ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ፋይናንስ ዘርፍ የፖሊሲ እና የቅንጅት ክፍተቶች እንዳሉባት ተጠቆመ
ኢትዮጵያ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆኑ የፋይናንስ ተግባራት " አረንጓዴ ፋይናንስ" ውጤታማነት የጎደሉ የፖሊሲ ማዕቀፎችና በመንግሥት ኤጀንሲዎች መካከል የቅንጅት ችግሮች እንደሚታዩባት አንድ ጥናት አመለከተ ።
ከቀናት በፊት በኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ እና በካፒታል ገበያ ባለስልጣን አዘጋጅነት በተካሄደው መድረክ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ሊሆኑ በሚችሉ አረንጓዴ የፋይናንስ ተግባራት ላይ የተደረገው የጥናት ግኝት" ቀርቧል።
በዚህ ጥናት፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ፋይናንስን ለመጠቀም አቅም ማነስ፣ ደካማ የመሠረተ ልማት፣ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራሞች አለመመጣጠን፣ የማይጣጣም የአደጋ አስተዳደር፣ የፖሊሲ አለመጣጣሞች፣ የቅንጅት ጉድለቶችና የብሔራዊ የካርቦን ክሬዲት ምዝገባ እጥረት እንደሚታይባት ጠቁመዋል።
ችግሮቹን ለመፍታትና የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ ኢትዮጵያ ብሔራዊ የካርቦን ክሬዲት ምዝገባ እንድትመሰርትና የተቀናጀ የገንዘብ ድጋፍ ሞዴሎችን እንድትቀበል በጥናቱ ተገልጿል።
በተጨማሪም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ቅንጅት ማጠናከርና የአረንጓዴ ፋይናንስ ተነሳሽነቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተግበር አቅምን መገንባት እንደሚያስፈልግ ከጥናቱ ካፒታል ለመረዳት ችሏል።
Read More
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily