በደርባ ከተማ ከታቦት ማደርያ ላይ የደብር አስተዳዳሪ እና ሁለት ሚሊሺያዎች ተወስደው ተገደሉ
በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል ከጫንጮ ከተማ 20 ኪ/ሜ ገደማ ርቀት ላይ በሚገኘው በተለምዶ 'ደርባ ሲሚንቶ' ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ታጣቂዎች ከታቦት ማደርያ ላይ አንድ የደብር አስተዳዳሪ እና ሁለት ሚሊሺያዎችን ወስደው መግደላቸው ታውቋል።
መሠረት ሚድያ ዛሬ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው ታጣቂዎቹ ከግድያው በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሰዎችንም አግተው ይዘው ሄደዋል።
"ግድያ የተፈፀመባቸው የደርባ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ናቸው" ብለው ለሚድያችን የተናገሩት አንድ የአካባቢው ነዋሪ ሁኔታው የፈጠረው ድንጋጤ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
መሠረት ሚድያ በስልክ ያናገራቸው አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የአካባቢው ባለስልጣን "ድርጊቱን የፈፀመው ሸኔ ነው፣ ሶስት ሰው ገድሎ ስምንት ሌላ ሰው ይዞ ጫካ ገብቷል" በማለት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ዙርያ ባለው የሸገር ከተማ እንዲሁም በሰሜን ሸዋ (ሰላሌ) አካባቢዎች ታጣቂዎች በርካታ ጥቃቶችን እየፈፀሙ እንደሚገኙ ይታወቃል፣ በዚህ መሀል በርካታ ንፁሀን ዜጎችም ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ።
የመንግስት ሚድያዎች በተለይ የመንግስት አመራሮች ላይ በታጣቂዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች እንዳይዘግቡ ጥብቅ መመርያ እንደተላለፈላቸው ከሰሞኑ የደረሰን ተጨማሪ መረጃ ያሳያል።
Photo: File
@MeseretMedia