እህቴ ሆይ! እምነትሽ ያዘዘሽን ሒጃብ በአግባቡ ለብሰሽ አክብሪው
———
ሒጃብን ሸሪዓው በሚያዘው መልኩ ዘውትር ለብሶ ማክበር ነው እንጂ የሒጃብ ቀን የሚባል የተለየ ቀን የለውም!!
"
ሒጃብ ማለት እስልምና በሴት ልጅ ግዴታ ያደረገባት ሙሉ አካሏን የምትሸፍንበት ሰፊ ልብስ እንጂ በአመት አንዴ አናቷ ላይ ብጣሽ ሻሽ ጠምጥማ ቀን ለይታ የምታከብረው ነገር አይደለም!!
"
ሒጃብ ማለት ሴት ልጅ እዚህች አለም ላይ ከተለያዩ ባለጌዎች ሙሉ አካሏን የምትሸፍንበትና የተለያዩ ጨዋ ወንዶች ደግሞ እርቃኗ በመሄዷ እንዳይፈተኑ የምታደርግበት ከፈጣሪዋ አላህ ዘንድ የታዘዘችው በህይወት ዘመኗ ሁሉ የማትለየው ልብስ ነው።
"
ሒጃብ ማለት ሸይጧን እና የእስልምና ጠላቶች እንደሚፈልጉት የምትለብሰው ልብስ ሳይሆን የፈጠራት ፈጣሪዋ እንዳዘዛት ዘውትር የምትለብሰው ወደ ፈጣሪዋም የምትቃረብበት የፅድቅ ልብስ ነው።
"
ሒጃብሽን ዘውትር ሸሪዓው በሚፈልገው መልኩ በመልበስ አክብሪው!! የባለጌዎችና የጅሎች መዝናኛ የዐይን ማረፊያ አትሁኚ።
"
ሒጃብ ማለት ፈጣሪሽ እንድትለብሺው ከእናቶችሽ ከነ ዓኢሻ፣ ከነ ኸዲጃ፣ እንዲሁም ከታላቁ ነቢይ ልጅ ከነ ፋጢማ (ረዲየላሁ ዐንሁም) እኩል እንዲህ በማለት ያዘዘሽ የፈጣሪ ትእዛዝ ነው:-
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ
«አንተ ነቢይ ሆይ! ለሚስቶችህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው፡፡» አል-አህዛብ 59
የአላህን ንግግር ልብ በይ! እህቴ:- «ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው፡፡» አለ፣ አንቺ ጨዋ ሴት ከሆንሽና በባለጌዎች እንዳትደፈሪ፣ እንዳትለከፊ ከፈለግሽ በስርኣት አላህ ባዘዘሽ መልኩ መልበስ ነው፣ በተቃራኒው ደግሞ ሸሪዓው ከሚፈልገው የሒጃብ አይነት ውጪ ከሆንሽ ራስሽን ለባለጌዎችና ለብልግና እያመቻቸሽ ነው ማለት ነው።
🔸የኢስላም ጠላቶች ይህን ጠንቅቀው ያውቁታል። ለዚያም ነው ሙስሊም ሴቶችን ለባለጌ ወንዶች አጋልጠው ለመስጠት በየ ተቋሙና አቅማቸው በቻለው ሁሉ በት/ት ተቋማትና በመንግስት ተቋማት የሙስሊም ሴቶችን ስርኣት ያለው እምነታቸው የሚያዛቸውን አይነት ሒጃብ እንዳይለብሱ የሚጥሩት። ሙስሊም እህቴን ሒጃቧን ካስወለቋት ለዲኗ ግዴለሽ እንድትሆን ያደርጓታል፣ ምን ይህ ብቻ በመስተፋቅርና በተለያየ መንገድ እምነቷንም የሚያስቀይሯትን ተኩላ ከሀዲ ወንዶችን ይልኩባታል።
"
ሒጃብሽን አላህ ባዘዘሽ መልኩ ከለበሺው ነገ በአኼራ ሰውነትሽ እሳት እንዳይነካውም ይከላከልልሻል። ሒጃብሽ እምነትሽ ነው፣ ሒጃብሽ ስብእናሽ ነው፣ ሒጃብሽ ማንነትሽ ነው!! ሒጃብሽን አውልቀሽ ት/ት የለም!፣ ማንነትሽን ክብርሽን ሽጠሽ ዱኒያዊ ጥቅም ጥንቅር ብሎ ይቅር እንጂ በሒጃብሽ ተደራደርሽ ማለት በእምነትሽ መደራደር እንደሆነ ጠንቅቀሽ እወቂው!! ጥላቻቸው ከእምነትሽ እንጂ ከጨርቁ አይደለም!!።
"
የሒጃብ ቀን ምናም እያሉ ሚያጃጅሉሽን ትተሽ ፈጣሪሽ ከሰባት ሰማይ በላይ ያዘዘሽን ትእዛዝ አክብረሽ ዘውትር አላህ በሚፈልገው መልኩ ሒጃብሽን ጠብቂ!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa