ኢትዮጵያ ለተለያዩ የገቢ እና የወጪ ምርቶች አዲስ አስገዳጅ ብሄራዊ ደረጃዎችን ተግባራዊ ልታደርግ ነው
ኢትዮጵያ ከሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለተለያዩ የገቢ እና የወጪ ምርቶች አዲስ አስገዳጅ ብሄራዊ ደረጃዎችን ተግባራዊ ልታደርግ መሆኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታዉቋል።
አዲሶቹ ደንቦች የተለያዩ ምርቶችን የሚያጠቃልሉ ሲሆን እነዚህም የግንባታ መስታወት፣ የአሉሚኒየም እና የአሉሚኒየም ቅይጥ ምርቶች፣ ቀለሞች፣ የተሽከርካሪ መቀመጫ ቀበቶዎች፣ የሞተር ሳይክል ሄልሜት፣ የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች እና የተሽከርካሪ ፍተሻ ደረጃዎችን ያካትታሉ።
ከሰኔ 1 ጀምሮ የእነዚህ አዲስ ቁጥጥር የተደረገባቸው እቃዎች አስመጪ እና ላኪዎች እቃዎቻቸው ከመገበያያ በፊት ከሚኒስቴሩ ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ካዉንስል የጸደቀውን መመዘኛዎች መከበራቸውን ያረጋግጣል።
በባንክ ፈቃድ ወይም በፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ ለተገዙ እና በአሁኑ ጊዜ በመጓጓዣ ላይ ላሉት ምርቶች የአራት ወራት የእፎይታ ጊዜ መሰጠቱ የተገለፀ ሲሆን ይህም ንግዶች ከአዲሱ ደንቦች ጋር ለመላመድ ጊዜን ይፈቅዳል ተብሏል።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily