Репост из: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
የሰላምን ንጉሥ ወልዳ የሰጠች ሰላሟ የማይናጋ ደኅንነቷ የማያሰጋ የሰላም ከተማ አማናዊቷ ኢየሩሳሌም ድንግል ማርያም ናት ስለዚህ የንጉሥ ዙፋን በወርቅ በልዩ ልዩ ጌጣጌጥ እና በከበሩ አልባሳት እንደሚያሸበርቅ ሁሉ እመቤታችንም የሰማያዊው ንጉሥ ዙፋን በመሆኗ በውስጥ በአፍአ በነፍስ በሥጋ በቅድስና የተጌጠች በንጽሕና ያሸበረቀች በሕብረ ዜማ የተመሰገነች ዘላለማዊ ድንግል ናትና ።
ድንግል : ሆይ : ባንቺ : ዓለም : ዳነ : በልጅሽም : ሰላም : ሆነ
በረከቷ ይደርብን አማላጅነቷ አይለየን!
ድንግል : ሆይ : ባንቺ : ዓለም : ዳነ : በልጅሽም : ሰላም : ሆነ
በረከቷ ይደርብን አማላጅነቷ አይለየን!