አቋም ለመቀየር የማይታክተው ሙስጦፋ ዐብደላህ
~
አቋም በመቀያየር ላይ ሙስጠፋ ዐብደላን የሚደርስበት ሰው አላውቅም። ምናልባት ቀድሞ ሱፊ ሊሆን ይችላል። የሰማሁት ቢኖርም እርግጠኛ ስላልሆንኩ ነው።
* ብቻ በቁርጥ የሚታወቀው የሆነ ጊዜ ከኢኽዋኖች ጋር ነበር። ወጣ። የሆነ ያክል ቆየ።
* ከሐጁሪ ጭፍራ ሲቀላቀል ሞቅ ያለ አቀባበል ተደረገለት። ጀምዒያ ይቻላል ሲል እንዳልቆየ በጀምዒያ ሰበብ ተብዲዕ ወደ ማድረግ አለፈ። ለሐጁሪ ወግኖ ቀድሞ ሲያከብራቸው የነበሩ ዑለማኦችን ቀፋፊ በሆነ መልኩ ወረፈ።
* ጥቂት ጊዜ ቆየና ከራሱ ጭፍራ ጋር ተበጣብጦ፣ በዱላ ተከታክቶ፣ ፖሊስ ጣልቃ እስከሚገባ ደርሰው ተራራቁ። አካሄዱ በውጥረት የተሞላ በመሆኑ በተለያዩ ቦታዎች ሁከት እየፈጠረ በተደጋጋሚ ወህኒ ወርዷል። እሱ ለደዕዋ የተከፈለ መስዋእትነት እንደሚያደርገው ይጠበቃል። በተደጋጋሚ ለመታሰሩ ዋናው ምክንያት ግን የራሱ በጥባጭ አካሄድ ነው።
* ቀደም ብሎ የዑዝር ቢል ጀህል ጉዳይ ልዩነቱ የሚቻቻሉበት የሚተላለፉበት እንደሆነ ያምን ነበር። ያንን የተጓዘበትን ገደል ከቶ አሁን በዑዝር ቢል ጀህል ሰበብ የትላንት ጭፍሮቹን ለሁለት ሰንጥቆ፣ ባህር አቋርጦ የመን ድረስ ያሉ ሲያደንቃቸውን የነበሩ አካላትን ጭምር ዝቅ ካለ በኢርጃእ እስከመወንጀል ደርሷል።
* ለሐጁሪ ወግኖ ሌሎች ላይ እንዳልዘመተ አሁን ደግሞ ለሐጁሪ ጀርባውን ሰጥቷል። ይጎነታትለው ይዟል።
* በጀምዒያ ጉዳይ ስንት ዘመቻ እንዳላደረገ አሁን ደግሞ ወደ ሳዑዲ ሄዶ ጀምዒያ የሚፈቅዱት ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አራጂሒይ ላይ እየተማርኩ ነው እያለ ነው። ሸይኽ አራጂሒይ በአቡ ሐኒፋ ጉዳይም ቢሆን እንደ ሙስጦፋ ጠርዝ የረገጠ አቋም የሚያራምዱና እኔ ያልኩትን ካላላችሁ ብለው አገር የሚበጠብጡ አይደሉም።
* የሚገርመው ከመውጣቱ በፊት ከአማራ ክልል የመጅሊስ ኃላፊ ጋር ተገናኝቶ አብሮ ምሳ ተገባብዞ የጀምዒያ ፍቃድ ጠይቆ ነበር። ሲጀመር አይኑን በጨው አጥቦ ቢሸመጥጥም ወደ ሳዑዲ የሄደው ራሱ በታዋቂ ኢኽዋኖች ድጋፍ ነው።
ነገ ደግሞ ምን ይዞ እንደሚመጣ እንጃ። ያለ ፊትና መቆየት የሚጨንቀው ይመስላል። በአንድ አቋም ላይ የሆነ ያክል ከቆየ በኋላ የኺላፍ ነጥብ ፈልጎ አቧራ ያስነሳና ከራሱ ጭፍራ ጋር አይጥና ድመት ይሆናሉ። ነገሮችን ራጂሕ ነው የሚለውን መርጦ ይቻላልም ይሁን አይቻልም ብሎ መቆም፣ በልክ መያዝ አይሆንለትም። ይልቁንም ለሁለት የሚከፍል ግንብ ነው የሚሰራው። እሱን የተቀበለና ያልተቀበለ። ይህንን ማዶና ማዶ መርገጡን፣ ይህንን ከአቋም አቋም መከረባበቱን፣ ይህንን እንደ ፔንዱለም መወዛወዙን ከነ ኢማሙ ሻፊዒይ "ቀውሉን ቀዲም" እና "ቀውሉን ጀዲድ" መለያየት፣ ከነ ኢማሙ አሕመድ የተለያዩ ሪዋያዎች ጋር ሲያመሳስል ትንሽ እንኳ እፍረት አይሰማውም። እነዚያ አኢማዎች በፊቅህ ርእሶች ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ያንፀባረቁባቸውን ጉዳዮች እሱ ወላእና በራእ እየቋጠረ ለቡድናዊ ፍረጃ በሚጠቀማቸው ጉዳዮች ላይ አንዴ እየፈቀደ፣ ሌላ ጊዜ እያወገዘ መንቦጫረቁ ጋር ያመሳስላል። የአኢማዎች አካሄድ እና ያንተ አካሄድ እኮ ሆድና ጀርባ ናቸው። ምኑን ከምኑ ነው የምታገናኘው? ይሄ ጉዳይ ለማንም የሚሰወር ሆኖ አይደለም። ማምታታትና ማጭበርበር ከስጋና ከደሙ ጋር የተዋሀደ ሆኖበት እንጂ።
አንድ ጉዳይ ከጀመረ ሌላ ጉዳይ የሌለ እስከሚመስል ሰርክ ያንን ይዞ ነው የሚነዛነዘው። የጀምዒያን ጉዳይ፣ የሐጁሪይን ጉዳይ፣ የአቡ ሐኒፋን ጉዳይ ማንሳት ይቻላል። አንዴ ተናግሮ ማለፍ ከዚያው ሲያስፈልግ መናገር አይበቃውም። አመታት እኝኝኝኝ የሚልበት የወላእና በራእ ጉዳይ አድርጎ ነው የኖረበት። አሁን እነዚህ አጀንዳዎች ኤክስፓየር አድርገው ጠዋት ማታ፣ ቆሞ ተቀምጦ ስለ ዑዝር ቢልጀህል ነው እኝኝኝኝ እያለ ያለው። ነገ ደግሞ ሌላ ጉዳይ ይፈልጋል።
ሲተጣጠፍ ሐያእ አያውቅም። ትናንት የኖረበትን፣ ደጋግሞ ያስተጋባውን ጉዳይ መመለሱን እንኳ በቅጡ ሳይናገር ተብዲዕ ማድረጊያ ሾተል አድርጎ ገልብጦ ሲመዘው ምንም አይገርመውም። ከዚያ ደግሞ ያንን በዚያ መልኩ የያዘውን ጉዳይ ጥሎ አቋም ይቀይራል። መቅቀያየሩ፣ መከረባበቱ አያሳስበውም። በፈሰሰበት የሚፈስሱ፣ በታጠፈበት የሚታጠፉ መንጋዎች አሉት። እሱ ግን አይሞቀው አይበርደው። እንኳን አቋሙን ስሙን የሚቀይር ጉድ ነው። ልብ በሉ! የቀድሞ ስሙ ጀማል ወርቄ ነበር። ምናልባት ከዚያ በፊት የቀያየረው ይኑር አይኑር አላውቅም።
በርግጥ ሙስጦፋ እስካሁን ያልቀየረውና በኢስቲቃማ የዘለቀበት አንድ ነገር አለው። እሱም ውሸቱ ነው። ሲበዛ ፈጣጣ ውሸታም ነው። አሁን እዚህ ያነሳኋቸውንና ብዙ የተከረባበተባቸውን ጉዳዮች ራሱ ሊሸመጥጥ እንደሚችል እጠብቃለሁ። ሌሎች ላይ ዋሽቶ ለመለጠፍም አይኑን አያሽም። እንዲያውም ለሱ የቀረቡ ሰዎች ጭምር በውሸቱ ተማርረው፣ እየሸመጠጣቸው ቢቸግራቸው ሪኮርድ ሁሉ እያደረጉት እንደነበር በቅርቡ ሰምቻለሁ።
ታዲያ የሚገርመው እሱ በተገለባበጠ ቁጥር የሚገለባበጡ፣ በወረደበት ቁልቁለት ሁሉ የሚወርዱ፣ በወጣበት ተራራ ሁሉ የሚወጡ ታማኝ ሙሪዶችን ማፍራቱ ነው። ሌላው ቢቀር ሲወጣ ሲወርድ አብራችሁት ስትንገላቱ ጣመናው (ስትራፖው) አይከብዳችሁም ወይ? መውጣት መውረዱ አያቆስላችሁም ወይ? "ኧረ አሁንስ በዛ!" የምትሉበት ጊዜ የለም ወይ? እሱ እንደሆነ ልማደኛ ነው፣ ነገም ሌላ አቋም ይዞ ይመጣል። እድሜ መስተዋት ነው ካለን እናያለን። ምናልባትም ዞሮ ዞሮ ከተነሳበት የኢኽዋን ፌርማታ ላይ ድቅ ሊል ይችላል። "ከሐጁሪ ይልቅ እነ እከሌ ይሻላሉ" እያለ ትናንት ኢኽዋኖች እንደሆኑ ሲገልፃቸው የነበሩ አካላትን ስም መጥቀሱ የአጋጣሚ አይመስልም።
ለመንጋዎቹ የምለው! ሲሆን ሲሆን ለራሳችሁ ኣኺራ ስትሉ ከሱ የፊትና ባቡር ውረዱ። ባቡሩ ማረፍ የማያውቅ፣ አቅጣጫውን በፍጥነት የሚቀያይር ስለሆነ በጊዜ ካልወረዳችሁ የሆነ ሰዓት ላይ ከ'ስከዛሬው የባሰ ከባድ ጉዳት ያደርስባችኋል። አመጣጡንና አያያዙን አይቼ ነው የምናገረው። ማንም እንዳሻው የሚያጥፋችሁና የሚዘረጋችሁ አትሁኑ። እምቢ ካላችሁ ደግሞ እሱ መተጣጠፉን ስለለመደው ምንም አይመስለውም። እናንተ ግን በሱ ፍጥነት ስትታጠፉ እንዳትቀጩ ረጋ እያላችሁ አስፍታችሁ ቢሆን ቢያንስ አደጋ ትቀንስላችሁ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዋል 4/ 1446)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor