እህቶቼ ሆይ! ኑ! ለሒጃባችሁ ተምሳሌት የምትሆናችሁን አንዲት የጀነት ሴት ላስተዋውቃችሁ!!
—————
ከዐጣእ ኢብን አቢ ረባህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ እንዲህ አለ:- ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለኝ:- ከጀነት ባለቤቶች የሆነችን ሴት አላሳይህን?!፣ እንዴታ (አሳይኝ እንጂ) አልኩት፣ ይህች ጥቁር ሴት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጥታ እንዲህ አለች:- «እኔ የአዙሪት በሽታ ይጥለኛል (እወድቃለሁ) ፣ ይህን ጊዜም ከሒጃቤ እገላለጣለሁ፣ አላህን ለምንልኝ፣ አለቾት፣ "ከፈለግሽ ታገሺ ጀነት አለሽ፣ ከፈለግሽም አላህን ጤነኛ እንዲያደርግሽ እለምንልሻለሁ" አሉዋት፣ እርሷም እታገሳለሁ አለች። ግን በምወድቅበት ጊዜ እገላለጣለሁና እንዳልገላለጥ ዱዓ አድርግልኝ፣ አለቻቸው። እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።» [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
ስንቶች ናቸው በዚህን ጊዜ በተልካሻ ምክንያት ሒጃባቸውን አውልቀው የሚጥሉት?! ስንቶች አሉ በማይረባ ምክንያት ትክክለኛውን ሒጃብ ከመልበስ ወደ ኋላ የቀሩ?!።
አስተውሉ! እሷን ያስጨነቃት ወደ ጌታዋ የሚያቃርባት፣ በህይወቷ ከመቀበር ለመዳን ሰበብ የሆናትን ነቢይ ትእዛዝ የምታከብርበትና ሀይማኖታዊ ግዴታዋ የሆነው የሒጃቧ መገላለጥ ነው እንጂ በአዙሪት መውደቋ አይደለም።
ሒጃብሽን በስርኣት ለባሽ የሆንሺው እህቴ ሆይ! በሒጃብሽ ምክንያት የተለያዩ ፈተናዎች ቢደርሱብሽ እንኳ ይህችን ድንቅ የጀነት ሴት ተምሳሌት አድርገሽ ከሚደርስብሽ ችግርና መከራ ታግሰሽ ሒጃብሽ ላይ ፅኚ!! በአላህ ፈቃድ ዐቂዳሽም ሰሊም ከሆነ ጀነት አለሽ።
በአውሮፓዎች ፋሺን ተታለው፣ በስሜት አዙሪት ታውረው፣ ትክክለኛውን ኢስላማዊ ሒጃብ የማይለብሱ (እርቃናቸውን የሚሄዱ) ሴቶችም ወደራሳቸው መለስ ብለው በማሰብ ይህችን የጀነት ሙሽራ የሆነችዋን ድንቅ እንስት ሁኔታ ሊያጤኑና "ኢስላማዊ ሒጃብ ምን አይነት ነው?!" ብለው ከቁርኣንና ከሀዲስ በትክክለኛ ማስረጃ አውቀው ተቀብለው፣ ተገስፀው ሊለብሱ ይገባል!።
እህቴ ሆይ! ሒጃብ ወደ ጀነት ለመግባት ሰበብ የሚሆንሽ፣ ከጀሀነም እሳት ለመከላከል ሰበብ የሚሆንሽና እንደ ፌስታል ተጠቅመውብሽ መጣል ከሚፈልጉ ዋልጌ ወንዶች ትንኮሳ ግርዶሽ የሚሆንሽ ፋሽን የማይጥለው ሀይማኖታዊ ልብስሽ እንጂ እንደ ጊዜው የሚቀያየር ፋሽን አይደለም!!
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa