በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ኤፍራታናግድም ወረዳ አገዛዙ በፈፀመው የድሮን ጥቃት የንፁኃኖች ሕይወት አልፏል!
በሁሉም መስክ ኪሳራ አያስተናገደ ያለው አሸባሪው የብልፅግና አገዛዝ በተለያየ ወቅት የሚፈፅማቸው ንፁኃንን ዒላማ ያደረጉ የድሮን ጥቃቶች በርካታ ሲቪሊያን ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ገደማ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የፋኖ አባላትና አመራሮች ይኖሩበታል በሚል የተሳሳተ ግምት በኤፍራታና ግድም ዘንቦ ቀበሌ በሰነዘረው የድሮን ጥቃት የግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ባደረሰው ጉዳት የንፁኃኖች ህይወት አልፏል።
አገዛዙ በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት እናት ከእነ ልጇ ጨምሮ 4 ሲቪሊያን ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከ20 በላይ የቀንድና የጋማ ከብቶች ላይ ጉዳትና ውድመት አድርሷል።
የአብይ አህመድ አማራ ጠል አገዛዝ በጋራ ታግለን ልናስወግደው የሚገባ ከባዕድ ወራሪ ያልተለየ አረመኔና ጨካኝ አገዛዝ በመሆኑ በተባበረ ክንድ ሁሉም አማራ በተሰለፈበት መስክ ስርዓቱን ለመቅበር የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን።
ክብር ለሰማዕታት
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
የካቲት 1/2017 ዓ.ም
@Showapress