መሷሊሐል ሙርሰላ፣ የመውሊድ አክባሪዎች ሌላኛው ምሽግ
~~ ~~~ ~~ ~~~~ ~~~~ ~~~
የመውሊድ ጨፋሪዎች ከዚህም ከዚያም የሚቃርሟቸው መረጃ መሰል ማምታቻዎች እርቃን ሲቀሩ የሚጠጉበት የመጨረሻው ምሽግ መሷሊሐል ሙርሰላ ነው። መሷሊሐል ሙርሰላ የሚባሉት ድጋፍም ይሁን ተቃውሞን የሚያሳይ የቁርኣን ወይም የሐዲሥ ወይም የኢጅማዕ ወይም የቂያስ ቀጥተኛ የሆነ መረጃ ያልመጣባቸው ነገር ግን በጥቅሉ ከሸሪዐው ግቦች ስር የሚካተቱ ጥቅሞች ናቸው። [መዓሊሙ ኡሱሊል ፊቅህ፡ 235]፣ [አልመሳሊሑል ሙርሰላ ሊሽሺንቂጢ፡ 19] የነሕውና የሶርፍ ትምህርት፣ ኡሱሉል ፊቅህ፣ የቁርኣን በአንድ መሰብሰብ፣ በቁርኣን ፅሑፍ ላይ የፊደል መለያ ነጥቦችን መጠቀም፣ የህዝብ ብዛትን ተከትሎ የተወሰነው የዑሥማን አዛን፣ ሐዲሦችን መመዝገብና መጠረዝ፣ ወዘተ የመሷሊሐል ሙርሰላ ምሳሌዎች ናቸው።
ከነዚህ ምሳሌዎች አንፃር መውሊድን ስንመለከተው አብሮ ለንፅፅር የሚቀርብ አይደለም። እነዚህ ነገሮች ወሕይ ሲወርድበት ከነበረው ዘመን በኋላ በገጠሙ አዳዲስ ክስተቶች የተነሳ ሸሪዐውን ለመጠበቅ ያስፈለጉ አስገዳጅ ነገሮች ናቸው። ማህበረሰቡ ላይ በታዩ ክፍተቶች የተነሳ ጉዳዮቹ ችላ ቢባሉ ወይም ባይፈፀሙ መጠኑ ይብዛም ይነስ በጉልህ የሚታይ አደጋ ወይም ክፍተት ተደቅኖ ነበር። ይህንን አደጋ ወይም ክፍተት ለመቀልበስ ወይም ለመቀነስ ሲባል ነው እነዚህን ጉዳዮች መፈፀም ያስገደደው።
መውሊድ ግን በራሳቸው በፈፃሚዎቹ ምስክርነት ብቸኛ ነብዩን ﷺ የመውደጃ መንገድ አይደለም። ስለዚህ እንድንፈፅመው የሚያስገድደን ሁኔታ የለም ማለት ነው። አስገዳጅ ሁኔታ ቢኖር ኖሮ ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች የጀመሩ አባቶች ሺዐዎች እስከሚጀምሩት ሳይጠብቁ ይህንንም ይጀምሩት ነበር። እነዚህ ሱፍዮች ግን “የመውሊድ ዋነኛ ዓላማ ነብዩን ﷺ ማስታወስ ነውና እርሳቸው በህይወት እያሉ አስፈላጊ አልነበረም” ይላሉ። ይህንን ከእውነት ጋር የተኳረፈ ሰበብ ለሙግት ያክል ይሁን እንበልና እሳቸው ከሞቱስ በኋላ ሶሐቦቻቸው፣ ታቢዒዮቹ፣ አትባዑታቢዒን፣ አራቱ ኢማሞች ለምን አላከበሩትም? የጀመረው ሙዞፈር ነው አይደል የምትሉት? ስለዚህ በስድስት ክ/ዘመን ሙሉ ያለፈ ትውልድ እሳቸውን ማውሳት አልፈለገም ማለት ነው?
በነገራችን ላይ እሳቸውን ለማውሳት አመት መጠበቅ አያስፈልግም። እንዲያውም ጭፈራ ከሶለዋት አይደለም። ይልቁንም እያንዳንዱ ሙስሊም በየሶላቱ ላይ ስማቸውን ያነሳል። ሙአዚኑ በየአዛኑ ላይ “አሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉሉላህ” ሲል ያስተጋባል። ሰሚውም በተመሳሳይ ይከተላል። ከአዛን በኋላ ባለው ዚክር ላይ፣ ተሸሁድ ላይ፣ ከሶላት በኋላ ባሉ ዚክሮች ላይ፣ ከውዱእ በኋላ ባለ ዚክር ላይ፣ መስጂድ ሲወጣና ሲገባ፣ በሌሎችም እጅግ በርካታ ክስተቶች ላይ የነብዩን ﷺ ስም ያወሳል። በየትምህርቱ፣ በየደዕዋው፣ በየኹጥባው፣ በየኒካሑ ፕሮግራም ላይ ስማቸው ይነሳል። የሚጠበቅብን ሰዎችን በነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው። ይበልጥ ማስታወስና መዘከር ለፈለገ ደግሞ ተጨማሪ ትምህርት መስጠት፣ ሲራቸውን ማቅረብ፣ ሰዎች ሱናቸውን እንዲላበሱ ማስተማር እንጂ በጭብጨባና በሙዚቃ መሳሪያ እየታገዙ “አሕመድ የመዲናው” እያሉ መደለቅ የጭፈራ ወልፍን ከማስተንፈስ ያለፈ ሚና የለውም።
እናም መውሊድን በመሷሊሐል ሙርሰላ ጥቅል መርህ ውስጥ ማካተት ስሜት የተጫነው ድምዳሜ ነው። እንዲያውም መሷሊሐል ሙርሰላን በሆነ ጉዳይ ከመጠቀማችን በፊት ሊሟሉ የሚገባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች አሉ። እነሱም፡-
1. ማሳካት የታለመው “ጥቅም” ግልፅ ከሆኑ ማስረጃዎች ጋር የሚፃረር መሆን የለበትም።
2. ኢጅቲሃድ በማይፈቀድባቸው ጉዳዮች ላይ መሆን የለበትም።
3. በተጨባጭ ሸሪዐው እንዲጠበቁ ከሚፈልጋቸው ግቦች ውስጥ መሆን አለበት።
4. ይበልጥ ሚዛን ከሚደፋ ጥቅም ጋር መጋጨት የለበትም። ወይም ደግሞ ሲፈፀም የከፋ ጉዳት ላይከተለው ነው።
5. ጥቅሙ አጠቃላይ ህዝባዊ እንጂ ግለሰባዊ ላይሆን ነው። [አልዋዲሕ ሊኡሱሊል ፊቅህ ሊልአሽቀር፡ 151]
6. ነብዩ ﷺ ሊሰሩት ቢፈልጉ መፈፀም የሚያስችላቸው ሁኔታ እያለ ሳይሰሩት የቀረ ነገር መስለሐ አይደለም። ልክ እንዲሁ ሊሰሩት ቢፈልጉ የሚከለክላቸው ምክንያት ካልነበር ያ ነገር መስለሐ አይደለም።
መውሊድን ከነዚህ ቅድመ-ሁኔታዎች አንፃር ስንቃየው የማለፍ አቅም አለው ወይ? ከተባለ በጭራሽ ነው መልሱ!! ምናልባት በተወሰኑት ጭቅጭቅ ሊነሳ ይችላል። እስኪ ከ 4ኛውና ከ6ኛው መስፈርቶች አንፃር እንገምግመው። መውሊድ ፈቃጆቹም ጭምር የማይስማሙባቸውን ብዙ ጥፋቶችን እያስከተለ ነው። በዚያ ላይ ነብዩ ﷺ ሊሰሩት ቢፈልጉ ሊተገብሩት የሚቻል ነበር። ቢያስፈልግ ኖሮ እንዳይፈፀም የሚያግድ ነገር አልነበረም። “ምናልባት ግዴታ እንዳይሆን ሰግተው ከሆነስ?” የሚል ምክንያትም አይሰራም። ከመውሊድ አንፃር ይህንን የሚጠቁም ፍንጭ የለንምና። ይሄ ምክንያት ቢሆን ኖሮ ከነብዩ ﷺ ሞት በኋላ በሶሐቦችና በታቢዒዮች ጊዜ ሊፈፀም ወይም ቢያንስ ቢያንስ አደራው እንኳን ሊተላለፍ ይችል ነበርና።
ደግሞም “መሳሊሐል ሙርሰላ” በሚል “መውሊድ ነብዩን ﷺ ከፍ በማድረግ ዲንን የመጠበቅ ሚና ስላለው በሸሪዐው ይሁንታ ያገኛል” ማለት ሰዎቹ ያሉበትን አሳፋሪ የዲን ግንዛቤ የሚያጋልጥ ነው። ሰው እንዴት በአመት አንድ ቀን በሚከበር ጭፈራ ዲን ይጠበቃል ብሎ ያስባል?! እንዲያውም የመውሊድ ስርኣቶችን ብንታዘብ ዲን በሚያፈርሱ ሺርኮች፣ መስጂዶችን በሚያረክሱ ጭፈራዎች፣ ከሶላት በሚያዘናጋ ዳንኪራ፣ ወዘተ የታጨቁ ናቸው። ከዚህም አልፎ ብልግና ሁሉ የሚፈፀምበት አጋጣሚ አለ። እነ አልመቅሪዚ፣ ኢብኑል ሓጅ፣ ኢብኑ ሐጀርና እነ ረሺድ ሪዷም በዘመናቸው የነበረው መውሊድ ላይ የሚፈፀሙ ሰቅጣጭ ጥፋቶችን ከዘረዘሩ ውስጥ ናቸው። ጉዳዩ በየጊዜው እየባሰ ነው ያለው።
ደግሞም የራሳቸውን ስሌት ብንጠቀም እንኳ መውሊድ ውግዘት እንጂ ድጋፍ አያገኝም። የሚጠቅም ነገር የሸሪዐ ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነ እንደ መውሊድ ያለ የሚጎዳ ነገር ደግሞ የሸሪዐ ድጋፍ አያገኝም ማለት እንችላለን። “አይ ከውስጡ ያሉ ጥፋቶችን አርመን እንጓዝ” ለሚል አካል የምንለው በርግጥ ብትቀንሱ ለራሳችሁም፣ ለኡማውም ማዘን ነው። መቼም ከጅግ በጣም መጥፎ በጣም መጥፎ፣ ከበጣም መጥፎ መጥፎ ይሻላል። ሆኖም ግን ደረጃው ይለያይ እንጂ ቢድዐ ነውና የተወገዘ ከመሆን አይተርፍም። ይልቅ ከውስጡ ያሉ ጥቅሞችን - ምናልባት ካሉ - በሌላ አማራጭ ስለሚገኙ ሶሐቦች በተብቃቁበት መንገድ ተብቃቁ። ስለዚህ የጥፋት መንገዶችን ለመዝጋት ሲባል የመውሊድን በር መከርቸሙ እራሱ ሁነኛ መፍተሄ ነው። እራሱን የቻለ መሷሊሕም አለው። እናም በመውሊድ መጥፎነት ላይ ባንግባባ እንኳን ለብዙ ጥፋቶች በር ስለሚከፍት ሊዘጋ ይገባዋል። በኢስላም ወደ ጥፋት የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋት (ሰዱ ዘራኢዕ) ከታወቁ መርሆዎች ውስጥ አንዱ ነውና። ሸውካኒ መውሊድን ሲኮንኑ ካነሷቸው ነጥቦች አንዱ እንዲህ የሚል ነው፡- “ወደ ጥፋት የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋትና ወደማይፈቀድ ነገር መንጠላጠያ ገመዶችን መቁረጥ ብዙሃን ምሁራን እርግጠኛ ከሆኑባቸው ወሳኝ ሸሪዐዊ መርሆዎች ውስጥ ነው። አንተ እራስህ እንጥፍጣፊ ሚዛናዊነት ቀርቶህ ከሆነ ይህንን ሐቅ አትክድም።” [አልፈትሑ ረባኒ፡ 2/1091]
==================
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor