መንሀጀ-ሠለፍን እንዴት ተረዳሀው/ሽው?!
…… …… መንሀጀ-ሰለፍን በትክክል እንገንዘብ!!
🔹 መንሀጀ-ሠለፍን በትክክል ከተረዳን የሁሉንም ነገር ልክና ድንበር እናውቀዋለን።
መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን) እና ባልደረቦቻቸውን ጨምሮ እነሱንም በትክክል የተከተሉ የደጋግ ቀደምቶች መንገድ ማለት ነው።
መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- አንዳንዶች እንደሚያስቡት ልክ እንደ ሌሎች የጥመት አንጃዎች ራሱን የቻለ አንጃ ሳይሆን ትክክለኛ (ንፁህ) ያልተበረዘው እስልምና ማለት ነው። ትክክለኛውና (ንፁህ) እስልምና ማለት ደጋግ ቀደምቶች ባመኑበት መልኩ ማመን ነው!።
አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-
فَإِنْ آمَنُوا بِمِثْلِ مَا آمَنتُم بِهِ فَقَدِ اهْتَدَوا ۖ وَّإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا هُمْ فِي شِقَاقٍ ۖ فَسَيَكْفِيكَهُمُ اللَّهُ ۚ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
«በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ፡፡ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱንም አላህ ይበቃሃል፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡» አል_በቀረህ 137
ትክክለኛ ሠለፊይ ማለት ደግሞ:- እነዚሁ ደጋግ ቀደምቶች ባመኑበት መልኩ አምኖ በአካሄድም ሆነ በአኽላቅ፣ ከከሀዲዎችና ከጥመት አንጃዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነትም ሆነ በሌላ ደጋግ ቀደምቶችን በመልካም ሁኔታ ተከትሎ መጓዝ ማለት ነው።
ሠለፊይነት ማለት:- የመልካም ቀደምቶችን መንገድ ለራስህ ዝንባሌ በሚመችህ መልኩ ሳታሰናዳው አጥብቀህ በመልካም ሁኔታ መከተል ነው።
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል:-
وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ
«ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡» አል_ተውበህ 100
መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- የፖለቲካው ሁኔታ ሲቀያየር የምትቀያይረው ማለት አይደለም!!
መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- የአንድ ሰሞን የግርግር አቋም አይደለም!!።
መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- በዱኒያዊ ጉዳይ ከተወሰኑ የጥመት አንጃዎች (የቢድዐ) ሰዎች ጋር ስትገናኝ ለዱኒያዊ ጥቅም አልያም አንዳች ለዲን ይጠቅማል ብለህ ምታስበው ነገር እንዳይቀርብህ ብለህ በማላላትም ይሁን በማጥበቅ የምትቀያይረው አቋም ሳይሆን የትም ሆነህ በየትኛውም ሁኔታህ እስከ እለተ ሞትህ አጥብቀህ የምትይዘው የማይቀያየር የደጋግ ቀደምቶች መንገድ ነው።
መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ከሆኑ ግለሰቦች ጋር በዱኒያዊ ጥቅምም ይሁን በስነ-ምግባር ስላልተጣጣምክ ለመወነጃጀል ያህል የምትጠቀምበት አይደለም!!
መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ቢደላህም ቢቸግርህ፣ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር በዱኒያዊ ጥቅማ ጥቅምም ሆነ በሌላ ብትጋጭም ሆነ ብትዋደድ፣ እስከ እለተ ሞትህ በክራንቻ ጥርስህ አጥብቀህ የምትይዘው የደጋግ ቀደምቶች መንገድ የሆነው ንፁህ እስልምና ነው!!
መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ሞቅ ሲልህ ምታወልቀው ሲበርድህ አንስተህ የምትለብሰው ጃኬት አይደለም!! ይልቅ ሞቅታህም መቀዝቀዝህም ትክክል ይሁን አይሁን የምትለካበት ትክክለኛው መነፅር ነው።
ስትቀዘቅዝ ለምን ቀዘቀዝኩ? ብለህ እንደ ሸሪዓ ራስህን የምትገመግምበት መንገድ ነው።
ሞቅ ሲልህ ደግሞ ይህ እንደ ሸሪዓ (እንደ ቀደምቶች አቋም) ተገቢ ነው አይደለም? ብለህ ራስህን ፈትሸህ ምታስተካክልበት ምንጊዜም ሊለይህ የማይገባ የደጋግ ቀደምቶች መንገድ እንጂ ሞቀኝ ብለህ አውጥተህ የምታስቀምጠው ልብስ አይደለም!!
ሠለፊይ (ሱኒይ) የሆነ ሰው የማይሳሳት ፍፁም አይደለም!!።
አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ:- “ሰለፊይ ነው ብዬ ፂሙን አስረዝሞ፣ ሱሪውን አሳጥሮ፣ እንዲህ ሲያደርግ አይቼ ሰለፊይነት አስጠላኝ… ኒቃቧን ለብሳ እንዲህ አድርጋ እንዲህ ስትል… ደግሞ በዛ ላይ ቀሪኣ ነች (የቀራች ናት) ከዛ በኋላ አስጠሉኝ…” ወዘተ ይላሉ።
ሆነ ብለውም ይሁን አይሁን እንዲህ መሰል ፀያፍ ቃላቶችን በሰለፊይ ወንድምና እህቶች ላይ ከምላሳቸው የሚያወጡ ሰዎች አሉ።
እንዲህ የሚሉ ሰዎች ሶስት ነገሮችን ዘንግተዋል:-
1ኛ, ዲናችን የሚለካው በቁርኣንና በሀዲስ እንጂ በሰዎች እንዳልሆነ ዘንግተዋል።
2ኛ, እነዚህ ኢስላማዊ ምልክት የሚታይባቸውን ሰዎች ሰው መሆናቸውን ዘንግተው ልክ ምንም የማይስቱ እንደ መላኢካ (ፍፁም) አድርጎ መሳል አለ።
3ኛ, አንዳንዴም እነዚህ ሰዎች ጥፋት ነው ብለው የሚያስቡት ነገር በሆነ ባህል ተፅእኖ ወድቀው ስህተት መስሎ የታያቸው ነገር ግን ደግሞ እንደ ሸሪዓ ችግር የሌለው ነገር በመሆኑ ሌሎች ቀለል አድርገው ተግብረውት ይሆናል።
የሆነው ሆኖ ብቻ ግን አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ሰለፊይ የሆነ ሰው ፍፁም አይደለም!! ይሳሳታል ከስህተቱ ግን ቶሎ ይመለሳል። እንዲሁም መንሀጀ ሰለፍ በሰዎች ሳይሆን የሚለካው ሰዎች ናቸው በመንሀጀ ሰለፍ የሚለኩት!!
ፈተናዎች በሚደራረቡበት ጊዜ እና የጥመት አንጃዎች ማእበል በሚበረታበት ወቅት እውቀት ያለው እንኳን ከመንሀጀ ሰለፍ ሲንገዳገድ ካየህ በጭላንጭል እውቀት መንሀጀ ሰለፍን የያዙ ሰዎች እንዴት ይሆኑ ይሆን?! ብለህ እንድታስብ ያደርግሃል።
መንሀጀ ሠለፍን በትክክለኛ እውቀትና በትክክለኛ ማስረጃ በሚገባ ተገንዝቦ መያዝ ግዴታ ነው!!
አለያ ግን ልክ ባህሩ በማእበል ሲናወጥ የጀልባዎች ሁኔታ እንደሚያሳስበው ሁሉ፣ በትክክለኛ እውቀት መንሀጀ ሰለፍን አጥብቀው ያልያዙ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ ነው!!
ሳጠቃልል ሠለፊነት ማለት:- ቁርኣን እና ሐዲስን በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መገንዘብ ማለት ነው። እንዲሁም ደጋግ ቀደምቶች በተጓዙበት መጓዝና በቆሙበት መቆም ነው።
✍🏻ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa