ሙስጦፋ ዐብደላህ ከከሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አራጂሒይ ዘንድ
~
የድሮው ጀማል ወርቄ የአሁኑ ሙስጦፋ ዐብደላህ አቋሙን ከጠርዝ ጠርዝ በመቀያየር የታወቀ እንደሆነ ትናንት ገልጫለሁ። የተጓዘባቸውን እርስ በርስ የሚቃረኑ ጉዳዮችንም ጠቅሻለሁ። ልብ በሉ! በየጊዜው የሚቀያይራቸው አቋሞች እንደሱ አያያዝ የፊቅህ ርእሶች አይደሉም። ይልቁንም ዝቅ ቢል ሰዎችን ከሱና በማስወጣት ተብዲዕ የሚያደርግባቸው ጉዳዮች ናቸው። እንዲያውም አሁን አሁን ከኢስላም ጭምር ለማስወጣት ዳር ዳር እያለ ነው። በዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ወላእና በራእ እየቋጠረ ቡድን በሚፈጥርባቸው ጉዳዮች ላይ አቋሙን መቀያየሩን በፊቅህ ርእስ ላይ ሃሳብ እንደመለወጥ እያስመሰለ ማቅረቡ ያው የተለመደው ማጭበርበሩ አንድ አካል ነው።
ለምሳሌ የዑዝር ቢል ጀህልን ጉዳይ እንመልከት። ቀደም ሲል በዚህ ርእስ የተለያየ ሃሳብ ማንፀባረቅ ለመራራቅ የማያበቃ የሚቻቻሉበት ጉዳይ እንደሆነ ያምን ነበር። ዛሬስ? ከራሱ ጭፍሮች ጋር ተደባድቦ የተለያየው በዚህ ርእስ ምክንያት ነው። አንድ ሰው ባለማወቅ ሺርክ ላይ ቢወድቅ አለማወቁ ዑዝር ይሆነዋል፣ ከኢስላም አይወጣም የሚሉ አካላትን እጅግ ፀያፍ በሆነና ብል -ግና በተሞላበት መልኩ እያብጠለጠለ ነው። እንዲያውም ለጃሂል ዑዝር መስጠት ይግገባል የሚል ሰው አቋሙ ስህተት እንደሆነ ከተነገረው በኋላ ከኢስላም ይወጣል እስከማለት ርቀት ሄዷል። በዚህ ንግግሩ ራሱን ነው ቅርቃር ውስጥ የከተተው። እንዴት? በአዲስ መስመር እንገናኝ።
ሙስጠፋ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ከሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አራጂሒይ ላይ እየተማርኩ ነው እያለ ነው። አራጂሒይ ዑዝር ቢል ጀህል እንዳለ፣ ጃሂል ባለማወቅ ሺርክ ቢወድቅ፣ ሙታንን ኢስቲጋሣህ በማድረግ ቢለምን ድርጊቱ ሺርክ ቢሆንም ሳያስተምሩ በፊት ከኢስላም ማስወጣት አይገባም የሚል አቋም አላቸው። ይሄ አቋማቸው አንዴ ሁለቴ ሳይሆን ደጋግመው የገለፁት ነው። የተወሰኑ ድምፆቻቸውን አያይዣለሁ።
ስለዚህ፡
ሙስጦፋ እዚህ ከተብዲዕ ጀምሮ ከኢስላም እስከማስወጣት የደረሰበትንና ብዙ ሰዎችን የበጠበጠበትን ጉዳይ ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አራጂሒይ አይቀበሉትም ማለት ነው። እዚያ አንገቱን ደፍቶ፣ ድምፁን አጥፍቶ፣ ሌላ ሰው መስሎ፣ ሙስጠፋ ሳይሆን ጀማል ወርቄ ሆኖ ሊማር ነው ማለት ነው። ያ ሁሉ "ዓዚሮች" እያለ ዑዝር በሚሰጡ ሰዎች ላይ ሲያወርደው የነበረው ውርጅብኝስ? እሱን በኢንተርኔት ይቀጥላል። ራጂሒይ ዘንድ ደግሞ ሌላ ሰው ሆኖ ይቀርባል። እንጂ ዑዝር የሚሰጥ ሰው ሑጃ ከተቆመበት በኋላ ከኢስላም ይወጣል የሚለውን መፈክሩን በራጂሒይ ላይ ሊተገብረው፣ እሳቸውን ሊያብጠለጥል አይደፍርም።
በርግጥ ይሄ የመጀመሪያ ተቃርኖው አይደለም። ሸይኽ አራጂሒይ በዑዝር ቢል ጀህል ብቻ ሳይሆን በጀምዒያም ጉዳይ፣ በአቡ ሐኒፋም ጉዳይ አቋማቸው ከሱ የተሳከረ አቋም ጋር የሚገጥም አይደለም። ከመሆኑም ጋር "የታላቁ ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አራጂሒይ ተማሪ የሆነው ሸይኽ ሙስጠፋ ዐብደላህ" እየተባለ ሊወደስ፣ በስማቸው ሊነግድ ግን አያፍርም። ሰውየው መንሀጁ ባጭሩ ሲገለፅ ማምታታት ነው። አጭበርባሪ ዶት ኮም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዋል 4/ 1446)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor