ዳዕዋ ሠለፍያ በኢቅራ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ማስረጃ በዞረበት እንዞራለን ! ለአንድም አካል ወገንተኛ ፤ጠርዘኛ አንሆንም ፈፅሞ!!!
Comment and Suggestion
👇👇👇👇👇
ይህ የቴሌግራም" ቻናል"የሚ•ቴ•ዩ የሚዛን ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎችን ያማከለ ሲሆን በውስጡም ኢስላማዊ ትምህርቶች፣ ሙሀደራዎች፣ፈትዋዎች፣መጣጥፎችና መሰል ጥቅም አዘል ፓምፕሌቶች ይለቀቁበታል።
ኢንሻኣላህ በመልቀቁላይ
ابو القاسم

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🚫::::::ለዉዱ ወንድሜ መልክት:::::🚫

ሱብሃን አላህ 📌☞የሴት ፈተና ኢስላምክን እንዲህ ሊያስጥልክ ይችላልና ተጠንቀቅ❗️
ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻣﻦ ﺍﻋﻈﻢ ﺍﻷﺳﺒﺎﺏ ﺍﻟﺘﻲ ﺗﻨﻘﺺ ﺍﻳﻤﺎﻥ ﺍﻟﺮﺟﻞ
በሚስር(ግብፅ) ከተማ ውስጥ መስጂድን በአዛን
በሰላት አጥብቆ የሚይዝ አንድ
ሰው (ሙዓዚን) ነበር። በርሱም ላይ ጥሩ
መታዘዝ እና የኢባዳህ ብርሃኖች
ይታዩበት ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀን አዛን ሊያደርግ ወደ መናራህ ወጣ፡ ታዲያ አዛን ላይ ሆኖ
ከመስጂዱ ስር ወዳሉ ነስራኒዮች ቤት አይኑን ሲልክ ድንገት ከአንዱ ቤት ውስጥ
አንዲትን እንስት ይመለከታል ከመቅፅበት
በውበቷ ተመርኮ ፈተና ላይ ይወድቃል ፡
በፍጥነትም እርሷ ወዳለችበት ቤት ይሄድና ዘው ብሎ ይገባል ልጅቱም ምን ፈልጎ እንደመጣ ትጠይቀዋለች

🚫☞እርሱም፡- እንዲህ ሲል መለሰላት አንቺን ነው የምፈልገው

📌☞እርሷም ፡- ለምንድን ነው እኔን የፈለከኝ?"ብላ ጠየቀችው

🚫☞እርሱም፡- ልቤ ባንቺ ተፈትኗል የልቤን
መሰባሰቢያ ይዘሺዋል አላት

📌☞እርሷም፡- ያለምንም ጥርጥር መቼም እሺ ልልህ አልችም አለቸው

🚫☞እርሱም፡- እንግዲያውስ አገባሻለሁ" አላት

📌☞እርሷም ፡- አንተ ሙስሊም ነህ እኔ ነስራኒይያህ (ክርስቲያን) ነኝ አባቴ ደግሞ እንዲህ ሆነህ አንተን አይድረኝም አለችው"

🚫☞እርሱም፡- "ግዴለም እኔ ላንቺ ስል ነሳራ (ክርስቲያን) እሆናለሁ አላት፡

📌☞እርሷም ፡-እንደዛ ያደረግክ እነደሆን
(ክርስቲያን ከሆንክ) እኔም ፍቃደኛ ነኝ
(አገባሀለሁ)

ከዚያም ይሄ ሰው እርሷን ለማግባት ሲል ነሳራ (ክርስቲያን) ሆነና ከነርሱ ጋር ቤት
ተቀመጠ ታዲያ በዚያኑ እርሷን ጠይቆ ባገባበት የሰርጉ ዕለት ቤቱ ውስጥ ወዳለ ከፍ ወዳለ ቆጥ ሲወጣ ወደቆ
ወዲያኑ # ህይወቱ_አለፈች ፡:
እርሷንም ሳያገኝ እስልምናውን አጥቶ በኩፍር ላይ ሞተ ።
(አል፡ዳኡ ወ’ደዋአ ሊኢብኑ አል፡ቀይም ገፅ 167)
ሰዓይድ ኢብኑ ሙሰየብ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ይል ነበር፡
(መውሱዓቱ ኢብኑ አቢ ዱንያ ቅጽ 4 ገፅ 540)
አል-ሀሰን ኢብኑ ሳሊህ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ሲል ይናገራል፡
✍(መውሱዓቱ ኢቡኑ አቢ ዱንያ ቅፅ 4 ገፅ 539)
ለወንድ ልጅ ከባዱ ፈተና
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል
ለወንዶች ከሴቶች ይበልጥ ጎጂ ፈተና በኋላዬ አልተውኩም
✍(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል✅

#ወንድሜ_ከእንድህ_አይነት_ፊቲና_አላህ_ይጠብቅህ ።
ከወደዳቹት #ሼር_አድርጉ_ሸር_የለበትም_እና

💍::::::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::::💍

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam


السلام عليكم ورحمت الله وبركاته

عيد مبارك! !ዒድ ሙባረክ

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال


1220- وعنه رضي الله عنه أنَّ رسول الله صلى الله عليه وسلم قَالَ: ((إِذَا جَاءَ رَمَضَانُ، فُتِحَتْ أَبْوَابُ الجَنَّةِ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ النَّارِ، وَصُفِّدَتِ الشَّيَاطِينُ)). متفقٌ عَلَيْهِ.
في رواية للنسائي: ((وتغل فيه مردة الشياطين)).
قال القرطبي: فإن قيل: كيف ترى الشرور والمعاصي واقعة في رمضان كثيرًا؟ فالجواب: أنها إنما تغل عن الصائمين الصوم الذي حوفظ على شروطه، وروعيت آدابه، أو المصفَّد بعض الشياطين وهم المردة لا كلهم، والمقصود تقليل الشرور فيه. وهذا أمر محسوس فإن وقوع ذلك فيه أقل من غيره إذ لا يلزم من تصفيد جميعهم أن لا يقع شر ولا معصية؛ لأن لذلك أسبابًا غير الشياطين، كالنفوس الخبيثة، والعادات القبيحة، والشياطين الإنسية.


1221- وعنه: أنَّ رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: ((صُومُوا لِرُؤْيَتِهِ، وَأفْطِرُوا لِرُؤيَتِهِ، فَإنْ غَبِيَ عَلَيْكُمْ، فَأكمِلُوا عِدَّةَ شَعْبَانَ ثَلاَثِينَ)). متفقٌ عَلَيْهِ، وهذا لفظ البخاري.
وفي رواية مسلم: ((فَإنْ غُمَّ عَلَيْكُمْ فَصُومُوا ثَلاَثِينَ يَوْمًا)).
في هذا الحديث: دليل على أنه لا يجب صوم رمضان إلا برؤية هلاله، أو إكمال عدة شعبان ثلاثين يومًا.
واختلفت الروايات عن الإمام أحمد فيما إذا حال دون منظر الهلال غيمٌ أو قتر، فعنه: يجب صومه، وعنه: أن الناس تبع للإمام، وعنه: لا يجب صومه قبل رؤية هلاله، أو إكمال شعبان.
واختاره شيخ الإسلام ابن تيمية، وقال: هو مذهب أحمد المنصوص الصريح عنه. وعنه: صومه منهي عنه، وهذا الموافق للأحاديث الصحيحة الصريحة.
وقال البخاري: باب قول النبي صلى الله عليه وسلم: ((إذا رأيتم الهلال فصوموا، وإذا رأيتموه فأفطروا)). وقال صلى الله عليه وسلم: ((يا عمار، من صام يوم الشك فقد عصى أبا القاسم صلى الله عليه وسلم)).


باب وجوب صوم رمضان، وبيان فضل الصيام وَمَا يتعلق بِهِ:
قَالَ الله تَعَالَى: {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُم الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ} إِلَى قَوْله تَعَالَى: {شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنْزِلَ فِيهِ القُرْآنُ هُدَىً لِلنَّاسِ وَبَيّنَاتٍ مِنَ الهُدَى وَالفُرْقانِ فَمَنْ شَهِدَ مِنْكُم الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ وَمَنْ كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَى سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أيَّامٍ أُخَر}. [البقرة: 183، 185].
قوله: {كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ}، أي: فرض.
قوله: {وَعَلَى الَّذِينَ يُطِيقُونَهُ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ} [البقرة: 184]، كانوا مخيَّرين في أول الإسلام بين الصيام والإطعام، ثم نسخ بقوله: {فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ} [البقرة: 185].
وَأما الأحاديث فقد تقدمت في الباب الَّذِي قبله.
أي: الأحاديث الدالة على وجوب صوم رمضان، كقوله صلى الله عليه وسلم: ((بُني الإسلام على خمس...)) الحديث، وغيره.


1215- وعن أَبي هريرة رضي الله عنه قال: قَالَ رسول الله صلى الله عليه وسلم: ((قَالَ اللهُ- عز وجل: كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ لَهُ إِلا الصِّيَام، فَإنَّهُ لِي وَأنَا أَجْزِي بِهِ، وَالصِّيَامُ جُنَّةٌ، فَإذَا كَانَ يَومُ صَوْمِ أَحَدِكُمْ فَلا يَرْفُثْ وَلا يَصْخَبْ، فإنْ سَابَّهُ أحَدٌ أَوْ قَاتَلَهُ فَلْيَقُلْ: إنِّي صَائِمٌ. وَالذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ لَخُلُوفُ فَمِ الصَّائِمِ أطْيَبُ عِنْدَ اللهِ مِنْ رِيحِ المِسْكِ. لِلصَّائِمِ فَرْحَتَانِ يَفْرَحُهُمَا: إِذَا أفْطَرَ فَرِحَ بفطره، وَإذَا لَقِيَ رَبَّهُ فَرِحَ بِصَوْمِهِ)). متفقٌ عَلَيْهِ، وهذا لفظ روايةِ البُخَارِي.
وفي روايةٍ لَهُ: ((يَتْرُكُ طَعَامَهُ، وَشَرَابَهُ، وَشَهْوَتَهُ مِنْ أجْلِي، الصِّيَامُ لي وَأنَا أجْزِي بِهِ، وَالحَسَنَةُ بِعَشْرِ أمْثَالِهَا)).
وفي رواية لمسلم: ((كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ يضاعَفُ، الحسنةُ بِعَشْرِ أمْثَالِهَا إِلَى سَبْعِ مِائَةِ ضِعْفٍ. قَالَ الله تَعَالَى: إِلا الصَّوْمَ فَإنَّهُ لِي وَأنَا أجْزِي بِهِ؛ يَدَعُ شَهْوَتَهُ وَطَعَامَهُ مِنْ أجْلِي. للصَّائِمِ فَرْحَتَانِ: فَرْحَةٌ عِنْدَ فِطْرِهِ، وَفَرْحَةٌ عِنْدَ لِقَاءِ رَبِّهِ. وَلَخُلُوفُ فِيهِ أطْيَبُ عِنْدَ اللهِ مِنْ رِيحِ المِسْكِ)).
في هذا الحديث: فضل الصيام، وأن الله يجزي الصائم بغير حساب.
وفيه: شرف الصوم عند الله تعالى.
قوله: ((والصيام جنة))، أي: وقاية من النار.
قال ابن العربي: إنما كان جُنَّة من النار، لأنه إمساك عن الشهوات، والنَّار محفوفة بها.


