የማርቆስ ወንጌል
የማርቆስ ወንጌል እና ስህተቶቹ
ስህተት አንድ፦►“እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥”
📖[ማርቆስ 1፥2-3]
►ቅሉ ግን ትንቢቱ ያለው ሚልኪያስ ላይ ነው፦“እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
📖[ሚልክያስ 3፥1]
ማርቆስ ኬት አምጥቶ ነው ኢሳይያስ የሚለን ?መንፈስ ቅዱስ ነው ወይስ ማርቆስ የተሳሳው ?
ስህተት ሁለት፦►“እርሱም፦ ዳዊት ባስፈለገውና በተራበ ጊዜ፥ እርሱ አብረውት ከነበሩት ጋር ያደረገውን፥ አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥”“ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።
📖[ማርቆስ 2፥25/26]
ዳዊት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕት እንጀራ በበላ ጊዜ ሊቀ ካህን የነበረ አብያታር ሳይሆን አቢሜሌክ ነበር፦
📖[1ኛ ሳሙኤል 21፥1/6]
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዳዊትም ወደ ካህኑ ወደ አቢሜሌክ ወደ ኖብ መጣ፤ አቢሜሌክም እየተንቀጠቀጠ ዳዊትን ሊገናኘው መጣና፦ ስለ ምን አንተ ብቻህን ነህ? ከአንተስ ጋር ስለ ምን ማንም የለም? አለው።
² ዳዊትም ካህኑን አቢሜሌክን፦ የተላክህበትን ነገርና የሰጠሁህን ትእዛዝ ማንም አይወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝዞኛል፤ ስለዚህም ብላቴኖቹን እንዲህ ባለ ስፍራ ተውኋቸው።
³ አሁንስ በእጅህ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም የተገኘውን በእጄ ስጠኝ አለው።
⁴ ካህኑም ለዳዊት መልሶ፦ ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን የተቀደስ እንጀራ አለ፤ ብላቴኖቹ ከሴቶቹ ንጹሐን እንደ ሆኑ መብላት ይቻላል አለው።
⁵ ዳዊትም ለካህኑ መልሶ፦ በእውነት ከወጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሦስት ቀን ጠብቀናል፤ የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት፤ ስለዚህ ዛሬ ዕቃቸው የተቀደሰች በመሆንዋ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል አለው።
⁶ ካህኑም በእርሱ ፋንታ ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ ከእግዚአብሔር ፊት ከተነሣው ከገጹ ኅብስት በቀር ሌላ እንጀራ አልነበረምና የተቀደሰውን እንጀራ ሰጠው።
አብያታር የአቢሊክ ልጅ ነው፦“ከአኪጦብም ልጅ ከአቢሜሌክ ልጆች ስሙ አብያታር የሚባል አንዱ ልጅ አምልጦ ወደ ዳዊት ሸሸ።”
►📖[1ኛ ሳሙኤል 22፥20]
ታዲያ ዳዊት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕት እንጀራ በበላ ጊዜ ሊቀ ካህን የነበረ አብያታር ሳይሆን አቢሜሌክ ነበር ማርቆስ አብያታር የሚለው ከየት አምጥቶ ነው የተሳሳተው የማርቆስ ጸሐፊ ወይስ የጠቀሰው ኢየሱስ ወይስ መንፈስ ቅዱስ ?
ስህተት ሦስት ፦►“ሙሴ፦ አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ፦ አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና።”
📖[ማርቆስ 7፥10]
ሙሴ ሳይሆን እግዚአብሔር ነው ያለው ፦
“አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል።”
📖[ዘጸአት 21፥17]
ይህንን ስህተት ማቴዎስ አስተካክሎታል፦
“እግዚአብሔር፦ አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ፦ አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና፤”
📖[ማቴዎስ 15፥4]
ማርቆስ ለምን እግዚአብሔር ያዘዘውን ሙሴ የሚለን?
ማቴዎስ አስታክሎታል
⛳️
ተርቡ አሊ