Репост из: የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
ዕውቀት እና የዕውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል - 4
በምድረ ገጽ ከሰዎች ሁሉ በላጮቹ እውቀትን ሳይደብቁ ለህብረተሰቡ ይፋ የሚያደርጉ ኡለሞች ሲሆኑ በዚህ ላይ ተቀዳሚዎቹ ሩሱሎችና ነብያቶች ናቸው። እነርሱ የዳእዋው ፣ የኢልሙ ሁሉ መሰረቶች ናቸው። ከእነርሱ ቀጥሎ የሸሪዓ ፣ የቁርዓን ፣ የሐዲስ እውቀት ባለቤቶች ናቸው።
ማንኛውም በአላህና በስሞቹ አዋቂ ፤ በተግባር እና በዳእዋው የተሟላ በሆነ ቁጥር ወደ ሩሱሎች የቀረበ ፣ የተጠጋ ይሆናል - በጀነት ባለው ደረጃም እንዲሁ።
የእውቀት ባለቤቶች የዚህች ምድር ብርሃኖችና መብራቶች ናቸው ፤ ሰዎችን ስኬት ወደሚያገኙበት አቅጣጫ ይመራሉ ፤ ከእሳት ነጻ መውጫ መንገዱን ያሳያሉ ፤ የአላህ ውዴታ ፣ ልቅና እና ክብር የሚገኝበትን ፍኖት ይጠቁማሉ ፤ ከቅጣት እና ከቁጣው የሚያርቁ ሰበቦችን ያመላክታሉ፡፡
ኡለሞች የነብያት ወራሽ ናቸው። ከነብያት በኋላ የማህበረሰቡ መሪዎች እነርሱ ናቸው። ወደአላህ መንገድ ይመራሉ ፤ ለሰዎች ዲናቸውን ያስተምራሉ፤ ባህሪያቸው ታላቅ ፤ መገለጫቸው ምስጉን ነው። ሀቀኛ አሊሞች ፤ ቅን ፤ የሩሱሎች ምክትል ፤ አላህን የሚፈሩ ፤ የእርሱን ትእዛዝ እና ክልከላ ክብር የሚሰጡ ናቸው።
የሸሪዓ ኡለሞች ስነምግባራቸው የላቀ ነው - ምክንያቱም ሩሱሎች የተጓዙበትን መንገድ አንድ በአንድ የተከተሉ በመሆናቸው። ወደአላህ በሚደረገው ዳዕዋ እውቀትን መሰረት በማድረጋቸው ፤ የቁጣ ምክንያቶችን በማስጠንቀቃቸው።
ኡለሞች በንግግርም ይሁን በተግባር የሚያውቁትን ሐቅ ለህብረተሰብ ለማስተላለፍ ችኩል ናቸው። በንግግርም ይሁን በተግባር ከሚያውቁት ሸር ቀድመው ይርቃሉ።
ከነብያት በኋላ በታላቅ ስነምግባራቸው፤ ምስጉን በሆነው መገለጫቸው፤ በታላላቅ ተግባራቶቻቸው፤ ለመልካም ሞዴሎቻችን እነርሱ ናቸው።
ማንኛውንም በተግባር ፈጽመው ያሳያሉ ፣ ወደከፍተኛ ስነምግባር እና የመልካም መንገዶች ለተማሪዎቻቸው አቅጣጫ ይሰጣሉ።
እውቀት ማለት አላህ የተናገረው ፣ ረሱል የተናገሩት መሆኑን ከዚህ በፊት አሳልፈናል። ሸሪዓዊ እውቀት ማለት በአላህ ኪታብ እና በረሱል ﷺ ሱና ማወቅ ማለት ነው ፤ ወደእርሱ የሚያግዙም እውቀቶች እንዲሁ።
በእውቀት ባለቤቶች ላይ ግዴታው ይህን ታላቅ መሰረት አጥብቀው መያዝ ፣ ሰውን ወደርሱ መጥራት፤ አላማቸው አላህ የተናገረውን ረሱል ﷺ የተናገሩትን መናገር ፣ በእርሱም መተግበር ሊሆን ይገባል።
በሐቅ ላይ መለያየት እና መከፋፈል አይፈቀድም፤ ጥሪያችን ወደተለያዩ አንጃዎች ሊሆን አይገባም። ጥሪያችን ወደአላህና ወደረሱል መሆን አለበት። ዳእዋችን ወደእከሌ መዝሀብ ወይም ወደእከሌ ዳእዋ ወይም ወደእከሌ ቡድን ወይም ወደእከሌ አስተያየት መሆን የለበትም፡፡ የሙስሊሞች ጥሪ አንድና አንድ ነው። እርሱም በሰለፎች ግንዛቤ መሰረት ወደ ተወሂድና ወደ ሱና ነው፡፡
በአራቱ መዝሀቦችም ይሁን በሌሎች የተከሰተው የኡለማ ውዝግብ ፤ ወደሀቅ ቀረብ ያለውን መያዝ ግዴታ ነው። አላህ ወደተናገረው ወይም ረሱል ወደተናገሩት ቀረብ ያለውን ወይም ለሸሪዓው ህጎች ቀረብ ያለውን መያዝ ግድ ነው፡፡
ሙጅተሂድ የሆኑ የሸሪዓ መሪዎች ከዚህ የተለየ አላማ የላቸውም። ከረሱል በኋላ የነበሩት ሶሃቦች በአላህ ጉዳይ ከሰዎች ሁሉ አዋቂዎች ነበሩ። በእውቀትም በላጭ ፣ በስነምግባርም የተሟሉ ነበሩ። በአንዳንድ ቅርንጫፋዊ የዲን ጉዳዩች በግንዛቤ ቢለያዩም ዳእዋቸው፣ አቂዳቸው ፣ መንሀጃቸው አንድ ነበር ፤ ወደአላህ ኪታብ ወደረሱ ሱና ጥሪ ያደርጋሉ ፣ ከእነርሱ በኋላ የመጡት ታብእዮች ፣ አትባኡ ታብእይም እንዲሁ።
ኢማም ማሊክ፤ አቡሀኒፋ ፤ ሻፍኢያ፤ አህመድ እና ሌሎቸም የቅን መሪዎች ፤ አውዛኢይ ፣ ሰውርይ፣ ኢብን ኡየይናህ፣ ኢስሀቅ ብን ራህዊያ፣ እና የመሳሰሉ የኢልም እና የኢማን ባለቤቶች ፤ ዳእዋቸው መንሀጃቸው አቂዳቸው አንድ ነበር። እርሱም ወደአላህ ኪታብ ወደ ረሱል ሱና መጣራት ነው። ተከታዮቻቸውን ከጭፍን ተከታይነት አጥብቀው ይከለክሉ ነበር፤ 'እኛ ከያዝንበት ያዙ' ይሏቸው ነበር። ማለትም 'ከአላህ ኪታብ እና ከረሱል ሱና ያዙ' ይሏቸው ነበር፡፡
ሀቅን ያላወቀ ጃሂል በእውቀትና በደረጃ የሚበልጡ ፣ በመልካም አቂዳቸው የሚታወቁ አሊሞችን ይጠይቅ። ይህ ሲባል ለኡለሞች ክብር ከመስጠት ፣ ደረጃቸውን ከማወቅ ጋር መሆን አለበት። አላህ ተውፊቁን እንዲሰጣቸው ፣ አጅራቸውን ከፍ እንዲያደርግላቸው ዱዓ ከማድረግ ጋር መሆን አለበት። ምክንያቱም በመልካም ተግባርና በደረጃ ቀድመውናል፤ ህብረተሰብን ወደ ጀነት ጎዳና አቅጣጫ ሰጠዋል፤ ትክክለኛውን መንገድ ግልጽ አርገዋል።
ትክክለኛ የሸሪዓ ኡለሞች ሶሃቦችም ይሁኑ ከእነርሱ በኋላ የመጡ የእውቀት እና የኢማን ባለቤቶችን ክብር እና ደረጃ ጠንቅቀው ያውቃሉ። በእነርሱም ላይ አላህ ይዘንላቸው ይላሉ ፤ እነርሱንም በመልካሙ ይከተላሉ ፣ ወደአላህ በሚደረገው ዳዕዋም አላህ የተናገረውን ረሱል ﷺ የተናገሩትንም ከሌላው ያስቀድማሉ። በዚህም ላይ ይታገሳሉ።
እኛም ወደመልካም ስራ መቻኮል ፣ በዚህ ታላቅ ደረጃቸው መከተል፤ ለቀደሙ የሱና ኡለሞች አላህ ይዘንላቸው ብለን ዱአ ማድረግ ይኖርብናል።
ከረሱል ውጭ ማንኛውም አካል ከስህተት የጸዳ አይደለም። ከኡለሞቻችን ትክክሉን እንወስዳለን ፣ ስህተቱን እንጥላለን። የኡለሞቻችንን ክብር ከመጠበቅ ጋር። ጭፍን ተከታይነት አይፈቀድም። ልዩነት ከተፈጠረ ወደአላህ ኪታብ እና ወደረሱል ﷺ ሱና መመለስ ይገባል።
አላህ ﷻ የሚከተለውን ተናግሯል፡
"فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا"
"በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡"
(ኒሳእ:59)
وَمَا اخْتَلَفْتُمْ فِيهِ مِن شَيْءٍ فَحُكْمُهُ إِلَى اللَّهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبِّي عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ
"ከምንም ነገር ያ በእርሱ የተለያዩበት ፍርዱ ወደ አላህ ነው፡፡ «እርሱ አላህ ጌታዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ፣ ወደርሱም እመለሳለሁ» (በላቸው)፡፡"
(ሹራ:10)
ድሮም ይሁን አሁን የእውቀት ባለቤቶች የተናገሩት ይህ ነው፡፡
ለዘይድ ወይም ለአምር ወይም ለእከሌ ለእከሌ አስተያየት ወይም ለእከሌ ቡድን ወይም ለእኬለ መዝሀብ ወይም ለእከሌ ጀማዓ ተጎታች መሆን የለብንም፤ ይህ አብዛኛው ሰው የወደቀበት ስህተት ነው፤ ወገንተኝነታችን ለቁርአን ለሐዲስ ሊሆን ይገባል ፣ ወገንተኝነታችን ለሰለፎች ጎዳና ሊሆን ይገባል ፣ ከቁርአን ከሐዲስ ውጭ ከሆነ ወርውረን እንጥለዋለን። ሙብተዲዖችን ልንርቅ ይገባል። ሁልጊዜ ቁርኝታችን ከሰለፍይ ወንድሞቻችን ጋር ሊሆን ይገባል።
የሙስሊሞች አላማ አንድና አንድ ነው። እርሱም የአላህን ኪታብ ፣ የረሱል ﷺ ሱናን አጥብቆ መከተል ነው። ደስ ባለን ጊዜም ይሁን በተቸገርን ጊዜ ፤ በሰፈርም ይሁን በከተማ ፤ በሁሉም ሁኔታ ቁርአንን እና ሱናን ልንከተል ይገባል።
ኡለሞች በሀሳብ ሲለያዩ ንግግራቸው ይታያል ለአንድም ተጎታች ሳንሆን ከደሊል ጋር መጓዝ አለብን፤