1216- وعنه: أنَّ رسول الله صلى الله عليه وسلم قَالَ: ((مَنْ أنْفَقَ زَوْجَيْنِ في سَبِيلِ اللهِ نُودِيَ مِنْ أبْوَابِ الجَنَّةِ، يَا عَبْدَ اللهِ هَذَا خَيرٌ، فَمَنْ كَانَ مِنْ أهْلِ الصَّلاَةِ دُعِيَ مِنْ بَابِ الصَّلاَةِ، وَمَنْ كَانَ مِنْ أهْلِ الجِهَادِ دُعِيَ مِنْ بَابِ الجِهَادِ، وَمَنْ كَانَ مِنْ أهْلِ الصِّيَامِ دُعِيَ مِنْ بَابِ الرَّيَّانِ، وَمَنْ كَانَ مِنْ أهْلِ الصَّدَقَةِ دُعِيَ مِنْ بَابِ الصَّدَقَةِ)). قَالَ أَبُو بَكْرٍ رضي الله عنه: بِأبي أنْتَ وَأُمِّي يَا رسولَ اللهِ! مَا عَلَى مَنْ دُعِيَ مِنْ تِلْكَ الأَبْوَابِ مِنْ ضَرورةٍ، فهل يُدْعى أحَدٌ مِنْ تِلْكَ الأبوَابِ كُلِّهَا؟ فَقَالَ: ((نَعَمْ، وَأرْجُو أنْ تَكُونَ مِنْهُمْ)). متفقٌ عَلَيْهِ.
قوله: ((فمن كان من أهل الصلاة)) إلى آخره، أي: صلاة التطوع، وصيام التطوع، وصدقة التطوع.
وفي الحديث: منقبة عظيمة لأبي بكر رضي الله عنه.


1217- وعن سهل بن سعد رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قَالَ: ((إنَّ في الجَنَّةِ بَابًا يُقَالُ لَهُ: الرَّيَّانُ، يَدْخُلُ مِنْهُ الصَّائِمُونَ يَومَ القِيَامَةِ، لاَ يَدْخُلُ مِنْهُ أَحَدٌ غَيْرُهُمْ، يقال: أيْنَ الصَّائِمُونَ؟ فَيَقُومُونَ لا يَدخُلُ مِنْهُ أَحَدٌ غَيْرُهُمْ، فَإذَا دَخَلُوا أُغْلِقَ فَلَمْ يَدْخُلْ مِنْهُ أَحَدٌ)). متفقٌ عَلَيْهِ.
قوله: ((لا يدخل منه أحد غيرهم))، كرر نفي دخول غيرهم منه تأكيدًا.
زاد النسائي: ((من دخله لم يظمأ أبدًا)).


1218- وعن أَبي سعيد الخدري رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رسول الله صلى الله عليه وسلم: ((مَا مِنْ عَبْدٍ يَصُومُ يَوْمًا في سَبِيلِ اللهِ إِلاَّ بَاعَدَ اللهُ بِذَلِكَ اليَوْمِ وَجْهَهُ عَنِ النَّارِ سَبْعِينَ خَرِيفًا)). متفقٌ عَلَيْهِ.
قال ابن الجوزي: إذا أطلق ذكر سبيل الله فالمراد به الجهاد.
وقال القرطبي: ((سبيل الله))، طاعة الله، فالمراد من صام قاصدًا وجه الله.


1219- وعن أَبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قَالَ: ((مَنْ صَامَ رَمَضَانَ إيمَانًا وَاحْتِسَابًا، غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ)). متفقٌ عَلَيْهِ.
قوله: ((إيمانًا واحتسابًا))، أي: مصدقًا محتسبًا ثوابه عند الله تعالى.


«635» حدثنا أبو نعيم قال: حدثنا شيبان عن يحيى عن عبد الله بن أبي قتادة عن أبيه قال بينما نحن نصلي مع النبي صلى الله عليه وسلم إذ سمع جلبة رجال فلما صلى قال: ((ما شأنكم)). قالوا استعجلنا إلى الصلاة. قال: ((فلا تفعلوا، إذا أتيتم الصلاة فعليكم بالسكينة، فما أدركتم فصلوا وما فاتكم فأتموا)).
[تحفة 12111].


Репост из: ዳዕዋ ሰለፊያ በሚዛን ካምፓስ
«የሴት ልጅ መስተካከልና መበላሸት በባሏ ላይ ተፅእኖ ያሳድራሉ!!»

➡️ሀሰኑል በስሪይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:–

“መካ ውስጥ ልብስ ሻጭ የሆነ ሰው ዘንድ ከርሱ ልብስ ለመግዛት ቆምኩኝ፣ እየማለ ልብሱን ማወደስ ጀመረ፣ ከሱ መግዛቱን ተውኩት፣ ከእንደዚህ አይነት ሰው መግዛቱም ተገቢ አይደለም አልኩና ከሌላ ሰው ገዛሁኝ፣ ከዚያም ከሁለት አመት በኋላ (ወደዚያው) ጉብኝት አደረግኩ፣ እርሱ ዘንደም ቆምኩኝ እየማለም እያወደሰም ሆኖ አላገኘሁትም፣ ለሱም እንዲህ አልኩት:– ያ ከአመታት በፊት ያገኘውህ ሰው አይደለህምን? አዎ ነኝ አለ፣ ከዚህ በፊት ከነበርከበት ሁኔታ ወደ ምመለከትህ ሁኔታ ምን አወጣህ? እየማልከና እያወደሰክም ሆነህ አላይህም፣ አልኩት።

1⃣ለኔ አንዲት ሚስት ነበረችኝ፣ ትንሽ ነገር ይዤ ስገባ የምታመናጭቅና አሳንሳ የምታይ, ብዙ ይዤ ስገባ አሳንሳ ተየዋለች፣ ከዚያም አላህ አሞታት (ሞተች)።
2⃣ከሷ በኋላ ሌላ ሴት አገባሁ፣ ወደ ሱቅ መውጣት ስፈልግ ልብሴን ይዛ ከዚያም እገሌ ሆይ! አላህን ፍራ ጥሩ ነገር እንጂ አትመግበን፣ ትንሽ ብታመጣልን ብዙ አድርገን እንቆጥረዋለን/እናብዛዘዋለን፣ ምንም ይዘህ ባትመጣ እንኳን እናግዝሃለን፣ ትለኛለች።”
ምንጭ:– አል ሙጃለሰቱ ወጀዋሂር አል ዒልም 5/251📚

ጥያቄ ለእህቶቼ፣ ለመሆኑ እናንተ ከየትኛዋ ሴት ናችሁ ከመጀመሪያዋ ወይስ ከሁለተኛዋ???
መልሱን……… ለአላህ ብላችሁ ከልባችሁ ለራሳችሁ መልሱት!
ከመጀመሪያዋ የሆናችሁ አላህን (ተባረከወተዓላ) ፈርታችሁ ተፀፅታችሁ ወደ ሁለተኛዋ ተመለሱ!!
ከሁለተኛዋ የሆናችሁ ሸይጧን ድንበር እንዳያሳልፋችሁ ነፍሳችሁን ዝቅ እንድትልና ከጌታዋ ከጃይ እንድትሆን አድርጓት! አላህ ፅናት እንዲሰጣችሁም የዘውትር ዱዓችሁ ይሁን!! ምክንያቱም ይህ እጅግ በጣም ከባድ ነገር ነውና‼
ኢብን ሽፋ 9/8/1439 ዓ. ሂ
⇩⇩⇩
https://telegram.me/selefiya2mizancampas


ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ
=
1- ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ (الطلاق المعلق) ማለት ለምሳሌ ሚስቱ ከሆነች ጓደኛዋ ዘንድ መሄዷ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ ተረዳ። "አትሂጂ" ቢላት ልትቆም ፈቃደኛ አልሆነችም። በዚህን ጊዜ "ዳግመኛ እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" በማለት ተናገረ። ይህንን ካለ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ወርዶ ፍቺው ይቆጠራልን?
=> ይህንን ሸርጥ የተናገረው ብትሄድ የእውነትም ሊፈታት ከሆነ በመሄዷ ኒካሑ ይወርዳል። ፍቺ ተፈፅሟል።
=> ሸርጡን ያስቀመጠው መፍታትን አስቦ ሳይሆን ለማስፈራራት ከሆነ ኒካሑ አይወርድም።

2- ያስቀመጠው ቅድመ-ሁኔታ ቀድሞ በተፈፀመ ጉዳይ ላይ ይሰራልን? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀመጠ። ይህን ከማለቱ በፊት ቀድማ ሄዳ ከሆነ ፍቺው ይቆጠራልን?

=> ቅድመ ሁኔታውን ሲያስቀምጥ ሃሳቡ ቀድማ ሄዳም ከሆነ "ፈትቻለሁ" የግል እሳቤን የሚያጠቃልል ከሆነ ፍቺው ይቆጠራል። ከዚህ በኋላ ቢከሰት የሚለውን ብቻ ነይቶ ካወራ ግን በቀደመ ተግባር ፍቺ አይታሰብም።

3- "ይህንን ካደረግሽ ፍቺ ነሽ" ቢልና አውቃ ሳይሆን ረስታው ያንን ነገር ብትፈፅም ኒካሑ ይወርዳልን?
=>አይወርድም።

4- ካስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መመለስ ይችላል? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀምጦ ነበር። ያስቀመጠውን ሸርጥ አንስቶ ቢፈቅድላትና ከዚያ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ይወርዳል?
=>ትክክለኛው አቋም አይወርድም የሚለው ነው።

5- ሚስቱን በሆነ ሰበብ ከፈታ በኋላ ሰበቡ ልክ እንዳልሆነ ካወቀስ? ለምሳሌ፦ ሚስቱ በሆነ ጉዳይ ላይ እንደዋሸችው ወይም ከቤቱ ወንድ እንዳስገባች ተረድቶ ፈታ። ሲያጣራ ግን ጉዳዩ እሱ እንዳሰበው እንዳልሆነ አወቀ። ኒካሑ ይወርዳል ወይ?
=>ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑ ባዝ እና ኢብኑ ዑሠይሚን ኒካሑ አይወርድም ብለዋል።
=
ከሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ፈትሑል ዐላም ኪታብ (8/543 - 554) ተጨምቆ የቀረበ
=
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
















እምቢ በይ እታለም!
(ከካ|ፊ- ር ጋር ትዳር ለሚያስቡ እህቶች)
=
ለአላፊ ደስታ ስትይ ………. ለምትከስመው ጠውልጋ
ትዳር ከምትመሰርቺ ………. ኢስቲንጃ ከሌለው ጋ
ለዚች ጤዛ ዱንያ ብለሽ ………. ብልጭ ብላ ለምትጠፋ
ከለጋሱ ጌታ ዘንዳ ………. ከትንኝ ክንፍ ለማትሰፋ
እያለቀስን መጥተን ሳለ ………. እያለቀስን ለምንለቃት
አኺራችንን አስበን ………. ምናለ ብንንቃት?!!

እቱ ከጌታችን ጋራ ………. ነገ ከባድ ሂሳብ አለ
አስፈሪ ጭንቅ የሚያይበት ………. መናጢ ሁሉ ያልታደለ
ዛሬ ከመስመሩ ለቆ ………. ወደ ጥፋት ያጋደለ
ከእርኩሳን ጋር ተጣምሮ ………. በክህደት ላይ የዋለለ
ነገን በዛሬ የሸመተ ………. የዋህ እራሱን ያታለለ
“ያ ለይተኒ” የሚልበት ………. ነገ የቁጭት ቀን አለ፡፡

ይልቅ ስሚኝ እህት አለም፡

ትዳር የጌታ ሲሳይ ነው ………. ከባለ ዐርሹ የሚወሰን
ስለቋመጥን ሳይሆን ………. ፈቃዱ ሲኖር የሚደርሰን
“ይታደሉታል እንጂ ………. አይታገሉትም” ነው ነገሩ
ውሳኔው ከላይ እስከሚወርድ ………. ከዱዓህ ጋር ይሶብሩ፡፡
እንጂ ከእንጨት አምላኪ ጋ
እንጂ “አንድም ሶስትም” ከሚል ዜጋ
በስሜት ናላው ዞሮ ………. ሊያጠምድሽ መረብ ቢዘረጋ
ማር በሚተፋ ምላሱ ………. በስልት ወዳንቺ ቢጠጋ
ምናባዊ ሐሴት አይተሽ ………. ጉም ለመጨበጥ መንጠራራት
ለተስፋ ዳቦ እየቋመጥሽ ………. አትሁኚ የ’ሳት እራት፡፡

በምታይው ብልጭልጭ ………. እራስሽን አትደልይ
ባለ ገዳይ መርዙ እባብም ………. ለስላሳ ነው አስተውይ፡፡
ይልቁንም ረጋ ብለሽ ………. ከአፅናፍ ማዶ ተመልከቺ
ጤፍ በሚቆላ ምላሱ ………. በተኩላ እንዳትረቺ
ለዚች አጭር ህይወት ስትይ ………. በራስሽ ላይ አትሸፍቺ፡፡

ለዚህ ብላሽ ፈራሽ ገላ
ለዚህ ከንቱ ገልቱ አተላ
ዛሬ እጅሽን አትዘርጊ
ነገ እንዳትጠወልጊ፡፡
ሶላት ቁርኣኑ ተትቶ
ሒጃብ አደቡ ተዘንግቶ
በላኢላሀ ኢለላህ ቦታ ………. “አንድም ሶስትም” ተተክቶ
ግንባር ለመስቀል ሲዋረድ ………. የሐያሉ ሱጁድ ቀርቶ
ከቤትሽ ግድግዳ ላይ ………. የፈረንጅ ስእል ተለጥፎ
ሐያእ ግብረ-ገብነትሽ ………. ከላይሽ ላይ ተገፎ
ከግንባርሽ ላይ ነጥፎ ………. ከልብሽ ላይ ተንጠፍጥፎ
መስጂድ የለመዱ እግሮችሽ ………. ወደ ከኒሳ ሲያመሩ
ጠላ ኮረፌ እየጠመቅሽ ………. ሰካራሞቹ ሲያጓሩ
ይሄ እውን የሆነ እለት
ያኔ ሆነሻል የቁም ሙት!!
.
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 21/2008)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor




#ቁርአንን__የተመለከተ_አጭር__መረጃ
=>ቁርአን የወረደው ለ23አመታት ነዉ።
=> ቁርአን በመካ ዉስጥ ለ13 አመታት ወርዷል።
=>ቁርአን መዲና ዉስጥ ለ10 ለአመታት ወርዷል።
=>የቁርአን ክፍሎች(ጅዞች) 30 ናቸው።
=>የቁርአን ሂዝብ 60 ናቸው።
=>የቁርአን ምዕራፎች (ሱራዋች) 114 ናቸው።
=>የቁርአን "ሩቡዕ" 240 ናቸው።
=>የቁርአን አንቀፅ ብዛት 6236 ናቸው።
=>የቁርአን ፊደላት ብዛት 321250 ናቸው።
=>ከቁርአን ውስጥ ታላቁ ምዕራፍ (ሱራ) ሱረቱል አል-ፋቲሀ።
=> ከቁርአን ዉስጥ ትልቁ አንቀፅ (አያህ) አያተል አል-ኩርሲ።
=>ቁርአን ውስጥ ረጅሙ ምዕራፍ (ሱራ) ሱረቱል አል-በቀራ ።
=>ረጅሙ የቁርአን አንቀፅ "አያተል ደይን" ሱረቱል አል በቀራ አንቀፅ 282 ነው።
=>ቁርአን ውስጥ ረጅሙ ቃል "ፈአስቀይናሙሁ"


Репост из: ቅድምያ ለ ተውሂድ
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አንድ ሰው በምንድን ነው ከአህለል ሱና ክልል የሚወጣው
ሸይኽ ፈውዛን ሀፊዘሁሏህ
https://t.me/Tewuhid1/1953
https://t.me/Tewuhid1/1953


‏إنا لله وإنا إليه راجعون
توفي فضيلة الوالد الشيخ الحيدان رحمه الله تعالى وأسكنه الفردوس الأعلى ..

اللهم أجرنا في مصيبتنا و اخلف لنا خيرا منها 💧

🔸‏الاستعداد ليوم الرحيل من الدنيا إلى الآخرة


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሸይኽ ሑሴን ጂብሪል ማነው?
የሸህ ሑሴንን ታሪክ የሚገልፀው አንድ ለናቱ ስራ ይሄው ቦጋለ ተፈሪ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ የጠቆመው ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሰውየው ምናባዊ ይሁን እውነተኛ ሰው ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ፀሐፊው እንዲህ ይላል፡- “ሼህ ሁሴን የነቢዩ መሐመድ ተከታይ ነበሩ፡፡ ቢሆኑም እንደ እስላሞች ጫት አይቅሙም፣ ሶላት አያደርሱም፣ መስገጃ ቁርበት፣ ውኃ መያዛ ጦሌ አያንጠለጥሉም፡፡ እንደ ዓባይ ጠንቋይም መጽሐፍ አይገልጡም፣ ጠጠር አይጥሉም። ግን ሱረት (ሐቀኑር) ያሸታሉ፣ ብርዝ ይጠጣሉ፣ ፍርድም ሲፈርዱ ማለት የሚታያቸውን ሲናገሩ ብርዝ በፎሌ (በሽክና) ይዘው ነበር ይባላል። [ቦጋለ፡ 23]
አያችሁ አይደል? ውዱእ እንኳ ያልነበረው ሰው ነው።

በነገራችሁ ላይ መጽሐፉ አንዳንድ የሃገራችን ህዝቦችንና ቋንቋዎችን የሚያነውሩ ቆሻሻ ስንኞች አሉት። ይህም የሚያሳየን አቶ ቦጋለ አንዳንድ በብሄር ጥላቻ የታወሩ ሰዎች የገጠሙትን አሰስ ገሰስ እንደሰበሰበ ነው። እኔ እንዲያውም እራሱን ቦጋለን ነው የምጠረጥረው። በሸህ ሁሴን ትንቢት ስም የራሱን ቅርሻት ለቅልቆ ሊሆን ይችላል። በነገራችን ላይ ቦጋለ ተፈሪ ጥሩ ነጋዴ ነው። ይህንን ብሽቅ መፅሀፍ ከ15 ጊዜ በላይ በማሳተም በደምብ አድርጎ ቸብችቧል። ታዲያ ገበያው እንዳይቀዘቅዝበት የኋላ ኋላ አሪፍ ዘዴ ዘይዷል። የመጽሐፉ የኋላኛው እትሞች ላይ እነዚያ ትግሬውን፣ አሮሞውን፣ ጉራጌውን የሚያንቋሽሹ ፀያፍ ፀረ ህዝብ ስንኞችን አውጥቷቸዋል። ችግሩ ግን የሱን ፈለግ የተከተሉ አያሌ ቦጋለዎች መፈልፈላቸው ነው። ከቀደሙ ህትመቶች ላይ ያሉትን ጨምሮ የራሳቸውን ጅምላ ፈራጅ የሆኑ ፀያፍና መደዴ ስንኞችን በማከል በኢንተርኔት ይለቃሉ። ወገኔ ሆይ! የቦጋለዎች መጫወቻ አትሁን። እንዴት ከቦጋለ ያነሰ ግንዛቤ ይኖርሃል? ቦጋለኮ ቢያንስ 15 ጊዜ ይህንን ኮተት እያተመ ቸብችቦታል። ሞኝነት ብዙ ደረጃ አለው። እንደ ቦጋለ ባሉ ቂሎች በዚህ መጠን መታለል ግን የእውነት በጣም የሚያሸማቅቅ ነው።

Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Показано 20 последних публикаций.

85

подписчиков
Статистика канала