💞…
ድሮ በኒ ኢስራኢሎች ወንጀል አበዙና አላህ ሊቀጣቸው አንድ መላኢካ ላከ። መለኢካውም በከተማዋ ሲመጣ አንድ አላህን በብዙ የሚገዛ አቢድ ሰው ያገኛል። ከዚያም ወደ አላህ ይመለስና ‹‹ከአንተ በቀር ስለሌላ ጉዳይ የሌለው ሰው አገኘሁ። እሱ እያለ እንዴት ልቅጣቸው?›› አለው። አላህም ‹‹እንግዲያው ከእሱ ጀምር። አንተ የማታውቀው ጉዳይ እኔ ዘንድ አለ።›› አለው። መላኢካውም ወረደና ሁሉንም አጠፋቸው። ከዚያም አላህን ‹‹ያንን ባሪያህን ለምን እንዲጠፋ ፌድክበት?›› አለው። አላህም ‹‹እሱ ህዝቡ ሲበድለኝ እያየ አንድም ቀን ፊቱ ጠቁሮ አያውቅም። ከወንጀላችሁ ተመለሱ ብሎ አያስጠነቅቃቸውም። ይህ አይነት ሰው ለራሱም ለህዝቡም ስለማይጠቅም እንዲጠፋ ወሰንኩበት።›› አለው። እዚህ ፌስቡክ ላይ ሰዎች አላህን ሲክዱና ሲዞልሙ እያያችሁ ‹‹ተዋቸው! መብታቸው ነው!›› የምትሉ ሰዎች አላህ መጀመሪያ ቅጣቱን የሚያወርደው በእናንተ ላይ መሆኑን እወቁ። ከዱንያ አልፎ በጀሐነም ውስጥ አንጀታቸው እየተጎተተ የሚቀጡት ሀቅን ይዘው ሰዎችን ከወንጀል ለመመለስ ያልደከሙ ናቸው። አላህ ለአንድ ሰው የኢስልምናን ፀጋ ሲሰጠው ለሌላው ከማድረስ ዋጂብ ጋር እንጅ ለራሱ ይዞ እንዲንመፃደቅበት አይደለም። አላህ በሰጠው ኒዕማ ያልታገለ በእርግጥ ከሁሉም የከፋው ቅጣት ያገኘዋል።
•• https://t.me/Golden_Speech ••
••❥ ሰል ማን✍