የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ቅዳሜ እና እሁድ በወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ላይ ባደረሱት ጥቃት 17 የቻድ ወታደሮች መግደላቸውን የቻድ ጦር አስታወቀ።
በጥቃቱ ወቅት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 96 የሚሆኑ አማፂያን መገደላቸውንም ጨምሮ ገልጿል።
የጦሩ ቃል አቀባይ ጀነራል ኢሳክ አቼክ እሁድ ምሽት በሀገሪቱ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ÷ በቻድ ሐይቅ ክልል ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ምሽት መሆኑን ተናግረዋል።
የቻድ ሐይቅ አካባቢ በዚህ አመት ከቦኮ ሃራም እና የምዕራብ አፍሪካ እስላማዊ መንግስትን ጨምሮ በአማፂያን ተደጋጋሚ ጥቃቶች ደርሶበታል።
ባለፈው ወር በወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 40 ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ÷ ፕሬዝዳንት ማሃማት ዴቢ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎችን ከቻድ ሐይቅ ለማትፋጥ ዘመቻ አካሂደው ነበር።
የምዕራባውያንን የትምህርት አሰጣጥ በመቃወም ያለፉትን አስር አመታት ትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የቆየው ቦኮ ሃራም÷ በናይጄሪያ በእስላማዊ ሕግ የሚተዳደር መንግስት ማቋቋም ይፈልጋል።
አማፂ ቡድኑ፣ ካሜሩን፣ ኒጀርን እና ቻድን ጨምሮ፣ በምዕራብ አፍሪካ ወደሚገኙ የአፍሪካ አገራትም ተስፋፍቷል።
https://t.me/Tamrinmedia