"የተፀነሰው" ለሚለው የገባው ቃል "ጌኔቴን" γεννηθὲν ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ጌናኦ" γεννάω ነው፥ የቀጥታ ትርጉም የሚባሉት "Literal Standard Version" እና "Young's Literal Translation" በግልጽ "የተወለደው"begotten" ብለው አስቀምጠውታል። "የተወለደው" ከመንፈስ ቅዱስ አሠራር ነው፥ የአምላክ እስትንፋስ የልዑል ኃይል ሲሆን ወደ ማርያም የመጣበት ምክንያት ይህ ፅንስ ሕይወት እንዲያገኝ ነው፦
ሉቃስ 1፥35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል። καὶ ἀποκριθεὶς ὁ ἄγγελος εἶπεν αὐτῇ Πνεῦμα Ἅγιον ἐπελεύσεται ἐπὶ σέ, καὶ δύναμις Ὑψίστου ἐπισκιάσει σοι·
"መጸለል" ማለት "መጋረድ" ማለት ሲሆን የልዑል ኃይል መንፈስ ቅዱስ ዮሴፍ ቅር ብሎት በስውር ሊተዋት ሲያስብ ከነቄፌታ ጋርዷታል፦
ሉቃስ 1፥35 ስለዚህ "ከ-አንቺ" የሚወለደው ቅዱስ የአምላክ ልጅ ይባላል። διὸ καὶ τὸ γεννώμενον ἅγιον κληθήσεται Υἱὸς Θεοῦ.
"የሚወለደው" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ጌኖሜኖን" γεννώμενον ሲሆን "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "ሆነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "የሚሆነው” ማለት ነው። "ከ" የሚለው መስተዋድድ "አንቺ" በሚለው ቃል ላይ መነሻ ሆኖ መግባቱ በራሱ ኢየሱስ ከማርያም መገኘቱን ያሳያል፥ በተጨማሪ "ዲኦ" διὸ ማለት "ስለዚህ"therefore" ማለት ሲሆን ከእርሷ የተገኘው ልጅ የአምላክ እስትንፋስ መንፈስ ቅዱስ ወደ ማርያም በመምጣቱ ምክንያት ነው። አምላክ መንፈሱን ሲልክ ፍጡራን ይፈጠራሉ፦
መዝሙር 104፥30 መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም።
ስለዚህ ወልድ ከአብ ሕይወትን ከተቀበለ ሕይወት አልባ እና በባዶነት የተቀደመ ነው፥ ሕይወት ሳይሰጠው በፊት ህልውና የለውም። ሕይወት ከተቀበለ ደግሞ መነሾ እና ጅማሮ አለው፥ መነሾ እና ጅማሮ ያለው ማንነት ሆነ ምንነት ፍጡር ነው፦
ኢዮብ 31፥15 እኔን በማኅፀን የፈጠረ እርሱንስ የፈጠረው አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ የሠራን አንድ አይደለንምን? πότερον οὐχ ὡς καὶ ἐγὼ ἐγενόμην ἐν γαστρί, καὶ ἐκεῖνοι γεγόνασι; γεγόναμεν δὲ ἐν τῇ αὐτῇ κοιλίᾳ.
እዚህ አንቀጽ ላይ "የፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤግኖሚን" ἐγενόμην ሲሆን ማኅፀን ውስጥ ሁሉንም ሰው በእስትንፋሱ የሚፈጥር አንድ ፈጣሪ ስለሆነ አብ ወልድን በመንፈስ ቅዱስ ፈጠረ፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 68 ቁጥር 43
"እግዚአብሔር ሕያው አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ሥጋን ፈጠረ"
ይህ በማኅፀን ውስጥ የተፈጠረ ፍጡር ከድንግል የተወለደ፣ ወደ ፊት የሚሞት እና በትንሣኤ ቀን የሚቀሰቀስ ነው፦
19፥33 «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን፡፡» وَالسَّلَامُ عَلَيَّ يَوْمَ وُلِدتُّ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا
ኢየሱስን በማኅፀን የፈጠረውን አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያች ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም