አብዛኛው የፌስቡክ ተጠቃሚ ሙስሊሞች ይመስሉኛል አልኩት ለአንድ ወዳጄ ። ባለፈው በቤጃይ ውድድር ጊዜ ከስድስቱ አሸናፊዎች አምስቱ ሙስሊም መሆናቸውን ሳይ ግምቴን ነበር ያወራሁት ። በርግጥ ፌስቡክን ለመልካም ነገር ስንጠቀም ውጤቱም ደስ ይላል። እንዲያም ሆኖ ግን በዚህ አካባቢ የሚጠፋው ሳያሳስበኝ አልቀረም። ጭራሽ ልጁ ደግሞ ጨመረልኝ -
ቲክቶክ አካባቢም የሚበዙት የኛው ልጆች ናቸው።
ፊልም ቤትም፣ ኳስ ቤትም፣ ቲያትር ቤትም የኛው ልጆች የሚበዙ ይመስለኛል አለኝ።
ሃይስኩል፣ ዩኒቨርስቲ፣ ላይብረሪ፣ ቢሮ፣ ፖለቲካ አካባቢ ግን ብዙ የሉም ።
ወጣቶች የት እንዳሉ ካወቅን እንደ ማኅበረሰብ የት እንዳለን ማወቅ አይከብደንም።
እስቲ ውሎአችን የላቀ ይሁን፣
ጊዜአችን ዕድሜአችን ነውና ይበልጥ ለተሻለ ነገር እናውል፣
በትላልቅ ነገሮች ላይ ተሳትፎአችን ይጨምር፣
ሂማችን ከፍ ይበል። ሂማ ማለት ዓላማ ማለት ነው።
ሶባሐል ኸይር
https://t.me/MuhammedSeidAbx