ነው ። ኅብረቱም አይቅርብኝ ፣ ግለኝነቱም አይቅርብኝ እየተባለ ነው ። ቀኑን ሙሉ ጋጋሪ አቁመው እንጀራ የሚያስጋግሩ ፣ የጋገሩትን እንጀራ መንገደኛ በልቶ ካልጨረሰው የሚያዝኑ ፣ እንግዳ መቀበል አገልግሎታቸው የሆኑ ሰዎችን እናውቃለን ። ከቤታቸው ደጃፍ አንድ ጎላ ንፍሮ ቀቅለው መንገደኛ ሁሉ ይበላው ዘንድ በየሰንበቱ የሚያስቀምጡ ቸሮችን አይተናል ። እያዘከሩ ሰው የሚሰበስቡ ፣ ማኅበራዊነትና መንፈሳዊነት እንዳይጠፋ የሚታገሉ ብዙዎች ናቸው ። “እኔ ቤት መጥቶ ሳይበላ ነው የሄደው” በማለት ተቀይመው የሚቀሩ ፣ እንደ እናቱ ባያየኝ ነው ብለው አዝነው የሚጎዱ የዋሃንን በትክክል እናውቃለን ። እነዚህ ደጎች ሳይጎድልባቸው እንደ ሰጡ አልፈዋል ። ስጡ ላለው አምላክ ታዘዋልና ተሰጥቶአቸዋል ። በብዛት ሳይሆን በበረከት መኖር ችለዋል ። ዛሬ ብዙ ገንዘብ አለ ፣ በረከት ግን የለም ። ለድሀ አንሰጥም ፣ ለማንድንበት መድኃኒት ግን ብዙ እናወጣለን  ። እግዚአብሔር ስንሰጥ በጤና እንደሚከፍለን አናውቅም ። እናውቃለን ብለን ሞኝ ሆንን ። የሌሎች የረሀብ ሕመም ሲሰማን የእኛ ሕመም እየተፈወሰ ይመጣል ።

ቸሮች በታኞች አይደሉም ። ሰውን የሚያሰክር መጠጥ ፣ ሱስ የሚጋብዙ እነዚህ ጥይት የሚመጸውቱ ናቸው ። ቸሮች የሚዘሩ ናቸው ። ዘሪ መሬቱን ያውቀዋል ፣ ከርሞ ይመለስበታል ። ዛሬ ይዘራል ፣ ነገ እዚያው ያጭዳል ። ቸሮች አንድን ሰው ካለበት ሁኔታ እልፍ ማድረግ ፣ ከግብ ማድረስ ዓላማቸው ነው ። ቸር ሰው በበረሃ እንደ ተገኘ ውኃ ነው ፣ ያረካል ። ቸሮች ውስጣቸው ሕያው ነው ፣ እንቅስቃሴ ላይ ሲሆን ሊወጣ የሚታገላቸው ኃይል አለ ። ራሳቸውን በጣም ስለማያዩት ፣ የሌሎች ጉድለት ስለሚታያቸው ደስተኞች ናቸው ። ፍቅር ተግባራዊ ሲሆን ቸር ያደርጋል ። ስስታም ፣ ንፉግ ሰው አፍቃሪ አይደለም ። እነዚህ ሁሉ ቸሮች ክፉ ቀንን ያለፍንባቸው ፣ ጨለማችን ላይ ብርሃን ያወጁ ናቸው ። ያለ ደጎች ድጋፍ እዚህ አልደረስንም ። ተቀብለን እንዳልተቀበለ መካድ አይገባንም ። እነዚያን ቸሮች ማመስገን ፣ ዛሬ ተራው የእኛ ከሆነ በችግራቸው መርዳት ይገባናል ።

ቸሮች የእግዚአብሔርን ጠባይ የተካፈሉ ናቸው ።
እግዚአብሔርን የሚመስሉ ፣ የሚንሰፈሰፉልን ፣ በረከትን በተርታ የሚያቀርቡልን ፣ ልባቸውም እጃቸውም የተከፈተልን ስጦታዎቻችን ናቸው ። እግዚአብሔርን የምናየው በቸሮች ውስጥ ነው ። ሰው ቅባትና የውበት ዕቃ ሲሸምት ይውላል ፤ እውነተኛ ውበት ግን ቸርነት ነው ። እግዚአብሔር በባሕርይው ቸር ነው ። ቸርነቱን በቃላት መግለጥ ፣ በእውቀት ማስረዳት አይቻልም ። የእግዚአብሔር ቸርነት ከሞት መንጋጋ ያስመልጣል ። ይህን ቸርነት ያልተካፈለ ሰው ፣ እንስሳና እጽዋት የለም ። ቸር አንድ ቀን ከሰዎች ብልጠት የተነሣ ቢስ ይሆናል ። “ቸር ሲያጠቁት ቢስ ይሆናል” እንዲሉ ። እግዚአብሔር ግን እያጠቃነው አሁንም ቸር ነው ።

ነቢዩ በመዝሙሩ፡- “እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው” ይላል ። እግዚአብሔርን ወደ ቤታችን መጋበዝ ፣ እግዚአብሔርን ተሸክሞ ወደ ሰዎች ቤት መሄድ ተገቢ ነው ። መቅመስ ማጣጣም ፣ ለመብላት መዘጋጀት ፣ መሞከር ፣ መለማመድ ነው ። የእግዚአብሔርን ቸርነት መቅመስ አለብን ። ቸርነቱን የሚቀምሱ ቸር ይሆናሉ ። ቀጥሎ፡- “በእርሱ የሚታመን ምስጉን ነው” አለ ። ቸር የማንሆነው ቢጎድልብኝ ብለን ነው ። ቸርነት ግን በእግዚአብሔር በመታመን የሚገኝ ነው ። ስጡ ላለው ቃል ታዝዤ አይጎድልብኝም ብሎ ማመን ይፈልጋል ። እምነት ልምምድ ነው ። መቅመስ ፣ ማየት ይገባል ። የቸርነት ሕይወት ደስ ያሰኛል ። የተቆለፉ ትልልቅ ቤቶች ፣ ምግብ እየተበላሸ የሚደፋባቸው የባለጠጋ ሳሎኖች ይህን ቸርነት ቢለማመዱ የሞት ጥላ ይገፈፍላቸዋል ። እንዴ በየምሽት በሚሊየን እያወጡ ይጋብዙ የለም ወይ? ቢባል እርሱ ንግድና ጉራ እንጂ ቸርነት አይደለም ። ቸርነት የባለጠጎች ዕዳ ሳይሆን ሁሉም የሰው ልጅ የሚለማመደው ሀብት ነው ። በእጃችን ማጉረስ ባንችል በእጃችን የቆሸሸውን ምስኪን ማጠብ እንችላለን ። የሰውነት ክፍሎቻችን የቸርነት መሣሪያ ናቸው ። ቸርነቱን የምንቀምሰው በጸሎት ነው ። የሚለምኑ ይቀበላሉ ፣ ቸርነቱንም ያያሉ ።

እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠን ሕይወትን ነው ።
የሕይወት ዋጋዋ ስንት ነው ? ያኖረን ቸርነቱ ነው ። እስትንፋሳችን በአፍንጫችን ላይ የተንጠለጠለች ፣ ለመሄድ የተዘጋጀች ናት ። እስትንፋሳችንን በአፍንጫችን ያሳደረልን ፣ ያዋለልን ጌታ ቸር ነው ። ይህን ቸርነቱን ማጣጣም ፣ ማመስገን ፣ መመስከር ይገባል ። በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው ቸር ነው ።

እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ ።

@Ethiopian_Ortodoks
  @Ethiopian_Ortodoks
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈




“እኔኮ አፌ እንጂ ልቤ ንጹሕ ነው…” የምንል ብዙዎች ነን —ጀብድ እንደኾነ ነገር፤ መርዘኛ ምላስ ከክፉ ልብ ይቀልል ይመስል ነገር።

“እኔ ሲፈጥረኝም መደባበቅ አላውቅም፣ ሲፈጥረኝም
ግልጽ ግልጹን ነው የማወራው” እያልን ሰው የምናቆስል አለን። ግልጽነትን መረን ከመኾን ለመለየት ዕድሜና ብስለት ያልሰጠን —ስናሳዝን።

ሰው ግን በልቡ ከሞላው በቀር በአፉ ሊወጣ የሚችል ምንም ነገር የለም  ከልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።”ማቴዎስ 12፥34
እርግጥ ነው አንዳንዴ ሰው በብስጭት ከአፉ ያልተገቡ ቃላት ሊወጡ ይችላሉ። ደጋግሞ ደጋግሞ የታቀደ በሚመስል መልኩ ሰውን የሚሰብር ሰው ግን “እኔም ሰው ነኝ” ብሎ ሊመሳሰል አይችልም።

“ይቅርታ” ማጣፊያው ሲያጥረን የምንመዘው ራስን የመከላከያ መሣሪያ አይደለም። “ይቅርታ” ማለት ድጋሚ ያንን ጥፋት ላለማድረግ መወሰን እንጂ፤ “የቀደመ ጥፋቴን እርሱልኝ” የሚል የብልጣ ብልጦች ይግባኝ ሊኾን አይገባም። ብዙዎች ግን ያለ ምንም ማመዛዘን ከአፋቸው አጥንትን የሚሰብር ቃል እያወጡ ደግመው ደግመው “ይቅርታ” በማለት የቃሉን ጉልበት ይፈትናሉ።

ይቅርታ” ማለት ግን “ቀጣይ በደንብ አስቤ አወራለኹ” ማለት ጭምር ነው። ይቅርታ ማለት ግን “ቀጣይ በቂ መረጃ ሳይኖረኝ አላወራም” ማለት ጭምር ነው። ይቅርታ ማለት ግን “የማወራው ነገር የሚያመጣውን ቅጣትና ወቀሳ ሙሉ ለሙሉ እቀበላለኹ” ማለት ነው። ካልኾነ ግን “ይቅርታ” የፍቅር መግለጫ፣ የሕግ ፍጻሜ የኾነውን ያሕል … የክፉ  ሰዎች መሹለኪያ መንገድ  እና የተደጋጋሚ ጥፋቶች ማምለጫ ሆኖ ይቀጥላል።
—————————
ይቅርታ ከብዙ በሽታዎች የሚፈሰው መድኃኒት ነው፡፡ ራሳችንን ከመመረዝ ነጻ ማውጣት የምንችለው በይቅርታ ነው፡፡ ይቅርታ ልክ የተቀደደ ልብስን እንደሚሰፋ የሚያውቅ መርፌ ዓይነት ነው። በየቀኑ የይቅርታን መድኃኒት እየዋጥን መፈወስ ስንችል ለምን ይሆን ራሳችንን የምንመርዘው?
    © አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ።"
አባ ኤፍሬም አረጋዊ


ከአበው መነኮሳት አንዱን "ትሕትና ምንድር ነው?" ሲሉ ጠየቁት። እርሱም ሲመልስ "የጎዳህ ወንድምህ ወደ አንተ መጥቶ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ይቅር ካልከው እርሱ ትሕትና ነው።" አላቸው። ለካስ ይህም ትሕትና ነው!!!

╔═ኦ══════════ር══╗
💚 @Ethiopian_Ortodoks💚
╚═ቶ══════════ዶ══╝
♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲       
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ 

5k 0 67 3 105

✝️✨ ጾመ ነነዌ ✨✝️

ነነዌ የአሦር ጥንታዊ ከተማ ነበረ። ፍርስራሹ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቅ ዳርቻ በሞሱል ዙሪያ አሁን አለ። ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትሆን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ የምትጀመረው ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አትለቅም ቀኑ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር 17 ድረስ ነው ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ እስከ የካቲት 24 ቀን ይረዝማል፡፡

በእነዚህ 35 ቀናት ውስጥ ስትመላለስ ከፍ ዝቅ ስትል ትኖራለች ከተጠቀሱት ዕለታት አባቶች እንደ ደነገጉት አትወርድም አትወጣም በዚህ ዓመትም የካቲት 03 ቀን ትጀመራለች፡፡ አጭርና የሦስት ቀን ጾም ብትሆንም እንኳ እጅግ ብዙ ጥቅምን የምታስገኝ ጾም ናት፡፡ ይህም "በመባጃ ሐመር ከፍና ዝቅ ስለሚል ቊጥሩ ከአጽዋማት ሐዋርያት ነው፡፡ አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል፡፡" ታዲያ ነነዌ ማን ናት? ነነዌ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ ናምሩድ በተባለው ሰው ተመሠረተች፡፡ ለአሰራውያን መናገሻ ከተማ ነበረች፡፡ ሰፊና ውብ ከተማ ሆና የተገነባች ናት፡፡ [ዘፍ. 10:1] አስር ከእስራኤላውያን ጋር ጠላት ሆነው በተቀናቃኝነት የኖሩ መንግሥታት ናቸው፡፡ ዮናስ የተላከው ተቀናቃኝ ወደ ሆኑት ሕዝቦች ነው፡፡ ከተማዋ ውብና ብዙ ሕንፃዎች ነበሩባት የከተማዋ ቅጽር ርዝመት 12 ኪ.ሜ እንደነበር በውስጧ ብዙ ሕንፃዎች ተሠርተውባት ነበር፡፡ የባቢሎን መንግሥት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከተማዋን አፈረሳት፡፡ [ዮና.4.1]
 
ሕንፃዎቿን የሠራቸው ሰናክሮም ሲሆን በስተመጨረሻ በ621 ዓ.ዓ የባቢሎን መንግሥት አፍርሷታል፡፡ ነነዌ ዛሬ የኢራቅ ከተማ ምሱል ናት በኩሽ ልጅ ናምሩድ በ1800 ዓ.ዓ ተቆረቆረች፡፡ ሽታር ወይም አስታሮትን ያመልኩ ነበር በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ገጥሟታል፡፡

ታዲያ ለነነዌ ሰዎች የተላከው ዮናስ ከአባቱ አማቴ እና ከእናቱ ሰና እንደተወለደ ታሪኩ ይነግረናል፡፡ ዮናስ ኤልሳዕ ያዳነላት የሰራጵታዎ ሴት ልጅ ነው የሚሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን ይነግሩናል፡፡ ነገር ግን ስለ ነቢዩ ዮናስ ጥልቀት ያለው ታሪክና መረጃ በስፋት አልተገለጸም፡፡ የስሙ ትርጉምም ቢሆን በእብራይስጥ ቋንቋ ርግብ የሚለው ትርጉም እንደሚገልጸው መተርጉማኑ ይገልጻሉ፡፡

ከእግዚአብሔር ዘንድ ለዮናስ የመጣው መልእክት "ክፋቷ በእኔ ፊት ወጥቷልና ወደ ታላቂቷ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ፣ በእርሷ ላይ ስበክ፡፡" [ዮና. 1.1] የሚል ነበር፡፡ ዮናስ ግን ጥሪውን መቀበል ባለመፈለጉ ኮበለለ፡፡ ከእግዚአብሔር መኮብለል አያዋጣምና ነብዩ ዮናስ በትልቅ አሣ እንዲዋጥ ተደረገ፡፡ በዚህ ውስጥ ዮናስ የትንቢት ቃሉን ለነነዌ ሕዝብ ማድረስ እንዳለበት ተረዳ፤ እግዚአብሔር ለኹለተኛ ጊዜ የነገረውን ድምጽም ሰምቶ ወደ ነነዌ ሄደ፡፡

በወቅቱ ነነዌ እጅግ ታላቅ የሆነች ከተማ ነበረች፡፡ በአርኪዮሎጂ ግኝት እንደተረጋገጠውም ከተማዋ ነቢዪ ዮናስ እንዳለው የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ (ዮና.3.3) ነበረች፡፡ በአሁኑ ወቅት እንዳሉ ከተማዎች ሁሉ ሕዝብ የበዛበት ነበረች፡፡ ከመቶ ሃያ ሺህ በላይ ሕዝብ ይኖርበት እንደነበረም በዚያው በነቢዩ ዮናስ መጽሐፍ ላይ ተጠቀወሶ እናነባለን፡፡ [ዮና.4.1] ሆኖም ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ እግዚአብሔርን እጅግ የሚያሳዝን ኀጢያት ይሠራ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ነብዩ ዮናስ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ነነዌ ሕዝቦች ይዞ ሄደ፡፡ ነነዌ እንደምትገለበጥም ተነገራቸው፡፡ 

በዚህ ታሪክ ውስጥ ትልቁን ትምህርት የምናገኘው እዚህ ጋር ነው፡፡ እግዚአብሔር የንስሐ ጥሪን ለኁሉም ያደርጋል፡፡ ከየሰው በኩል የሚሰጠው ምላሽ ግን የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ የነነዌ ንጉስ ከተማይቱ እንደምትጠፋ በሰማ ጊዜ "ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱንም አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ በዐመድ ላይ ተቀመጠ፡፡" [ዮና.3.6] ከዚህም በኋላ በነነዌ ሕዝብ ዘንድ ጾም እንዲታወጅ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "ማንም ሰው ወይም እንስሳ፣ ከብትም መንጋም ሆነ የበግ መንጋ፤ ምንም ነገር አይቅመስ፤ አይብላ፤ ውሃም አይጠጣ፡፡ ነገር ግን ሰውም እንስሳም ማቅ ይልበስ፤ ኁሉም አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጩህ ሰዎችም ኁሉ ክፉ መንገዳቸውንና የግፍ ሥራቸውን ይተው፡፡ እና እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቁጣው ይመለስም እንደሆነ ማን ያውቃል" [ዮና. 3:7-9] በዚህም ጥሪ ምክንያት ሕዝቡ በጾም ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡ 

እግዚአብሔርም ለዚህ የሰጠው ምላሽ እንዲህ ነው፡- "እግዚአብሔርም ምን እንዳደረጉና ከክፉ መንገዳቸውም እንዴት እንደ ተመለሱ ባየ ጊዜ ራራላቸው፤ በእነርሱም ላይ ሊያመጣ ያሰበውን ጥፋት አላደረገም፡፡" [ዮና. 3:10]

ነነዌና አንዳንድ ነገሮች
ሀ. በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የዚህ ጾም ስም "የዮናስ ጾም" ይባላል፡፡ ሆኖም ግን ቀደምት መዛግብት ላይ የሠፈሩ መረጃዎች (የነነዌ ጾም) በሚለው ይሄዳሉ፡፡ እዚህ ጋር የምንዘክረው የነነዌ ሰዎች የጾሙትን ጾም ብቻ ሳይሆን ነብዩ ለሦስት ቀን በአሣው ሆድ ውስጥ መቆየቱን እናሳስባለን፡፡

ለ. የዚህን ጾም ታሪክ ወደ ኋላ ይዘን ስንሄድ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እናገኛለን፡፡ ይህ ጾም በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲጾም የነበረ ነው፡፡ በዚህም ጾም ምክንያት ብዙዎች ከአደጋ ለመዳን ችለዋል፡፡   
 
ሐ. ለመሆኑ ነብዩ ዮናስን የዋጠው የባሕር እንስሳ ምንድር ነው; ግእዙ (ዐንበሪ) ይለዋል፡፡ ብዙዎች (ዐሣ ዐንበሪ) በማለት ዛሬ ላይ በተለምዶ የምናውቀው ትልቅ ዐሣ ዮናስን እንደዋጠው ይናገራሉ፡፡ ግሪኩ (ኬቶስ) ይለዋል፤ ትርጉሙም ታላቅ የባሕር እንስሳ ማለት ነው፡፡ ሊቁ ኒቆዲሞስ ገዳማዊ st. Nicodemus the hagiorite ስለዚህ (ኬቶስ) የተባለ የባህር እንስሳ ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
ዕውቀትን እና መማርን ለሚወዱ ሰዎች ስለ ኬቶስ እንዲህ ብለን እንናገራለን፡፡ ቴዎክለስ እንዳለው ከሆነ ኬቶስ ከአስር መርከብ የበለጠ ነው፡፡ አሊያንስ እንደተናገረው ደግሞ ከዝሆን ዐምስት ጊዜ ይበልጣል፡፡ ኤራቶስቴንስ ሲናገር ደግሞ ሀምሳ ኪውቢት (23 ሜትር) በላይ ርዝማኔ አለው ይለናል፡፡ --- እነዚህን ጥንታዊ ሰዎች በመከተል ታላላቅ አባቶች ስለ ኬቶስ ግዙፍነት ይናገራሉ፡፡ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ኤቶስ ሰውነቱ እንደ ትልቅ ተራራ ያለ እንደሆነ እና ደሴት እንደሚመስል ይነግረናል፡፡ (አክሲማሮስ ዘባስልዮስ ድርሳን ሰባት) ታላቁ አምብሮስ ደግሞ ሲናገር ኬቶስ ሲዋኝ ቀና ቢል ሰማይን እንደሚነካ ሁሉ ግዙፍ እንደሆነ እና ትልቅነቱ እንደ ደሴት ወይም እንደ ተራራ እንደሚመስል ይናገራል፡፡ ኤውስጣቴዎስ ዘአንጾኪያ ደግሞ በአክሲማሮስ ሲነግረን አስፒዶኬሎን የታለው ኬቶስ እጅግ ግዙፍ ከመሆኑ የተነሣ ሰዎች ሲያዩት ደሴት እንደሚመስል ተናግሯል፡፡

ሐዋርያትም ሰብአ ነነዌ የተነሣህያን አብነት ናቸውና ሥርዓቱም ጾሙም አይቀር ብለው ሠርተውታል፡፡ እኛም በጾምና በጸሎት ከፈጣሪያችን ምህረትና በረከት ለማግኘት ስንል እንጾመዋለን፡፡ በተጨማሪም ይህ ጾም ለዐብይ ጾም መዘጋጃ በመሆን ያገለግላል፡፡

ጾሙ ከመግባቱ አስቀድሞ ኦርቶዶክሳውያን ሁላችን ንስሓ እንግባ።
ከዚህ ንስሓ ጋር የታወጀውን የየነነዌ ጾም ጠዋት በኪዳንና ከሰዓት በቅዳሴ ማታ ደግሞ በጸሎተ ምሕላ በየአጥቢያችን እየተገኘን አምላካችንን እንማጸነው።

መልካም ጾም ይሁንልን 🙏🤍
💚 💛 ❤️
@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks


ጾመ ነነዌ ሰኞ የካቲት ፫ ይገባል።

5.8k 0 35 22 149

*አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሷል፤ ያበሰብሷልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ

@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks


ትልቁ መሳሪያችን ፀሎት ነው
እስካሁን ያላነው በአባቶች ፀሎት ልመና፣ በእናቱ በድንግል ማርያም፣ በፃድቃን መላእክት አማላጅነት ነውና
አሁንም የአባቶች ፀሎት ይጠብቀን🙏
የድንግል ማርያም፣ ፃድቃን መላእክት አማላጅነት የልጇ የወዳጇ ይቅር ባይነት አይለየን🙏

5.8k 0 9 20 186

🥰 ደስ የሚል መዝሙር
♡ ናና አማኑኤል ♡


ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
ናና አማኑኤል ና መድኀኒቴ
ፍቅርህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/

የምሕረት አባት     አማኑኤል
የቸርነት ጌታ           ''
ፊትህ የተመላ         ''
ሁሌ በይቅርታ         ''
ካለው ፍቅር በላይ    ''
አባት ለአንድ ልጁ     ''
አምላክ ይወደናል       ''
አይጥለንም ከእጁ      ''

መድኃኒቴ ልበል        አማኑኤል
ድኛለው በሞትህ         ''
ቁስሌ ተፈውሷል         ''
በቁስልህ በሞትህ        ''
ስሸጥህ አቀፍከኝ         ''
ስወጋህ አይኔ በራ         ''
በፍቅርህ አወጣኽኝ       ''
ከዚያ ከመከራ               ''

አንተ ከኔ ጋር ነህ          አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ                    ''
ድል አርገህልኛል             ''
የጭንቄን ተራራ               ''
በጉባኤ መሀል                ''
አፌ አንተን አወጀ             ''
የከበረ ደምህ                 ''
ነፍሴን ስለዋጀ                ''

የድንግሏ ፍሬ                አማኑኤል
የበላቴናዋ                       ''
የቤቴ ምሰሶ                     ''
የነፍሴ ቤዛዋ                    ''
መሠረቴ አንተ ነህ              ''
ያሳደገኝ እጅህ                  ''
አተወኝም አንተ                  ''
ስለሆንኩኝ ልጅህ               ''

ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
✝ሼር
👉
@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks

5.8k 0 101 5 85

“አካሔድህን አስተካክል”

“ከአፍቃሪያችን ክርስቶስ
ያገኘነው ስጦታ እንዲህ ነው ተብሎ በቃላት መግለጥ የሚቻል አይደለም፡፡ እንዴት ያልን እንደሆነ እኛ በኀጢአት እየተንፏቀቅን I'mባለንበት ወራት እርሱ በምሕረቱ ጐብኝቶናልና፡፡ ኀጢአት ሸክም በሆነችብን ጊዜ እርሱ በእኛ ቦታ ተገብቶ ተሸክሞልናልና፡፡ በዚህ የማይለካ ፍቅሩ ከዲያብሎስ አገዛዝ ወደ መንግሥቱ አፈለሰን /ቈላ.1፡14/፡፡ እኛው ራሳችን ርቀን እርሱ ራሱ አቀረበን፡፡ እኛ ራሳችን በድለን እርሱ ካሠልን፡፡ ተወዳጆች ሆይ! ይህን ሁልጊዜ ከልቡናችን አናውጣ፡፡ የተሠጠንን ነጻ ሥጦታ አንዘንጋ፡፡ከምን እንደወጣን አንርሳ፡፡

ሰው ሆይ! የተጠራኸው ወደ ዘለዓለም ሕይወት ነው፡፡ የተጋበዝከው ወደ ልጁ መንግሥት ነው፡፡ ታድያ አንተእዚህ ስለምን ታንጠራራለህ? ስለምን እዚህ ትቀመጣለህ? ስለምን እዚህ
ትንፏቀቃለህ? ስለ ሥጋህ ድሎት ብዙ ዋጋን ትከፍላለህ፡፡ ታድያ ስለ ነፍስህስ ትንሽ አይገድህምን? ወደ ሕይወት ተጠርተህ ሳለ ስለምን ወደ ሞት ትሮጣለህ? ቢያስፈለግ ይህ
ያገኘኸው ስጦታ ላለማቆሸሽ ብዙ መሥዋዕትነትን መክፈል በተገባኽ ነበር፡፡ ብዙ ሰይፍን መታገሥ በተገባህ ነበር፡፡ ወደ እሳት እንኳ ብትጣል ስለ ድኅነተ ነፍስህ መቋቋም ይገባህ ነበር፡፡
ወዳጄ ሆይ! እስኪ ንገረኝ! የመንግሥተ ሰማያት ዜጋ ለመሆን ተጠርተህ ሳለ ራስህን የዚህ ዓለም ዜጋ ማድረግህ ስለምንድነው? እንደምን ያለ ስንፍና እንደያዘህስ ታስተውላለህን? ይህን
ዓለም የመውደደህ ምስጢር ምቾትን መሻትህ ያሳያል፡፡ በዚህ ዓለም በምቾት መኖርን የሚሻሰው ደግሞ ክርስቲያን መሆን፣ ክርስቲያን ተብሎ መጠራት፣ ክርስቶስን መስሎ መመላለስ
ምቾት ሳይሆን እስር ቤት መስሎ ይታየዋል፡፡ ሁላችንም ወደዚሁ ቈጥ ካስገባን ሰነባብተናል፡፡ ከዚህች ዓለም ጋር የተወዳጀ ግን ምንም ክርስቲያን ቢባልም ምንም በአርባና በሰማንያ ቀኑ የሥላሴን ልጅነት ቢያገኝም ክርስቲያን ክርስቲያን መሽተቱ እየጠፋ ይሔዳል፡፡በዚኽ ዓለም ወጥመድ ተቀፍድዶ ይያዛል፡፡

ወዳጄ ሆይ! ይህን አድምጥና ፍርሐትና ረዓድ ይያዝህ!!! ምንም በቤተ መንግሥት
ብትኖርም፣ ምንም በተሽቆጠቆጠ መኖርያ ቤት ብትኖርም እንደተመቸህ አድርገህ
አትንገረኝ፡፡ አንተ የምትኖርበት ኑሮ ለእኔ ወኅኒ ቤት ነው፤ ያውም ሊፈርስ የተቃረበ ቤት!!!
ይኽ ቤትህ ክረምት ሲመጣ ይፈርሳል፡፡ ክረምት (የመጨረሻይቱ ቀን) ስትመጣ ቤትህ ይፈርሳል፡፡ ክረምት ስላልኩህ ደግሞ “ለሁሉም ሰው ክረምት ከሆነበት እኔ ከማን እለያለሁ” ብለህ አታስብ፤ ይህቺ ቀን ለሁሉም ክረምት አትሆንምና፡፡ ዳግመኛም እግዚአብሔር ሌሊትና
ቀን ብሎ ጠርቷታልና፡፡ ሌሊት የምትሆንባቸው ለኀጥአን ነው፤ ቀን የምትሆንላቸው ደግሞ ለጻድቃን ነው፡፡ እኔም ክረምት ብዬ መናገሬ ከዚህ አንጻር ነው፡፡ ሁላችንም ክረምት ሲመጣ
መብረር እንችል ዘንድ በበጋው ላይ ካላደግን የገዛ እናቶቻችን እንኳ ቢሆኑ ትተዉን ይሔዳሉ እንጂ በዚያ ሰዓት እኛን መሸከም (ማዳን) አይቻላቸውም፡፡ የገዛ እናቶቻችን እንኳ በረሃብ እንሞት ዘንድ ትተዉን ይሔዳሉ፡፡ ቈጡ (ቤቱ) በላያችን ላይ ሲፈርስ እኛን መታደግ አይቻላቸውም ፡፡ እግዚአብሔር ቤቱን ሲያፈርሰው፣ አሮጌው እንደ አዲስ ሲያደርገው፣ እያንዳንዱ እንዳልነበረ ሲሆን እኛን መርዳት የሚችል አንድ ስንኳ አይገኝም፡፡ የዚያን ጊዜ ጌታን በአየር ላይ መገናኘት የማይችሉቱ፣ የመንፈስ ክንፍ ተሰጥቶአቸው መብረር የማይችሉቱ ቤቱ በላያቸው ላይ ይፈርስባቸዋል፡፡ ስቃይ የስቃይም ስቃይ ይሆንባቸዋል፡፡ ስቃዩ
የስቃይ ስቃይ ነው ማለቴ ከ እስከ የሚባል ስለሌለው ነው፤ ለዘለዓለም ስቃይ ስለሆነ ነው፡፡ ክረምት ብዬ መጥራቴ ስለዚሁ ነው፤ ኧረ እንደውም ከክረምት የባሰ ነው፡፡ እንዴት ያልከኝ እንደሆነ በዚሁ፡ክረምት ላይ የሚዘንበው ውኃ አይደለምና፤ እሳት እንጂ፡፡ በዚሁ ክረምት ዙርያህ ጨለማ የሚሆነው ከደመና ብዛት የተነሣ አይደለምና፤ ጽኑ ጨለማ እንጂ፡፡ የብርሃን
ጭላንጭል የሌለው ጨለማ እንጂ፡፡ እዚህ የሚገቡት ሰዎች ተድላ መንግሥትን ማየት
አይቻላቸውም፤ ሰማያትን ማየት አይቻላቸውም፡፡ ከመቃብር ውስጥ የባሰ ጨለማ ይውጣቸዋል እንጂ፡፡
ወዳጄ ሆይ! አሁንስ አትርድምን? ወዴት እየሔድክ እንደሆነ አታስተውልምን? ፊትህንስ ወደ ልጁ መንግሥት አታደርግምን?”… አካሔድህን አስተካክል…

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )

@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks



5.7k 0 40 5 124

በጨነቃችሁ በችግራችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ አማኑኤል አለሁ ይበላችሁ።

🥰🙏🥰

5.4k 0 7 35 223

❤️‍🩹" የተሻለ ነገር አስብህልኝ ነው መከራ የበዛው " በሚለው ዝማሬ የምትታወቀው ዘማሪት መስከረም ወልዴ ስርዓተ ጋብቻ ፈጸመች 🥰

በዝማሬ አገልግሎት ቅድስት ቤተክርስቲያንን እያገለገለች የምትገኘው እህታችን ዘማሪት መስከረም ወልዴ በስርዓተ ቁርባን በአገልግሎት አጋራችን ከሆነው ወንድማችን ጸጋአብ ኢያሳያስ ጋር በአርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ገዳም ስርዓተ ጋብቻ ፈጽማለች።

የመንፈስ ቅዱስ ማኅተም ያለበት፣ የንጽህና መኝታ ፣ ፍሬው የተባረከ፣ በሁለት ገላ አንድነት የሚገለጥበት የተዋሕዶ ምልክት ወደ ሆነው ቅዱስ ጋብቻ ትደርሱ ዘንድ እንኳን ቅድስት ሥላሴ ረዳችሁ!!!

በእዚህ ቤት ድንግል ከእነ ልጇ ትግባበት!!!
እንደ ዶኪማስ ቤት ያኑራችሁ!
የአብርሐም እና የሣራ በረከት ይደርበት።
✤✞✤
@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks


" ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥
እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ
ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።” — ሮሜ 9፥5


መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ።
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።

መልካሙን ሁሉ የምትሰሙበት ሌሊት ይሁንላችሁ🙏🥰✝

6.7k 0 27 13 167


6.6k 0 11 1 149
Показано 20 последних публикаций.