ጌታ ነኝ?
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
6፥164 በላቸው «እርሱ አሏህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ከአሏህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጂ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا
"ረብ" رَبّ ማለት "ጌታ" "አስተናባሪ" "ባለቤት" ማለት ሲሆን ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ አንድ ጌታ አምላክ ነው፦
ማርቆስ 12፥29 እስራኤል ሆይ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው። اسْمَعْ يَا إِسْرَائِيلُ. الرَّبُّ إِلَهُنَا رَبٌّ وَاحِدٌ.
በዐረቢኛው ባይብል እዚህ አንቀጽ ላይ "ጌታ" ለሚለው የገባው ቃል "ረብ" رَبّ እንደሆነ ልብ አድርግ! ነገር ግን ኢየሱስ ለሐዋርያቱ "እንዲሁ ነኝና" ብሎ ለመለሰበት የገባው ቃል "ረብ" رَبّ ሳይሆን "ሠይድ" سَيِّد ነው፦
ዮሐንስ 13፥13 እናንተ መምህር እና ጌታ ትሉኛላችሁ፥ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። أَنْتُمْ تَدْعُونَنِي مُعَلِّماً وَسَيِّداً وَحَسَناً تَقُولُونَ لأَنِّي أَنَا كَذَلِكَ
እዚህ አንቀጽ ላይ ሐዋርያት "ጌታ" ላሉት የገባው ቃል "ሠይድ" سَيِّد እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ሠይድ" سَيِّد በስም መደብ "አለቃ" "አውራ" "ራስ" "የበላይ" "ጌታ" ማለት ነው፥ "ሠይድ" سَيِّد በቅጽል መደብ "ለዘብተኛ" "ደግ" "ንዑድ" "ስቡት" "ሕሩይ" "ጥበበኛ" ማለት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ "እንዲሁ ነኝና" ያለው ሐዋርያት "ሠይድ" سَيِّد ስላሉት እንጂ "ረብ" رَبّ ስላሉት አይደለም፥ "እኔ ጌታ ነኝ" ማለትማ ተወዳጁ ነቢያችንም"ﷺ"፦ "እኔ በትንሣኤ ቀን የሰዎች ጌታ ነኝ" ብለዋል፦
ሢልሢለቱ አስ ሶሒሕ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 100
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "እኔ በትንሣኤ ቀን የሰዎች ጌታ ነኝ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ أنا سَيِّدُ الناس يوم القيامة
ቅሉ እና ጥቅሉ እዚህ ሐዲስ ላይ "ጌታ" ለሚለው የገባው ቃል "ሠይድ" سَيِّد እንጂ "ረብ" رَبّ አይደለም፥ ነቢዩላህ የሕያ "ሠይድ" سَيِّد ተብሎአል፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት፦ «አሏህ በየሕያ ከአሏህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታ፣ ድንግል እና ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል» በማለት ጠሩት። فَنَادَتْهُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَهُوَ قَآئِمٌۭ يُصَلِّى فِى ٱلْمِحْرَابِ أَنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًۢا بِكَلِمَةٍۢ مِّنَ ٱللَّهِ وَسَيِّدًۭا وَحَصُورًۭا وَنَبِيًّۭا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
የትንሣኤ ቀን ሰዎች አሏህን "ጌታችን" ሲሉ እና መሪዎቻቸው "ጌቶቻችን" ሲሉ ይለያያል፦
33፥67 ይላሉም "ጌታችን" ሆይ! እኛ "ጌቶቻችንን" እና ታላላቆቻችንን ታዘዝን፡፡ መንገዱንም አሳሳቱን። وَقَالُوا۟ رَبَّنَآ إِنَّآ أَطَعْنَا سَادَتَنَا وَكُبَرَآءَنَا فَأَضَلُّونَا ٱلسَّبِيلَا۠
ልብ አድርጉ! ሰዎቹ የትንሳኤ ቀን ሰዎችን “ሣደተና” سَادَتَنَا ሲሉ አሏህን ግን “ረበና” رَبَّنَا ብለው ተጠቅመዋል። በኢሥላም ሸሪዓህ "ሠይዲ" سَيِّدِي አክብሮትን ለማሳየት ለሰዎች ብንጠቀምበትም "ረቢ" رَبِّي ማለት ግን አይቻልም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 40, ሐዲስ 14
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከእናንተ መካከል ማንም ባሪያዬ አይበል፥ ሁላችሁም የአሏህ ባሮች ናችሁ። ነገር ግን ሎሌዬ ይበል! "ረቢ" አይበል አይበል፥ ነገር ግን "ሠይዲ" ይበል። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " لاَ يَقُولَنَّ أَحَدُكُمْ عَبْدِي . فَكُلُّكُمْ عَبِيدُ اللَّهِ وَلَكِنْ لِيَقُلْ فَتَاىَ . وَلاَ يَقُلِ الْعَبْدُ رَبِّي . وَلَكِنْ لِيَقُلْ سَيِّدِي " .
አምላካችን አሏህ የሁሉ ነገር ረብ ሲሆን ከአሏህ በቀር ሌላን ረብ እፈልጋለሁን? እረ በፍጹም፦

ሥሉሳውያን ክርስቲያኖች ሆይ! ኢየሱስ እራሱ "ጌታ ፈጠረኝ" የሚለው ጌታውን፣ "ጌታዬ" የሚለው ጌታውን፣ ጌታው ኢየሱስን "ባሪያዬ" የሚለውን፣ ጌታው ኢየሱስ በማዕረግ ጌታ ያደረገውን አንዱን ጌታ አምላክ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም