በኢትዮጽያ ያለውን የቤት ፍላጎት ከአቅርቦቱ ጋር ለማመጣጠን በዓመት በአማካኝ 471 ሺህ ቤቶችን መገንባት ያስፈልጋል ተባለ
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እንደገለፀው በከተሞች ያለውን የቤት አቅርቦት ችግር ለመፍታት በዓመት በአማካኝ 471 ሺህ ቤቶችን መገንባት ይጠይቃል ብሏል።
ኢንስቲትዩቱ ተመራማሪ የሆኑት ሰለሞን ጥላሁን የቤት ልማት የፍይናንስ ስረዓት ላይ ያቀረቡትን ጥናት ዋቢ አድርጎ ኢፕድ እንደዘገበው በኢትዮጵያ 68 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ቤት ለመስራት የብድር አገልግሎት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።
ይህን ተከትሎ የሀገሪቷ መንግስት በ10 ዓመት እቅዱ 4 ነጥብ አራት ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት እየሰራ መሆኑና በአማካኝ የሚያስፈልገውን 471 ሺህ ቤት የሚያሟላ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል ።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily