የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዓለም ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ሊቀበል ነው
መንግስታዊዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአለም ባንክ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ድጋፍ በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለመቀበል በዝግጅት መሆኑ ተጠቆመ ።
ከ650 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከተመደበው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በዚህ የመጀመሪያ ዙር ዝውውር እንደሚካተት ይጠበቃል።
ይህ በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ድጋፍ የአለም ባንክ የፋይናንስ ሴክተርን የማጠናከር ፕሮጀክት አካል ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋይናንስ አቅሙን እንዲያሳድግና የኢትዮጵያን ሰፋ ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እንዲደግፍ ያለመ ነው።
ባንኩ ይህንን ድጋፍ ለማግኘት መንግስት ቦንድ ማውጣትንና የቦርድ ስብጥርን ማስተካከልን ጨምሮ የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቷል።
ይህን ተከትሎ በሚቀጥለው ሳምንት ቢያንስ 350 ሚሊዮን ዶላር መቀበል እንደሚችል ይጠበቃል። ይህ የገንዘብ ድጋፍ በተለይም ባንኩ ቀደም ሲል ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በሰጠው ያልተመለሰ ብድር ምክንያት ያጋጠሙትን የፋይናንስ ተግዳሮቶች ለማቃለል ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት የንግድ ባንኩን ካፒታል ለማጠናከር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተገልጿል። ባለሙያዎች ይህ የዓለም ባንክ ድጋፍ የሀገሪቱን የፋይናንስ ሴክተር ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ይስማማሉ።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily