Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ወቅታዊ ብስጭትን መነሻ በማድረግ ሳይሆን እንዳጠቃላይ ፎሎው፣ ላይክ፣ ሰብስክራይብ፣ ሼር የምናደርጋቸውን ሁሉ ማጤን ይገባል። የጥፋት ወይም የአጥፊዎች ተባባሪ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን። ስለዚህ ፀረ ኢስላም የሆኑ፣ ፀያፍ ነገሮችን የሚለቁ፣ ህዝብና ህዝብን የሚያባሉ፣ አልባሌ ነገሮችን በመልቀቅ የሚታወቁ፣ አጥማሚ ይዘቶችን በመልቀቅ የሚታወቁ፣ ረብ የለሽ ነገሮችን በመልቀቅ ጊዜ የሚያቃጥሉ፣ የጥላቻ ፖለቲካ የሚያራምዱ፣ ... ገፆችን / ቻናሎችን፣ ግለሰቦችን ከመከተል እንጠንቀቅ። በተግባር Unfollow, Unsubscribe, Unlike እናድርግ። ከግሩፖቻቸው እንውጣ። አላስፈላጊ ይዘት ስናገኝ ሪፖርት እናድርግ። የምንከታተላቸው ወይ ለዲን ወይም ደግሞ ለዱንያ የሚጠቅሙን ብቻ ይሁኑ። ፋይዳ የሌላቸውን ለምንድነው የምንከተላቸው?
=
https://t.me/IbnuMunewor
=
https://t.me/IbnuMunewor