Фильтр публикаций




Репост из: እሁድ ገበያ (EHUDGEBEYA.COM)
ሰላም Ehud Tech እንሰኛለን ዌብ ሳይት ዲዛይን እናረግለን (website development)

1. የኢኮሜርስ ዌብ ሳይት /e-Commerce  Website
2. የንግድ ዌብ ሳይት /Trade investment Website
3. ብሎግ/ዜና ዌብ ሳይት/blog or News Website/
4. የፖርትፎሊዮ ዌብ ሳይት /Portfolio Website
5. የክስተት ዌብ ሳይት /event Organizing website
6.የግል ዌብ ሳይት /personal Website
7. የአባልነት ዌብ ሳይት /Membership website
8. ለትርፍ ያልተቋቋመ ዌብ ሳይት / NGO website
9.ማረፊያ ገጽ የዌኪ ዳታቤዝ ዌብ ሳይት /Database Management System
10.የሞባይል መተግበሪያ /Mobile app
11 የትምህርት ዌብ ሳይት /eLearning website

እንሰራለን  እርሶ  ብቻ  👇   ይደውሉ
+251940943866
+251955022429
+251948408675
በ Telegram @Am_ermi

ለማሳያ ይሆን ዘንድ ከዚህ ቀደም የሰራናቸዉ በጥቂቱ 👇
https://ehudgebeya.com
https://Zemenjob.com Coming Soon ... and more

You can get more in GitHub link 👇
https://github.com/Ermiyaslishan


Репост из: The Christian News
#አስቸኳይ መግለጫ

#ቤተክርስቲያን አስቸኳይ መግለጫ ሰጥታለች።

ከሰሞኑን ከአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው እና በግለሰብ በተከፈተ አካውንት ለማጭበርበር እየተሞከረ መሆኑን አስመልክቶ በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን አስቸኳይ መግለጫ ሰጥታለች።

ቤተክርስቲያን በመግለጫዋ የተሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን በመጥቀስ ምዕመናን ከአጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስባለች።

መግለጫውን የሰጡት የቤተክርስቲያኒቱ ም/ፕሬዘደንት ለወየው ስንሻው (መጋቢ) በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያንና በፓስተር ዮናታን አክሊሉ በትብብር የሚሰራ የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ እንዳለ ተደርጎ እየተሠራጨ ያለው ማስታወቂያ ፍፁም ሀሰትና ማጭበርበር ስለሆነ ቅዱሳን ከዚህ የማታለል ድርጊት ራሳችሁን እንድትጠብቁ ሲሉ ተናግረዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ #አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በበኩሉ ምዕመናን እንዲጠነቀቁ የማብራሪያ እና የማስጠንቀቂያ መግለጫ ሰጥቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተለቀቀው የባንክ አካውንቶችን በተመለከተ ቤተክርስቲያን በፍጹም የማታውቀው እንደሆነ በመጥቀስ ምዕመናን ከአጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

የመግለጫውን ሙሉ ቪዲዮ በፌስቡክ ገጻችን ይመልከቱ!!


ርዕስ አልቀይርም እደጋማለሁ እየሱስ እላለሁ 🙌❤️ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ


መዝሙረ ዳዊት 18፥2
እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።


Репост из: The Christian News
በቡታጅራ አካባቢ ላለ ለሚመለከተው የመንግስት አካላት ይድረስልን #ሼር #share #SharePost

የቡታጅራ መካነየሱስ #ቤተክርስቲያን የተሰጣት ቦታ ላይ ያለ አግባብ በመግባት መሪውን በመደብደብ ጭምር፣ የቤተክርስቲያን ንብረት የሆኑ ነገሮችን በማፈራረሰ የልጆች መማሪያ ስፍራዎችን በማፈራረስ፣ እንደ ደረሰን መረጃ ህጋዊ ያልሆነ የመሬት ወረራ ተደርጎባታል።

የቤተክርስቲያን ንብረት የህዝብ ንብረት ነው።

ህጋዊ ባልሆነ የሚደረግን በቤተክርስቲያን ላይ የሚደረግን ጥቃት እንቃወማለን።

የሚመለከተው አካል ተገቢውን ምላሽ በአስቸኳይ እንዲሰጠን ስንል እንጠይቃለን።

#ፍትህ #ለቤተክርስቲያን


ትኩረት ሁሉ ወደ ኢየሱስ🙌🏾🙌🏾🙌🏾


የመስቀሉ ስራ አይቀልብንም ❤️

@HaleluyaTube


በኛ ቤት ግን ዛሬም ኢየሱስ ሲመሽም ሲነጋም ብቻውን ጌታ ነው!   🙌🏾🥰

@haleluyatube


አንተ አለህበት ወይ

አንተ የሌለህበት ትልቅ ነገር ትንሽ ነው።ድልም ካላንተ ሽንፈት ነው፣ያተረፈ የመሰለውም ብዙ የጎደለበት ነው።ኑሃሚን በቤተልሔም ረሀብ ስለሆነ ያለ እግዚአብሔር ከባልዋ አቤሜሌክ እና ከሁለት ወንድ ልጆችዋ ጋር ወደ ሞዓብ ምድር ሄደች።በዚያም ባልዋን እና ሁለት ልጆቿን አጣች።እርሱ ከሌለበት የድሎት ሰፈር እርሱ ባለበት በተስፋ ቃሉ ፀንቶ መቆየት እና ከየትኛውም ውሳኔያችን በፊት አንተ አለህበት ወይ?ማለት እንዴት መልካም ነው።


ኢየሱስ ይወደናል ❤️💐


ስትደክሙበትም ይፈልጋቿል 😔

እውነት ነው ይሄ ጌታ ሁሌ ብርቱ ብንሆንለት እና እርሱን መስለን ብንኖርለት እንደ አባት  ደስ ይለዋል ነገር ግን እንደ ልጅ ስንደክምበትስ ፣ መኖር ሲያቅተንስ 😔 የሚተወን ይመስላቿል ? ቆይ አንዴ የሆን መዝሙር ላስታውሳቿ ...

ሁሉ እንዲድን አንዷ እንዳጠፋ
ሚገደው ያ መልካም እረኛ 🥰
በረት ያሉትን ይተውና ይሄዳል እርሷኑ ፍለጋ🐑
ያሰማታል ድምፁን አውጥቶ
በእቅፉ ሊያስገባት ጓግቶ 😍
ነፍሱን ስለ በጓቹ ያኖረ እውነተኛ ፍቅር እርሱ ነው
💯


ይሄ አባት ከእርሱ ጋር መዋል ስታበዙ ብቻ ሳይሆን አቅም አጥታቹ ስደክሙበትም ይፈልጋቿል

@Haleluyatube


እሱን ስሙት ❤️


የታረደው በግ የመስዋዕትነቱን ዋጋ ሊቀበል ይገባዋል ❤️


ይሳቅን ፍለጋ...

እግዚአብሔር ለአብርሀም ልጅ እሰጥሀለው ብሎት  ኪዳን ገባለት ነገር ግን የተነገረው የትንቢት ቃል ሳይፈፀም አመታቶች ይቆጠራሉ በዚህም ምክንያት አብርሃም ትኩረቱ ልጅ ላይ ብቻ ስለነበር በዚያም በዚም ብሎ ይወርስሀል ተብሎ የተነገረውን ልጅ ፍለጋ ሚስቱን ሳራን ትቶ ሞግዚቷ አጋር ጋር ገባ ነገር ግን ይሳቅን አገኛለው ብሎ አጋር ጋር የሄደው  አብርሃም ከአጋር ማግኘት የቻለው የተጠበቀውን ይሳቅን ሳይሆን ያልታሰበውን እስማኤልን  ነበር ....ለካስ የተስፍው ቃል ባለቤት ይስሀቅ ያለው ያረጀቺው ሳራ ጋር እንጂ ወጣቷ አጋር ጋር አልነበረም  ፤  አብርሃም ተሸወደ 😊 የተወደዳቹ እግዚአብሔር የእናንተን ይሳቅ ጠብቃቹት እንጂ አቋራጭ መንገድ ተጠቅማቹ እንድታገኙት በፍፁም አይፈልግም፤ ጌታ የነገራቹን ቃል የሚፈፅምበት የራሱ ጊዜ አለው እናንተ ብቻ የተባላቹትን በተባላቹት ስፍራ ላይ  ሆናቹ ጠብቁ

@thedayofPentecost
@HaleluyaTube






እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።
— ኢሳይያስ 40፥31


. እግዚአብሔር ጠብቁት 🙏

@HaleluyaTube


እግዚአብሔር መልካም ነው ❤️


እግዚአብሔር ጉዳይ አስፈፃሚ አይደለም 🔔

ይመስለኛል እኛ የዘመኑ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን እንደ "አምላክነቱ" ሳይሆን እንደ ጉዳይ አስፈፃሚያችን ማየት የተለመደ ነገር አድርገነዋል 😔

ለዚህም ምክንያት የምለው "የእግዚአብሔር ምህረት መለማመዳችን ነው":: እስኪ እዚህ ጋር አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ የምታመልኩት እግዚአብሔር ማነው ?
እናንተ የራሳችሁን እየመለሳችሁ እኔ ደግሞ ትንሽ ልበል እርሱ እግዚአብሔር እኮ ሰማይና ምድርን በቃሉ ያፀና እኛን በአምሳሉ የህይወትን እስትንፋስ እፍ ብሎ ህይወት የዘራብን .......... ወዘተ የእግዚአብሔር ስራ ይህ ነው ተብሎ ባያልቅም እኛ ግን እግዚአብሔርን ትከሻ ለትከሻ መለካካት ጀምረናል 😭

እግዚአብሔር ይጠብቀን እንጂ አንድ ቀን ተረከዙ የረዘመ ጫማ ለብሰን በለጥንክ ብለን አወዳደቃችን ሀያል እንዳይሆን እፈራሀለው 😭 ........ ብዙ ማለት ብፈልግም ሀሳቤን እዚህ ገታ ላድርግ ‼️

እግዚአብሔር አምላክ ነው 🔔
እግዚአብሔር ሉአላዊ ነው
🔔
እግዚአብሔር የሰራውም ያልሰራውም ሁሉ ልክ ነው
🔔
እግዚአብሔር ለምን አይባለም
🔔

@HaleluyaTube

Показано 20 последних публикаций.