የግብፅ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርትራ ይገኛሉ
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት ማምሻውን በግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር በድር አብደላቲ የተመራው የግብፅ ልኡካን ቡድን ተቀብለዉ አነጋግረዋል።
ሁለቱ ሀገራት ሰፊ ውይይቶችን አድርገዋል ያሉት የኤርትራ የመረጃ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ሲሆኑ በሁለቱ ሀገራት እንዲሁም በአህጉራዊ - የአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባህር - የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ምክክር አድርገዋል ብለዋል።
ጥልቀት ከተሰጣቸዉ ጉዳዮች ዉስጥም በሶማሊያ የሀገር ግንባታ ላይ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር አካባቢዎች የሰላም እና የደህንነት ፈተናዎች በኤርትራ እና ግብፅ ባለስልጣናት ሰፊ ዉይይት መደረጉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር በድር አብደላቲ ለኤርትራ ዜና አገልግሎት በሰጡት አጭር መግለጫ እንደገለፁት በየወቅቱ የሚደረጉ ምክክሮች በቀጠናዊ ጸጥታና መረጋጋት ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋሞችን ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኤርትራ እና ግብፅ መሪዎች መካከል ከአስመራ ካይሮ የሚደረጉ ጉብኝቶች በርከት ብለዋል። የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደልፋታህ አልሲሲን ጨምሮ በርካታ የግብፅ ባለስልጣናት ወደ ኤርትራ ጉብኝት ሲያደርጉም ተስተዉሏል።
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር በባህር በር ስምምነት ጉዳይ ዉዝግብ ዉስጥ ከገባችበት ጊዜ አንስቶ የግብፅ የምስራቅ አፍሪካ እንቅስቃሴ እየተስተዋለ መጥቷል።
https://t.me/Tamrinmedia