መቀሌ ውጥረት ነግሷል‼️
ዛሬ ለሊቱን ጀምሮ ብዛት ያለው ሰራዊትና መትረየስ የጫኑ ፓትሮል መኪኖች በመቀሌ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ እያደሩጉ እንደሚገኙ ታውቋል‼️
በደብረፂዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት መግለጫ ያወጣ ሲሆን ህዝባዊ ሰራዊታችን በከሃዲ ቡድን ሴራ አይፈርስም ብሏል።
ህወሓት በመግለጫው የግዚአዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ብሄራዊ ክህደት የፈጸሙ እና እየሰሩ ያሉ አመራሮችን በማባረር በጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ያላቸውን ውክልና አንስቻለሁ ያለ ሲሆን ነገር ግን ጊዚያዊ ፕሬዝዳንቱ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት ከህግና ስርዓት ውጪ ፀረ ህዝብ ተግባራቸውን ቀጥለዋል ብለዋል።
የህዝባችንን አንድነት በማደፍረስ የትግራይን ሁለንተናዊ አቅም በማዳከም ብሄራዊ ክህደት እየፈፀመ ያለው የቀድሞ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አሁን በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ለመፋለም የተደራጀውን የትግራይ ሰራዊት ለመበተን ድርጊቱን አጠናክሮ ቀጥሏል"ብሏል።
የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከስልጣናቸው እና ከኃላፊነታቸው ውጪ የትግራይ ጦር ግንባር አመራሮችን እና ጄኔራሎችን አግደዋል ያለው ህወሃት፣ይህ ማዕቀብ መሠረተ ቢስ እና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ቢሆንም ህዝባዊ ትግሉን ከህግ እና ከስርዓት ውጭ ለማድረግ ቡድኑ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑን ያሳያል ማለቱን አዩዘሀበሻ ከመግለጫው ተመልክቷል።
አዩዘሀበሻ
===================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/kumengergna