እውነተኛ ሠለፊይ ነኝ ካልክ፣
በቢድዐህ ሰዎች ላይ ትክክለኛ የሠለፎች አቋም ይኑርህ!!
—————
ልብህ የተምይዕ በሽታ ሳይመርዘው ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር ያለህን መቀራረብ በፍጥነት አቋርጥ።
አንተ እውነተኛ የሀቅ ተከታይ ከሆንክ ስለ ቢድዐ ሰዎች ጠንከር ያለን ንግግር ስትሰማና ስታነብ አትበርግግ!። ይልቅ በስምህ ወደ ሰለፎች እንደተጠጋህ ሁሉ በተግባርህም ተከተላቸው!!
ብዙ ምስኪን የሆኑ ሰለፊይነትን የሚሞግቱ ወንድም እህቶች በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ከተለያዩ የቢድዐህ ባለ ቤቶች ግንኙነት አላቸው፣ ለዚያም ነው በየ ጊዜው አቋማቸውን የሚቀያይሩና በአቋማቸው መፅናት ሲያቅታቸው የሚስተዋለው። አንድ ሠለፊይ ነኝ ያለ ሰው በምንም መንገድ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር የሚገናኝበትና ንግግራቸውን የሚያደምጥበት መንገድ ሊኖር አይገባም!!። ምናልባት ጠንካራ እውቀት ኖሮት ረድ ሊያደርግባቸው (በስህተታቸው በማስረጃ መልስ ሊሰጥባቸው) አስቦ ካልሆነ በስተቀር ተንኮላቸውን አውቄያለሁ አልሸወድም ብሎ የትኛውም አካል ማድመጥም ሆነ የነሱን ፅሁፍ ማንበብ አይፈቀድለትም!! ትላልቅ እውቀት የነበራቸው ከቀደምቶችም በዚህ ዘመንም ስንቶች ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር ባላቸው መቀራረብና ማድመጥ የተቀየሩ አሉ። ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር በመቀራረብ ሰበብ ከተቀየሩ ቀደምት ሰው አንዱን ልጥቀስ…
የህ ኢብኑ መዒን (ረሂመሁላህ) የቡኻሪ ሸይኽ ናቸው እንዲህ አሉ:-
“ዳውድ ኢብኑ ሚህራን በሀዲስ የታወቀ ሀዲስን የሚፅፍ ሰው ነበር፣ ሀዲሱን ትቶ ከሙዕተዚላህ የሆኑ ሰዎችን ጓደኛ አድርጎ ያዘና አበላሹት።” [ተህዚቡል ከማል ፊ አስማኢ ሪጃል ገፅ 444 እና ተህዚብ አት-ተህዚብ ሊብኒ ሀጀር 3/174]
ታዲያ ኡሱል አስ-ሰላሳን እንኳን አስተካክሎ ያልቀራ ምስኪን በምን አቅሙ ነው የጥመት ባለ ቤቶችን ብዥታ እችላለሁ ብሎ ከስርስራቸው የሚልከሰከሰው?!፣ ታላላቅ የዲን መሪዎች እኮ ናቸው የቢድዐህ ባለ ቤቶችን ብዥታ በመፍራት በሩቁ ይጠነቀቁ የነበረው። የዲን ተማሪ የሆነ ሰው የአህሉሱንና መሻይኾችን ት/ት እየቀሰመ በመተግበር በተቻለው አቅም ሁሉ ለሌሎችም እንዲደርስ ሊያሰራጭ ይገባል እንጂ ማህበራዊ ሚዲያ ቀረበኝ ቀለለኝ ብሎ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በአካል ከስርስራቸው ሊልከሰከስ አይገባም!!
የቢድዐህ ባለ ቤቶችን ድምፅ መስማትም ሆነ ፅሁፍ ማንበብ ሀራም እንደሆነ እያወቀ ወደነሱ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚልከሰከስ ሰው በሰለፊይነቱ ሊጠነክርም ሆነ ሊፀና አይችልም።
ደጋግ ቀደምቶቻችን በቢድዓ ሰዎች ላይ የሚከተለው አይነት አቋም ነው የነበራቸው፣ እውነት ከልብ እነሱን እንከተላለን ካልን በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ ይህ የሠለፎች አቋም ሊኖረን ይገባል!!
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ስለ ቀደሪዮች መከሰትና በቀደር ላይ ያላቸው የተዛባ የፈጠራ አመለካከታቸው ሲነገረው እንዲህ አለ:-
“…እነዚህን ሰዎች ካገኘሃቸው ንገራቸው:- እኔ ከነሱ የጠራሁኝ ነኝ፣ እነሱም ከኔ የጠሩ ናቸው። በዚያ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር በሚምልበት ጌታ (በአላህ) ይሁንብኝ እነዚህ ሰዎች የእሁድን ተራራ ያህል ወርቅ ቢኖራቸውና ሶደቃ ቢያደርጉት በቀደር እስኪያምኑ አላህ አይቀበላቸውም።” [ሙስሊም፣ ነሳኢይ፣ አቢዳውና ትርሚዚይ ዘግበውታል]
በይሀቂይ (ረሂመሁላህ) ስለ ኢማሙ ሻፊዒይ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ:-
“ኢማሙ ሻፊዒይ (ረሂመሁላህ) በአፈንጋጮችና በቢድዓ ሰዎች ላይ ጠንካራ ነበሩ፣ በነርሱም ላይ ያላቸውን ጥላቻቸውንና ኩርፊያቸውን ግልፅ ያወጡት ነበር።" [መናቂቡ ሻፊዒይ ጥራዝ 1/469]
ኢማሙ አህመድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“አንድ ሰው በሙብተዲዕ ላይ ሰላምታን ካቀረበ እሱ ያንን የቢድዐ ሰው ይወደዋል ማለት ነው።" [ጦበቃቱል ሀናቢላ ጥራዝ 1/196]
ይህ የኢማሙ አህመድ ንግግር የቢድዐ ሰዎችን መውደድ እንደማይፈቀድና ጭራሹኑ እነሱን መዝጋት ተገቢ እንደሆነ አመላካች ነው።
ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይሉ ነበር:-
“አላህ ሆይ! እኔ ዘንድ ለቢድዐህ ባለቤት ውለታን አታድርግለት፣ (ውለታ ካለብኝ) ልቤ ይወደዋልና።" [ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሉሱንነቲ ወልጀማዐህ ጥራዝ 1/140]
የቢድዐ ሰው ውለታ ያለበት እውነታውን ቢያውቀውም መናገር ይከብደዋል። ይህ ደግሞ አላህ ይጠብቀንና በተጨባጭ የታየ ነገር ነው። ብዙዎችን ገደል የከተተውም ይሄው ነው።
ፉደይል ኢብን ዒያድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“የቢድዐ ባለቤቶችን የወደደ ሰው አላህ ስራውን አበላሽቶበታል፣ የእስልምናን ብርሃንም ከልቡ አውጥቶበታል።"
[ሸርሁ ሱንነህ ሊልበርበሃሪይ 138–139 አል ኢባነህ ሊብኒ በጣህ ጥራዝ 2/460]
ልብ በሉ የቢድዐህ ባለ ቤትን መውድ ያለው አደጋ!!
ዐብዱላህ ኢብኑ ዳውድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“ከሀቅ ምልክቶች ሀይማኖትን በስሜት የሚይዝን ሰው መጥላት ነው። ሀቅን የወደደ ሰው በእርግጥም የስሜት ባለቤቶችን (የቢድዓ ሰዎችን) መጥላት ግዴታ ሆኖበታል።"
[ሲየር አስሰለፍ አስሷሊሂን ሊተይሚይ ጥራዝ 3/1154]
ሙሀመድ ኢብኑ ሲሪን (ረሂመሁላህ) ዘንድ ሁለት የስሜት ባለ ቤት የሆኑ ሰዎች ገቡና እንዲህ አሉት:-
“አንተ የበክር አባት ሆይ! አንድ ሀዲስ እንንገርህ? አሉት፣ በጭራሽ አይሆንም፣ አላቸው፣ አንድ የቁርኣን አንቀፅ እንኳን እንቅራልህ? አሉት፣ በጭራሽ አይሆንም!፣ አላቸውና ትነሳላችሁ አለያ እኔ ተነስቼ እወጣላችኋለሁ፣ አለ፣ ተነስተው ወጡ። ከወጡ በኋላ ከአጠገቡ የነበሩ ሌሎች ሰዎች፣ የበክር አባት ሆይ! ቁርኣን ቢያነቡልህ ምንችግር አለው? ብለው ጠየቁት፣ እንዲህ በማለት ድንቅ መልስ መለሰ:- የቁርኣኑን አንቀፅ አንብበውት ያለ ትርጉሙ አዛብተው ተርጉመውት በልቤ እንዳይቀር ፈርቼ ነው።” [ሲየር አዕላም አንኑበላእ ሊዘሀቢይ ጥራዝ 11/285]
ይህ ታላቅ የኢስላም ሊቅ በዚህ መልኩ ከፈራ አንተ ማን ነህ እንደ ዝምብ ሁሉም ላይ ዘለህ ጥልቅ የምትለው?!፣
የጣውስ ልጅ (ረሂመሁላህ) አንድ የቢድዐህ ባለ ቤት የሆነ ሰው እያናገረው ለልጁ እንዲህ አለው:-
“ልጄ ሆይ የሚናገረውን እስከማትሰማ ድረስ ጣቶችህን ጆሮህ ውስጥ ክተታቸው፣ ከዚያም ቀጠል አደረገና በደንብ ጠንከር አድርገህ አስገባ አጠንክር። አለው” [አላለካኢይ እና ሲየር አዕላም አንኑበላእ]
በዚህን ጊዜ ሰለፊይነት ስም ብቻ እስኪመስል ድረስ አንዳንድ ወንድምና እህቶች ዘንድ ከቢድዐህ ሰዎች ጋር ሊኖር የሚገባው ጠንካራ የሰለፎች አቋም ወርዷል። የሰለፎቻችን በቢድዐህ ሰዎች ላይ የነበራቸው ጠንካራ አቋም ኪታብ ላይ ይቀራል ተግባር ላይ ግን አደጋ ላይ ነው። በተለይ ብዙ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ፕሮፋይል ላይ ሰለፊነትን ለማንፀባረቅ ማሻአላህ ናቸው፣ በተግባር ግን ከሙመይዓና ከኢኽዋን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስሮች ስር ሲልከሰከሱ ይስተዋላሉ፣ አላህ ይጠብቀንና የሆነ ኮሽታ ሲፈጠር ወደዚያው ለመጠቃለል ቅርብ ናቸው፣ ከዚህ ተግባር ልንቆጠብና ከቢድዐህ ባለ ቤቶች የተኛውንም መልእክታቸውን ከሚያብራሩባቸው የማህበራዊ ሚዲያም ሆነ ሌሎች መድረኮች መራቅና መጠንቀቅ ግዴታ ነው። ሙመይዓዎች ወርደው ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር የተደመሩበት አንዱ አደጋ ይህ ነበር። ሰለፊይ ነን ካልን በአቋማችን የፀናን ልንሆን ይገባል!! የሰለፎችን አቋም በሁለመናችን ተግባራዊ ልናደርግ ግድ ይለናል!! አላህ በሐቅ ላይ ያፅናን!!
በአላህ ፈቃድ በሌላ ርእስ እመለሳለሁ…
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa