"የመንግስት አካላት ለሰብዓዊ መብት መጠበቅ ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ጥሰቶቹ እንደቀጠሉ ይገኛሉ"- ኢሰመጉ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በተደረገ ምርመራ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጻናት፣አረጋውያን እና ሴቶች በታጠቁ መገደላቸውን አስታውቋል፡፡
ምርመራው የተደረገው ከታህሳስ 7ቀን2016 እስከ ህዳር 23/ 2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በሚገኙ 20 ቀበሌዎች በተፈጸሙ ኢሰብዓዊ ድርጊቶች የንጹሀን ህይወት ማለፉን ለማወቅ መቻሉን ኢሰመጉ ገልጿል።
ይህን ተከትሎም የፌደራል እና የኦሮምያ ክልል መንግስታት በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ የመጡትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በቂ ትኩረት በመስጠት የህዝቡ ሰላም ተጠብቆለት የመኖር መብቱን እንዲያስከብሩ አሳስቧል፡፡
በተጨማሪም በኦሮምያ ክልል በተደጋጋሚ ጊዜ ለሚፈጸሙ ጥቃቶች የፌደራልና የኦሮምያ ክልል መንግስታት የጸጥታ አካላት ጥቃቶች ሳይደርሱ ቅድመ የመከላከል ስራን መስራት፣ ተፈጽመው ሲገኙም አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት ስራን በትኩረት በመስራት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል፡፡
@MeribahTimes