Репост из: ገድለ ቅዱሳን
❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ አውሳብዮስን ወደ ግብጽ አገር ወስደው በዚያ ይገድሉት ዘንድ ህርማኖስ ንጉሡን መከረው "እርሱ በዚች አገር ከኖረ ያገር ሰዎችን በላይህ ያስነሣብሃልና ያሰብከው ምንም ምን መሥራት አትችልም" አለው። ንጉሡም ቅዱስ አውሳብዮስን ጽኑዕ ሥቃይን ያሠቃዩት ዘንድ ወደ ግብጽ አገር ወደ ቅፍጥ ገዥ ሉልያኖስ ዘንድ እንዲወስዱት ጻፈ ወደ መኰንን ሉልያኖስም በደረሰ ጊዜ በመንኰራኵር ሕዋሳቱን በመቈራረጥ በግርፋት አሠቃዩት። ዳግመኛም በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት ጌታችንም መልአኩን ልኮ ከመከራው ሁሉ አዳነው አጽናንቶም አረጋግቶ ያለ ጉዳት አስነሣው። ነፍሱንም ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት ወሰዳት የጻድቃንና የሰማዕታትንም መኖሪያ አየ ለርሱና ለአባቱ ለዘመዶቹም ያዘጋጀላቸውን ቦታዎች አይቶ ነፍሱ እጅግ ደስ አላት። ከዚያም በኋላ ወደ እሳት ማንደጃ ውስጥ ይጨምሩት ዘንድ መኰንኑ አዘዘ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ወርዶ እሳቱን እንደ ጠል አቀዝቅዞ ያለ ጥፍት የከበረ አውሳብዮስን አወጣው። መኳንንቱም እንዲህ ብለው መከሩት "መኰንን ሆይ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ እዘዝ ከእርሱም ትግል ታርፋለህ" እርሱም የአውሳብዮስን የከበረች ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና የካቲት23 ቀን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አውሳቢዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የካቲት23 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ወልደ_ፋሲለደስ_ሊቀ_ሖራ። ወቢጸ ብፁዕ መርቆራ። አውሳብዮስ ሰማዕት ትቤዝወኒ እምከራ። አርኢ ሊተ ለአምላክ መሐሪ ለአባልከ ምታራ። አመ ለነፍስየ ይትነበብ እኩይ ምግባራ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_23።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL