#ጓደኛ ማለት ይሄ ነው ↙
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሸኽ ሀሰን አልበስሪ እንዲህ በማለት ስለ ሷሊህ ጓደኞች አወሱ…
'
ሷሊህ ጎደኞችን አብዙ ከእነሱ ጋርም ተዋዋሉ ለዛች ለጭቅ ቀን ለቅያም ቀን ሸፋአ ይሆንዋችኃል በማለት ሲናገሩ… ከአድማጮቹ አንዱ እንዴት ያ ሸኽ በማለት ጥያቄ ያቀርባል…
'
ሸኹም እንዲህ በማለት በጣፈጠ አንደበታቸው አስረዱት…
የጀነት ሰዎች ጀነት የጀሃነም ሰዎች ጀሃነም ከገቡ በኃላ የጀነት ሰዎች ስለሚያውቋቸው ሰዎች ይጠያየቃሉ ይተዋወሳሉ በዛ መካከል ከእነሱ ውስጥ አንዱ የዱንያ ጓደኛውን ካላገኘው ጀሃነም መግባቱን ካረጋገጠ የእሳት መሆኑን ከሰማ … ወደ ጌታው እጆቹን ዘርግቶ እንዲህ በማለት ዱአ ያደርጋል"" ያ ረብ የጀነት ደስታዬም ምቾቴም ከዚህ ጀሃነም ካለ ባርያህ ጓደኛዬ ውጭ ሙሉ አትሆንልኝም"" በማለት ጌታውን የጓደኛውን ወደ ጀነት መምጣት አጥብቆ ይማፀናል ይለምናል …
ምን እነደሚፈጠር ታውቃላችሁ????!!!!
'
አሏህ ሱብሃነሁ ወተዕላ ዱአውን ይቀበለውና ያን የሚወደውን ጓደኛውን ከጀሃነም እሳት ቅጣት ወደ ጀነት ምቾት ድሎት እንዲዘዎወር ያደርግለታል…በሱ በአላህ ማሃሪነት ለዛ ለሷሊህ ባርያው ክብር ጀሃነም እሳት ውስጥ የነበረውን ጓደኛውን ወደ ጀነት ድሎት ያመጣለታል…
'
'
ሱብሃነላህ አይደንቅም የ አላህ ራህመት ስፋቱ??!!
ከዛም የጀሃነም ሰዎች ባልደረቦቹ የነበሩት በሁኔታው በመደነቅ በእድሉ በመጓጓት… ይህ ሰው አባቱ ወይም ወንድሙ ሸሂድ መሆን አለባቸው አልያም መላኢካ ሸፋአ ሆኖት ይሆናል… በማለት የጉጉት ጥያቂያቸውን ያቀርባሉ… ነገር ግን መልሱ ከጠበቁት እና ካሰቡት ውጭ ነበር…
'
ዱንያ ላይ የነበረው ሷሊህ ጓደኛው እንደሆነ ሸፈአ የሆነው ይነገራቸዋል… ያኔ እንዲህ በማለት የቁጨት ቃላቸውን ይሰጣሉ…
{ ﻣﺎﻟﻨﺎ ﻣﻦ ﺷﺎﻓﻌﻴﻦ ﻭﻻ ﺻﺪﻳﻖ ﺣﻤﻴﻢ }
ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺸﻌﺮﺍﺀ
{አማላጂም ለእኛ የለንም አዛኝ ወዳጂም የለንም}
ምነው ወደ ዱንያ ተመልሰን ሷሊህ ጓደኞችን ባበዛንም በማለት የቁጭት ምኞታቸውን ያቀርባሉ…
ሸፋአ በአሏህ ሱብሃነሁ ወተአላ ፍቃድ ብቻ የምትፈፀም ከእዝነት በሮቹ አንዷ ናት… ለጠየቀው የሚሰጠውም ሆነ የሚነፍገው እሱ ራህመተ ሰፊው አላህ ብቻ እና ብቻ ነው።
'
በተከበረው ቃሉም ስለ ሸፋአ እንዲህ ይለናል…
{ ﻣﻦ ﺫﺍ ﺍﻟﺬﻱ ﻳﺸﻔﻊ ﻋﻨﺪﻩ ﺍﻻ ﺑﺈﺫﻧﻪ } ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ
{እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማነው}
{ ﻭﻻ ﺗﻨﻔﻊ ﺍﻟﺸﻔﺎﻋﺔ ﻋﻨﺪﻩ ﺍﻻ ﻟﻤﻦ ﺍﺫﻥ ﻟﻪ } ﺳﻮﺭﺓ ﺳﺒﺄ
{ምልጃም እሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም} ሲል ያረጋግጥልናል!።
ሰው በሰው ነውና ውበቱ አላህ ከሷሊህ ባርያዎቹ ይቀላቅለን፣ ሷሊህ የሆኑ ወዳጆችንም ያበርክትልን፣ እኛንም፣ ወዳጆቻችንንም ፣ቤተሰባችንንም፣ ሙስሊሙን ኡማ በአጠቃላይ ከሷሊሆች ያድርገን።
••⇝ https://t.me/Golden_Speech ⇜••