اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ
﷽
الحَمدُ لله رَبِ العَالَمِين
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
قَالَ #عُمَر بن خَطّٰب رَضِيَ الله تَعَالَی عنه
ﻧﺤﻦ ﻗﻮﻡ ﺃﻋﺰﻧﺎ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﺎﻹﺳﻼﻡ فمهما ﺍﺑﺘﻐﻴﻨﺎ ﺍﻟﻌﺰﺓ ﺑﻐﻴﺮﻩ ﺃﺫﻟﻨﺎ الله
*ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ መልካም ስራውን አላህ ይውደድለት እና እንዲህ አለ *
⬇️እኛ አላህ በእስልምና ያከበረን( ያላቀን) ህዝቦች ነን
⬇️ከእስልምና ውጪ መክበርን( መላቅን) ብንፈልግ አላህ ያዋርደናል ፡፡
👌የትኛውም ኢስላም ለኛ የደነገገው ለኛ ክብር እንጂ በፍፁም ውርደት አይደለም
👌ፂም ማሳደግ ክብር ነው መዋረድ መስሎህ ለመላጨት ብትሞክር የተዋረድከው የዛኔ ነው
👌ሱሪ ማሳጠርም እንደዛው .. የትኛውም አላህ እና መልዕክተኛው ያዘዙበት ነገር ለኛ ክብር ነው ልቅና ነው ከእነሱ ትእዛዝ ብናፈነግጥ ወላሂ ውርደትን ነው የምንከናነበው ° ሰሃቦችም የበላይነት ያገኙት የአላህን እና የመልዕክተኛውን ትዕዛዝ አጥብቀው ስለያዙ ነው ፡፡
👌አንቺም ቢሆን እህቴ መከናነብ ኒቃብ መልበስ ወላሂ ላንቺ ክብር እንጂ ውርደት አይደለም ° ከተለያዩ ችግሮች ይጠብቅሻል !!
🚆 ዘምነናል የሚሉትን አትስሚያቸው ፡፡ የነሱ ሴቶች ምንድነው የሚመስሉት ለአንቺ በሁለቱም አለም የሚያከብርሽ እስልምናሽ ነው !!
🗞ከፊሎች እንደሚሉት ኢስላም የሴቶች ክብር አይጠብቅም ፤ ዘመናዊነት ነው የሚያዋጣው፤ ጅልባብ ያጨናንቀኛል ወዘተ ብትይ በአኼራም በአዱንያም ጭንቀት ያገኝሻል፡፡
🗞በየትኛው ሀገር በየትኛውም ክፍለ ዘመን ሰዎች መጥተው ዘመንን ቢሉ እስልምና ከእነሱ እጥፍ እጥፍ በላይ የዘመነ ነው፡፡
🗞ኢስላማዊ ልብስ ላንቺ እስከመጨረሻው መዳኛሽ ነው ዋስትናሽ ነው ስለዚህ አደራ!!
ከእስልምና ውጪ መክበርን መላቅን ብትፈልጊ አንቺንም የሚጠብቅሽ ውርደት ነው
ይህ ከዑመር ንግግር የምንቀስመው ታላቅ ት/ት ነው
#⃣ውርደት እና ክብር ቢስነት ትዕዛዜን በጣሰ አካል ላይ ሆነች (ሙሀመድ ﷺ)
✍አቡ ያስር_አብዱልፈታህ
⤵️⤵️
https://t.me/abdul_fettahhttps://t.me/abdul_fettah