Репост из: Ibn Yahya Ahmed
▪️#እናትን_መሳደብ
🔻ወንድሜ ሆይ! የወለደችህን እናትህን ከመሳደብ ተቆጠብ!! እስኪ ቆም ብለህ አስብ .. ከሷ ሆድ ወጥተህ እሷኑ መስደብ ትንሽ አይሰቀጥጥምን? ምናልባት እናትህን በቀጥታ ለመሳደብ ድፍረቱ ላይኖርህ ይችላል ግን የሌላን ሰው እናት ልክ በአሁኑ ጊዜ ከልጅ እስከ ሽማግሌው ተንሰራፍቶ እንደምንሰማው እናትህ እንዲህ ትሁን ስትል በተዘዋዋሪ እናትህን እየተሳደብክ መሆኑን ልታውቅ ይገባል።
°
🔻እንዴት? እኔኮ የሌላን ሰው እናት ነው እንጂ የኔን እናት አልተሳደብኩም ካልከኝማ መልሴ እንደሚከተለው ነው። ነብያችን - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ አንድ ሰው ወላጆቹን መሳደቡ ከትላልቅ ወንጀሎች ነው። ] በዚህን ጊዜ ሶሓቦቹ ገርሟቸው የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! እንዴት አንድ ሰው ወላጆቹን ይሰድባል አሏቸው። እሳቸውም ፦ [ የአንድን ሰው አባት ይሰድባል በዚህ ምክንያት ሌላኛው አባቱን ይሳደባል ፤ የአንድን ሰው እናት ይሰድባል እናም በዚህ ምክንያት ሌላኛው እናቱን ይሰድባል። ] በማለት መለሱላቸው። (ቡኻሪ እና ሙስሊም ላይ ተዘግቧል)። እናም ወንድሜ ሆይ! አውቀህም ይሁን ሳታውቅ እናትህን ከመሳደብ ተጠንቀቅ!!
___
✍ኢብን የሕያ አሕመድ
ረቢዐልአወል 14/1442ሂ. # ጥቅምት 21/2013.
~~~
📣ጆይን ፦ https://t.me/ibnyahya777
✅ላይክ ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya7777