ግዝረተ ኢየሱስ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
21፥22 የዐርሹ ጌታ አሏህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
ፈጣሪ ጾታ የለውም፥ ሴትም ወንድም አይደለም። ፈጣሪ የሴትም የወንድም ሩካቤ ሥጋ የሌለው ሲሆን ወንድ ልጅ ግን ሩካቤ ሥጋ"sex organ" አለው፥ ይህ ሩካቤ ሥጋ"sex organ" ሽንት ለመሽናት እና ከሴት ጋር ተራክቦ"intercourse" ለማድረግ ያገለግላል። ኢየሱስ ከሴት የተወለደ ወንድ ልጅ ነው፦
ሉቃስ 1፥31 እነሆም፥ ትፀንሻለሽ "ወንድ" ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
"ወንድ" የሚለው ቃል የሥጋ መደብ እና አንቀጽ እንደሆነ ልብ አድርግ! እንደሚታወቀው ወንድ ሩካቤ ሥጋው ላይ ያለውን ሸለፈት በስምንተኛ ቀን ይገረዛል፦
ዘፍጥረት 17፥12 የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።
ኢየሱስም ስምንት ቀን ሲሞላው ተገርዟል፥ በማኅፀን ከመረገዙ ማለትም ከመፀነሱ በፊት ስም እንደወጣለት ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ፦
ሉቃስ 2፥21 ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይጸነስ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።
ሮሜ 15፥9 ክርስቶስ ስለ አምላክ እውነት የመገረዝ አገልጋይ ሆነ እላለሁ። λέγω γὰρ Χριστὸν διάκονον γεγενῆσθαι περιτομῆς ὑπὲρ ἀληθείας Θεοῦ,
አምላክ በሥጋ ሊገረዝ ይቅርና ክርስቶስ እራሱ ስለ አምላክ እውነት የተገረዘ አገልጋይ እንደሆነ በመግለጽ በአምላክ እና በክርስቶስ መካከል የምንነት ልዩነት እንዳለ ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። ይህ የተገረዘውን ሕፃን በጌታ ፊት ያቆሙት ዘንድ ዮሴፍ እና ማርያም ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፦
ሉቃስ 2፥24 እንደ ሙሴም ሕግ የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥ በጌታ ሕግ፦ የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ተብሎ እንደ ተጻፈ "በጌታ ፊት ሊያቆሙት፥ በጌታም ሕግ፦ ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት"።
የሁሉ ጌታ እና ሕፃኑ ሁለት የተለያዩ ኑባሬ እንደሆኑ አያችሁን? ፈጣሪ ፆታ ኖሮት፣ ወንድ ሆኖ፣ ተገርዞ፣ ሕፃን ሆኖ በጌታ ፊት ሊያቆሙት ሲወስዱት አስቡት! የተገረዘው ወንድን ልጅ ወደ ጌታ አምላክ ከወሰዱት ዘንዳ የተገረዘው ወንድ ልጅ እንጂ ጌታ አምላክ አይደለም።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥር 6 ቀን በዓመት አንዴ "ግዝረተ ኢየሱስ" ተብሎ የተገዘረበትን ዓመታዊ ክብረ በዓል ትዘክራለች፥ "ግዝረት" ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን "ግርዘት"circumcision" ማለት ነው፥ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ስለ ኢየሱስ መገረዝ እንዲህ ይለናል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 70 ቁጥር 24
"ሰውም እንደ መሆኑ ለሥጋ እንደሚገባ ተገዘረ"።
ኢየሱስ መገረዙን ከተረዳን ዘንዳ ይህ ተቆርጦ የተገዘረው ሸለፈት ሥጋ አምላክ እንደሆነ እራሱ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ እና አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ ይናገራሉ፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 78 ቁጥር 31
"ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ ሥጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን"።
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 29 ቁጥር 19
"ከእመቤታችን ከቅድስት ከድንግል ማርያም የነሳው ይህ ሥጋም እውነተኛ የባሕርይ አምላክ ነው"።
ተቆርጦ የተገረዘው ሸለፈታዊ ሥጋ እውነተኛ የባሕርይ አምላክ ተሸልቶ አፈር ሆኖ ታመልኩታላችሁን? "ያ ፍጥረትን የፈጠረውን አሏህን ማርያም የወለደችው ወንድ ልጅ ነው" ብለው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ የዐርሹ ጌታ አላም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦
5፥17 እነዚያ "አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ
21፥22 *የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ*። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
"ከሚሉት" ለሚለው ቃል የገባው "የሲፉን" يَصِفُون ሲሆን "ባሕርይ ካደረጉለት"They attribute” ማለት ነው። አምላካችን አሏህ አባጣ እና ጎርባጣ ከሆነ የሺርክ ሕይወት አውጥቶ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም