ሰፊ ህዝብ የሚያስተናግዱ መስሪያ ቤቶች በር ላይ መታጠቢያ ከማዘጋጀት የዘለለ በቂ ዝግጅት አይታይባቸውም። በሽታው በትንፋሽም የሚተላለፍ እንደሆነ እየታወቀ የፊት መሸፈኛ እንኳን ሳያደርጉ ያን ሁሉ ደንበኛ ሲያስተናግዱ ማየት ግራ የሚያጋባ ነው። ከዚያ ሁሉ ተመላላሽ መሐል ከበር እጆቹን ታጥቦ የገባ የቫይረሱ ተሸካሚ ቢኖር ጉዳዩን ለማስፈፀም ሲነጋገር በቀላሉ ሊያስተላልፍባቸው ይችላል። ቀጥሎስ? አንዴ ቫይረሱን የተሸከመ ሰራተኛ ፈርሞ በሚሰጠው ሰነድ፣ ቆጥሮ በሚሰጠው ብር፣… ስንቶችን ሊያለቃልቅ እንደሚችል አስቡት።
ትላንት በሆነ ጉዳይ ወደ ሁለት ጤና ጣቢያዎች ሄጄ ነበር። ሌላው ቀርቶ ነርሶች ላይ እንኳን በቂ ጥንቃቄ አይታይም። ሰፍቷቸው የተንጠለጠለ ማስክ ለብሰው አፍንጫቸው ባዶ ሆኖ አፋቸውን ይሸፍናሉ። ይሄ ምን ማለት ነው? እንዲያው ጥሩ ማስኮችን የሚያቀርብ ቢጠፋ እንኳን ምናለ ሰብሰብ አድርገው አስረው እራሳቸውን ቢጠብቁ? የጤና ተቋማት ጥንቃቄ የማያደርጉ ከሆነ የቫይረሱ ማከፋፈያ ቦታ ነው የሚሆኑት።
https://t.me/IbnuMunewor