ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ
=
1- ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ (الطلاق المعلق) ማለት ለምሳሌ ሚስቱ ከሆነች ጓደኛዋ ዘንድ መሄዷ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ ተረዳ። "አትሂጂ" ቢላት ልትቆም ፈቃደኛ አልሆነችም። በዚህን ጊዜ "ዳግመኛ እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" በማለት ተናገረ። ይህንን ካለ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ወርዶ ፍቺው ይቆጠራልን?
=> ይህንን ሸርጥ የተናገረው ብትሄድ የእውነትም ሊፈታት ከሆነ በመሄዷ ኒካሑ ይወርዳል። ፍቺ ተፈፅሟል።
=> ሸርጡን ያስቀመጠው መፍታትን አስቦ ሳይሆን ለማስፈራራት ከሆነ ኒካሑ አይወርድም።
2- ያስቀመጠው ቅድመ-ሁኔታ ቀድሞ በተፈፀመ ጉዳይ ላይ ይሰራልን? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀመጠ። ይህን ከማለቱ በፊት ቀድማ ሄዳ ከሆነ ፍቺው ይቆጠራልን?
=> ቅድመ ሁኔታውን ሲያስቀምጥ ሃሳቡ ቀድማ ሄዳም ከሆነ "ፈትቻለሁ" የግል እሳቤን የሚያጠቃልል ከሆነ ፍቺው ይቆጠራል። ከዚህ በኋላ ቢከሰት የሚለውን ብቻ ነይቶ ካወራ ግን በቀደመ ተግባር ፍቺ አይታሰብም።
3- "ይህንን ካደረግሽ ፍቺ ነሽ" ቢልና አውቃ ሳይሆን ረስታው ያንን ነገር ብትፈፅም ኒካሑ ይወርዳልን?
=>አይወርድም።
4- ካስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መመለስ ይችላል? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀምጦ ነበር። ያስቀመጠውን ሸርጥ አንስቶ ቢፈቅድላትና ከዚያ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ይወርዳል?
=>ትክክለኛው አቋም አይወርድም የሚለው ነው።
5- ሚስቱን በሆነ ሰበብ ከፈታ በኋላ ሰበቡ ልክ እንዳልሆነ ካወቀስ? ለምሳሌ፦ ሚስቱ በሆነ ጉዳይ ላይ እንደዋሸችው ወይም ከቤቱ ወንድ እንዳስገባች ተረድቶ ፈታ። ሲያጣራ ግን ጉዳዩ እሱ እንዳሰበው እንዳልሆነ አወቀ። ኒካሑ ይወርዳል ወይ?
=>ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑ ባዝ እና ኢብኑ ዑሠይሚን ኒካሑ አይወርድም ብለዋል።
=
ከሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ፈትሑል ዐላም ኪታብ (8/543 - 554) ተጨምቆ የቀረበ
=
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor