Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
“አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው”ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 43ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።
ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው። በዚህ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ማምጣት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡
ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት ቅዱስ ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነውን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይገባናል ብለዋል።
በዛሬው ዕለት የተጀመረው 43ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት እንዲሁም ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።
#ድምፀ_ተዋህዶ