ፈተናውን እናልፍ ዘንድ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
『በ478 ኛው አመተ ሂጅራ ከፍተኛ ትኩሳት የቀላቀለ በሽታና ከባድ ወረርሽኝ በኢራቅ ፣ በሂጃዝና በሻም ውስጥ ተስፋፋ። በዚህም ምክንያት የዱር እንስሳት አለቁ ፤ ከብቶችም ይረግፉ ጀመር ፤ በነበረው አስፈሪ አውሎ ንፋስ ዛፎች ወዳደቁ ፣ ከተሞች በከባድ መብረቅ ተመቱ። በጊዜው የነበረው ኢስላማዊ መሪ አል ሙቅተዲ ቢ—አምሪላህ ( ﺍﻟﻤﻘﺘﻀﻲ ﺑﺄﻣﺮ ﺍﻟﻠﻪ ) ሰዎች ወደ አላህ እንዲመለሱ (ተውበት እንዲያደርጉ) ጥሪ አቀረቡ። በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ተጠናክሮ እንዲሰራ ወሰኑ ፤ የሙዚቃ መሳሪያዎች እንዲሰባበሩ ውሳኔ አስተላለፋ።
በአላህ ፍቃድ የተከሰተው ወረርሽኝና በሽታ ጠፋ።』
‹አልቢዳያ ወኒሃያ አብኑ ከሲር›
አማኝ ነው የሚባለው የኛ ሰው ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል አጨማላቂ ሆኖ ሳለ እንዲህ አይነት ፈተና ሲገጥመው ወደ አላህ ከመመለስ ይልቅ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የሸቀጥ ዋጋ በመጨመርና ሸቀጥ በማከማቸት የበለጠ ጌታውን ማስቆጣት የመረጠ ይመስላል።
ﻧﺴﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺴﻼﻣﺔ ﻭﺍﻟﻌﺎﻓﻴﺔ !
ነጋዴዎች አላህን ፍሩ !
ሀገርንና ህዝብን መውደድ በችግርና በፈተና ጊዜ የበለጠ ሊንፀባረቅ ይገባል እንጂ በፈተና ጊዜ ጨካኝና አረመኔ ራስ ወዳድ መሆን ፈጣሪንም ሀገርንም ከመክዳት ነው ። አህባቢ!
አሁን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ሰዎችን በመልካም የምናዝበት ከመጥፎ ተግባር የምናስጠነቅቅበት ወቅት ነው።
አላህ እኮ በኒ—ኢስራኢሎችን የረገመበትና ከራህመቱ ያራቀበት ዋነኛ ምክንያት በመልካም ባለ ማዘዛቸውና ከመጥፎ ባለ መከልከላቸው ነበር።
ረሱልም ﷺ እንዲሁ ከመጥፎ መከልከልና በመልካም ማዘዝን ስንዘነጋ የአላህ ቁጣ ሊሰፍንብን እንደሚችል አስጠንቅቀውናል።
ታላቁ ሰሀብይ አቡበክር (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) ሲናገሩ ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋሉ አሉ…
《ሰዎች መጥፎ የሆነን ስራ አይተው ባልከለከሉ ጊዜ ፤ አላህ ሁሉንም በቅጣቱ ሊቀጣቸው የቀረበ ይሆናል።》
አህመድ ዘግበውታል
ስለዚህ ሁላችንም እራሳችንን ከመጥፎ ስራ ቆጥበን ሌሎችን እናስጠንቅቅ። መልካም ስራን እየሰራን ሌሎችም መልካም እንዲሰሩ እናስታውስ።
በአላህ ፍቃድ ሁሉ ነገር
መልካም ይሆናል።
°° https://t.me/Golden_Speech °°
…አቡ ቁዳማ…