ዋና አስተዳዳሪው ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሱሉልታ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ የሆኑት አበበ ወርቁ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት መገደላቸው ተሰማ
ታጣቂ ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ከወረዳ አሥተዳዳሪው ጋር የነበረ የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በቡድኑ ታፍኖ መወሰዱን አስረድተዋል።
ዋና አሥተዳዳሪው፣ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊው እና በርካታ የጸጥታ ኃይሎች ታጣቂ ቡድኑ በስፋት ይንቀሳቀስበታል ወደተባለው "ሞዬ ጋጆ" በተባለው ስፍራ ሲደርሱ አማጺ ቡድኑ ድንገተኛ የእሩምታ ተኩስ እንደከፈተባቸው ተጠቁሟል።
ለጊዜው ቁጥራቸውን ማጣራት ያልቻለችው የጸጥታ ኃይሎች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለው ጫንጮ ሆስፒታል መግባታቸውን ምንጮች ተናግረዋል።
ከጸጥታ ዘርፍ ኃላፊው በተጨማሪ በርካታ የጸጥታ ኃይሎች በቡድኑ ታፍነው ተወስደዋል
ከወራት በፊትም በተመሳሳይ በዚሁ ታጣቂ ቡድን ጥቃት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ለገሰ ሥዩም መገደላቸው ይታወሳል።
ሟቹ አበበ ከሁለት ዓመት በፊት የወረዳው ዋና አሥተዳዳሪ ሆነው ከመሾማቸው በፊት፣ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ነበሩ
https://t.me/Tamrinmedia