እውቀት ብርሃን ነው!


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


t.me/ binhalal

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የፀጉር ማሽን የሚፈልግ በተመጣጣኝ ዋጋ ያናግሩን t.me/ binhalal


Репост из: ሙዘሚል ሙሳ


+251991832619


በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን ይዘዙን




↪️እጅግ አሪፍ የሆነ Airpods pro...
↪️አንዴ ቻርጅ ከተደረገ ለብዙ ሰዓታት መቆየት የሚችል
↪️ለጆሮ ተስማሚ የሆነ
↪️ማስቀመጫው ልክ እንደ ፓወር ባንክ የሚያገለግል ማለትም ማስቀመጫው ላይ ሲደረግ ቻርጅ ያደርጋል
↪️እጅግ አሪፍ በሆነ ዋጋ አሁኑኑ ያናግሩን


Репост из: Ibn Yahya Ahmed
▪️#እናትን_መሳደብ

🔻ወንድሜ ሆይ! የወለደችህን እናትህን ከመሳደብ ተቆጠብ!! እስኪ ቆም ብለህ አስብ .. ከሷ ሆድ ወጥተህ እሷኑ መስደብ ትንሽ አይሰቀጥጥምን? ምናልባት እናትህን በቀጥታ ለመሳደብ ድፍረቱ ላይኖርህ ይችላል ግን የሌላን ሰው እናት ልክ በአሁኑ ጊዜ ከልጅ እስከ ሽማግሌው ተንሰራፍቶ እንደምንሰማው እናትህ እንዲህ ትሁን ስትል በተዘዋዋሪ እናትህን እየተሳደብክ መሆኑን ልታውቅ ይገባል።
°
🔻እንዴት? እኔኮ የሌላን ሰው እናት ነው እንጂ የኔን እናት አልተሳደብኩም ካልከኝማ መልሴ እንደሚከተለው ነው። ነብያችን - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ አንድ ሰው ወላጆቹን መሳደቡ ከትላልቅ ወንጀሎች ነው። ] በዚህን ጊዜ ሶሓቦቹ ገርሟቸው የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! እንዴት አንድ ሰው ወላጆቹን ይሰድባል አሏቸው። እሳቸውም ፦ [ የአንድን ሰው አባት ይሰድባል በዚህ ምክንያት ሌላኛው አባቱን ይሳደባል ፤ የአንድን ሰው እናት ይሰድባል እናም በዚህ ምክንያት ሌላኛው እናቱን ይሰድባል። ] በማለት መለሱላቸው። (ቡኻሪ እና ሙስሊም ላይ ተዘግቧል)። እናም ወንድሜ ሆይ! አውቀህም ይሁን ሳታውቅ እናትህን ከመሳደብ ተጠንቀቅ!!
___
✍ኢብን የሕያ አሕመድ
ረቢዐልአወል 14/1442ሂ. # ጥቅምት 21/2013.
~~~
📣ጆይን ፦ https://t.me/ibnyahya777
✅ላይክ ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya7777


🔻ለማግባት ብለው የሚሰልሙ ወንዶችን መጠንቀቅ እንደሚገባ ኡስታዝ አሕመድ አደም ለእህቶቻችን ያስተላለፈው አጭር ምክር

ከዛዱል መዓድ ፈታዋ ቁ.70 ላይ የተወሰደ
t.me/ibnyahya7


Репост из: 2️⃣ ዲን መመካከር ነው ቂርአት ብቻ 2️⃣
📋ማስታወቂያ
°
🔻በኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ ተቀርተው የተጠናቀቁ ደርሶችን ለማግኘች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ።
°
1.ኡሱሉ-ሲትተህ
https://t.me/ibnyahya77/11

2.ሹሩጡ-ሰላቲ ወአርካኑሃ ወዋጂባቱሃ
https://t.me/ibnyahya77/23

3.ረካኢዙል ዐሸራ ሊተሕሲሊልዒልሚ
https://t.me/ibnyahya77/29

4.ቀዋዒዱል አርበዓህ
https://t.me/ibnyahya77/33

5.መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን
https://t.me/ibnyahya77/543

6.መዝሀቡ ሸይኺል ኢስላም ፊልሓጅር
https://t.me/ibnyahya77/223

7.ኹዝ ዓቂደተክ
https://t.me/ibnyahya77/262

8.ሲፈቱ-ሰላት ሊብኒ ዑሰይሚን
https://t.me/ibnyahya77/323

9.ኡሱሉ-ሰላሰህ
https://t.me/ibnyahya77/345

10.ሪፍቀን አህለስ-ሱንናህ
https://t.me/ibnyahya77/362

11.አጅዊበቱል ሙፊዳህ
https://t.me/ibnyahya77/395

12.አድዱሩሱል ሙሂማህ
https://t.me/ibnyahya77/418

13.ሙኽተሰሩ ዐቂደቲ አህሊስ-ሱንናህ
https://t.me/ibnyahya77/439

14.መካሪሙል አኽላቅ
https://t.me/ibnyahya77/452

15.ከሽፉ-ሹቡሃት
https://t.me/ibnyahya77/470

16.ሓኢያህ ሊብኒአቢዳውድ
https://t.me/ibnyahya77/483
__
©ዲን መመካከር ነው ቂርአት ብቻ
https://t.me/ibnyahya77


Репост из: Ibn Yahya Ahmed
▪️ቻናል ማስታወቂያ ቁ.6

🔻በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ የተሰጡ የበፊት እና አዳዲስ የተለያዩ የድምፅ ስብስቦችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ።
https://t.me/yeilyaswedaje


▪️የቁርአን ትርጉም ላይ የ"ኢስተዋ" ትርጉም ስህተት ~ አጫጭር ፈትዋዎች

🔻ከዛዱል መዓድ ፈታዋ ቁ.103 ላይ የ1ኛው ጥያቄ መልስ

➠ጥያቄ ፦ 1.የቁርኣን ተፍሲር በአማርኛ የተተረጎመውን ስናነብ አሏህ ከዐርሽ በላይ ነው የሚለውን ሲፈስሩ አላህ በዐርሹ ላይ ስልጣኑ ተደላደለ ብሎ ተፈስሯል። ይህ እንዴት ይታያል? ያብራረሩልኝ?
°
👤በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
___
©ዲን መመካከር ነው - الدين النصيحة
https://telegram.me/ibnyahya7


Репост из: Ibn Yahya Ahmed
▪️ቻናል ማስታወቂያ 5.

🔻ሪያዱ-ሷሊሒን ኪታብ መቅራት የምትፈልጉ እንዲሁም ሌሎች በኡስታዝ ዳውድ ያሲን የሚሰጡ ጠቃሚ ትምህርቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ።
👇👇
https://telegram.me/dawudyassin


Репост из: Ibn Yahya Ahmed
▪️#በስሕተት_ያለቂብላ_መስገድ

➠ ጥያቄ ፦

6.ሶላት ስሰግድ ቂብላ በትክክል ካልሆነ ሶላት ማቋረጥ አለብኝ ወይ?

➠ መልስ ፦

🔻መጀመሪያ በግዴለሽነት ዝምብሎ ከሆነ ሶላቱን የጀመረው እና ኋላ ላይ ትክክል አለመሆኑን ካወቀ አው! ወጥቶ እንደገና መግባት አለበት። መጀመሪያ ሶላቱን ሲጀምር ሳያጣራ ሳይጠይቅ በግዴለሽነት ዝምብሎ ከጀመረው በኋላ ቂብላ አለመሆኑን ካወቀ አዎ! ሶላቱን አቋርጦ ወደቂብላ ዞሮ ይጀምራል። ነገር ግን መጀመሪያ ጥረት አደረገ ፣ ጠየቀ ፣ የሚችለውን ሁሉ አድርጎ ቂብላ ወደዚህ ነው ብሎ ሶላት ከጀመረ በኋላ ትክክል አለመሆኑ ቢነገረው ወይም ቢያውቅ በነበረበት ዞሮ የተቀረውን ሶላት ይቀጥላል። ❶.
_
❶.ሰግዶ ከጨረሰም የሚሰጠው ፍርድ ተመሳሳይ ነው። ጥረት ሳያደርግ ከሆነ ሶላቱን ይደግማል ፤ ካደረገ ደግሞ ሶላቱ ትክክል ነው። (እንደምሳሌ ፈታዋ ልጅና ዳኢማ 6 ፥ 314 ወይም ፈታዋ ሸይኽ ኢብንባዝ ፥ 10/421 ላይ ይመልከቱ።)
_
🩸ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የዛዱል መዓድ ፈታዋ ቁ.119 የ6ኛው ጥያቄ ምላሽ ላይ የተወሰደ
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
📆እሮብ ሙሐረም 21/1441ሂ. # ጷግሜ 4/2012. # Sep 9/2020.
➖➖➖
📣ጆይን ያድርጉ፦ https://telegram.me/ibnyahya777
✅ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya7777




Репост из: Ibn Yahya Ahmed
የዘንድሮው የ1442ሂ. የዐሹራ ፆም ቀናቶች ... ላልደረሳቸው ያስተላልፉ እና ከአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ ..


Репост из: Ibn Yahya Ahmed
▪️#ሙሐረም_እና_የዐሹራ_ፆም

🔻በሙስሊሞች አቆጣጠር የመጨረሻው ወር ዙልሒጃህ ሲሆን የአዲሱ አመት የመጀመርያ ወር ደግሞ ሙሐረም ይባላል። ሙሐረም ከተከበሩት ኣራቱ ወራቶች ማለትም (ዙልቂዕዳህ ፣ ዙልሒጃህ ፣ ሙሐረም እና ረጀብ) ውስጥ አንዱ ነው። የአሏህ ወርም በመባል ይጠራል። ወሩን መፆምም ተወዳጅ ነው። ከአቡሁረይራ ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ከረመዷን ወር በኋላ በላጩ ፆም ፤ የአሏህ ወር የሙሐረም ፆም ነው። ] (ሙስሊም ፥ 1163).
°
🔻የሙሐረም ወር ለየት ከሚያደርገው ውስጥ አንዱ በውስጡ የዐሹራ ቀንን መያዙ ነው። ይህም የዐሹራ ቀን የረመዷን ወር ፆም በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ከመደረጉ በፊት በግዴታነት ይፆም ነበር። ይህን የሚያመላክት (ቡኻሪ ፥ 2001) ላይ የተዘገበ ሐዲስ አለ።
°
🔻በሱናነት መልኩ ይህንን ቀን መፆም ተገቢ ነው። ምክንያቱም አሏህ ነብዩሏህ ሙሳ - ዐለይሂሰላምን - እና ህዝቦቹን ከፊርዓውን በደልና ግፍ ያላቀቀበት ቀን ነው። ይህን በማስመልከትም ዐብደሏህ ኢብን ዐባስ - ረዲየሏሁ ዐንሁማ - [ ረሱል - ﷺ - የዐሹራን ቀን ፁመውታል ሰዎችም እንዲፆሙ አዘዋል። ] በማለት ተናግረዋል። (ቡኻሪ ፥ 2004 እና ሙስሊም ፥ 1130)
°
🔻የዐሹራን ቀን መፆም ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል(ማለትም ትናንሹን) ያስምራል። የአሏህ መልእክተኛ - ﷺ - ስለዐሹራ ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል ፦ [ የዐሹራን ቀን መፆም አላህ ዘንድ ከዚህ በፊት ያለውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ] (መሰሊም ፥ 1162 ላይ ዘግቦታል). የዐሹራን ቀን መፆም እንጂ #እንደዒድ_አድርጎ_መያዝ ክልክል እና አዲስ መጤ የሆነ ተግባር ነው እና ልንርቀው ይገባል። ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው።
°
🔻ከአስረኛው ቀን አብሮ 9ኛውንም ቀንም መፆም ተገቢ ነው። ምክንያቱም ረሱል - ﷺ - (ሙስሊም ፥ 1134) በዘገቡት ሐዲስ ላይ [ የሚቀጥለው አመት ብደርስ 9ኛውንም ቀን ፆመዋለው። ] ስላሉ ማለት ነው። በዚህም ምክንያት ከአይሁዶች ጋር መቃረን ይገኝበታል።
°
🔻ዘጠነኛውን ቀን መፆም ካልቻሉ 10ኛውን እና 11ኛውንም ቀን መፆም እንደሚቻል ዑለማዎች ተናግረዋል። ማስረጃቸውም ተከታዩ ሐዲስ ነው ፦ [ የዐሹራን ቀን ፁሙ የሁዳዎችንም ተቃረኑ ፤ ከሱ በፊት ያለውን ቀን ፁሙ ወይም ከሱ በኋላ ያለውን ቀን ፁሙ። ] (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ ፥ 2154 ላይ ተዘግቧል / አሕመድ ሻኪር ሐሰን ብለውታል).
°
🔻በመሆኑም የዐሹራ ፆም ደረጃዎች ጠቅለል ሲደረጉ እንደሚከተለው ይሆናል ፦

1ኛ ደረጃ ፡ 9ነኛው እና 10ኛውን ቀን መፆም
2ኛ ደረጃ ፡ 10ኛው እና 11ኛውን ቀን መፆም
3ኛ ደረጃ ፡ 10ኛውን የዐሹራን ቀን ብቻ መፆም ነው ፤ በእርግጥ አንዳንድ ዑለማዎች 10ኛውን ቀን ብቻ መፆምን ጠልተውታል ምክንያቱም ነብዩ - ﷺ - አይሁዶችን በመቃረን ስላዘዙ ይላሉ ሌሎች ደግሞ ችግር የለውም ብለዋል።
°
🔻እነዚህን ሶስት ደረጃዎች ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (ሸርሕ ሪያዱሷሊሒን ፥ 3/463) ላይ አስቀምጠውታል። ❶. ኢብኑልቀይዪም (ዛዱል መዓድ ፥ 2/75) ላይ ደግሞ 9 ፣ 10 እና 11ኛውን ሶስቱንም ቀን መፆም የመጀመሪያ ደረጃ ነው በማለት ተናግረዋል። ሌሎቹ ደግሞ ኢብኑልቀይም ይህን ያሉት ደከም ያለ ሐዲስ ላይ ተንተርሰው ነውና በላጩ ደረጃ 9ኝ እና 10ኛውን ቀን መፆም ነው ብለዋል። ወሏሁ አዕለም።
°
🔻ሌላው የሚነሳው ነጥብ #ቀዷእ_ያለበት_ሰው የዐሹራን ፆም መፆም ቢፆም አጅሩን ያገኛል ወይስ አያገኝም የሚለው ነው። እዚህ ላይ አንዳንድ ዑለማዎች የቀዷእ ፆም ግዴታ ስለሆነ ለብቻው መፆም አለበት ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ አብሮ ነይቶ ቢፆምም በአሏህ ፍቃድ የሁለቱንም አጅር ያገኛል የሚሉ አሉ።
°
🔻ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (ፈታዋ-ሲያም ፥ 438) ላይ የሚከተለውን ብለዋል ፦ |" የረመዷን ቀዷእ እያለበት የዐረፋን ወይም የዐሹራን ቀን ፆም ቢፆም ፆሙ ትክክል ነው ፤ ነገር ግን ይህን ቀን ለቀዷኡም አብሮ ቢነይት የሁለቱንም አጅር ያገኛል። "|. ሸይኽ ኢብንባዝም በተመሳሳይ በአሏህ ፍቃድ የሁለቱንም ምንዳ ያገኛል ብለን ተስፋ እናደርጋለን በማለት ተናግረዋል።
ንግግራቸውን በዚህ ሊንክ ማዳመት ትችላላችሁ ፦ bit.ly/2YkwxpA
የቀዷእ ፆማችንን ቶሎ በማውጣት ላይ ልንተጋ ይገባናል።
°
🔻#በተጨማሪም በየወሩ ሶስት ቀን መፆም ያስለመደ ሰው 9ነኛው 10ኛውን እና 11ኛውን ቀን ለሁለቱም ነይቶ ቢፆም የዐሹራውንም እና በየወሩ ሶስት ቀን የመፆምን የሁለቱንም አጅር ያገኛል። ምክንያቱም በየወሩ ሶስት ቀን መፆም ግዴታ "#አያመል-#ቢድ" ላይ ብቻ አይገደብም። ማስረጃውም (ሙስሊም ፥ 1160) በተዘገበ ሐዲስ ላይ ነብዩ - ﷺ - ከየወሩ ሶስት ቀን እንደሚፆሙና ቀናቶችን በተመለከተ ደግሞ መጀመሪያም ላይ ይሁን መካከለኛም ላይ ይሁን መጨረሻ ቀናቶች ላይ እንደተመቻቸው ይፆሙ እንደነበረ ተገልጿልና ነው።
°
🔻9ነኛውን እና 10ኛውን ቀን ፁሞ በተጨማሪም "አያመል-ቢድ" የተባሉት 13 ፣ 14 እና 15 ቀናቶችን ቢፆም ደግሞ በአሏህ ፍቃድ ምንዳው የበለጠ ይሆናል። ምክንያቱም 1ኛ. አያመል-ቢድን መፆም ለብቻው ትሩፋት እንዳለው በተለያዩ ሐዲሶች ላይ መዘገቡ 2ኛ ደግሞ ወሩ ሙሐረም በሙሆኑ ከላይ ባሳለፍነው ሐዲስ መሰረት ፆም ማብዛት ተወዳጅ ስለሆነ ነው።
°
🔻#በመጨረሻም የዐሹራ ቀን ከቅዳሜ ቀን ጋር ከተገጣጠመ ቅዳሜን መፆምን የሚከለክል ሐዲስ ስላለ እንዴት እናድርግ? የሚለው ላይ ሸይኽ ኢብኑዑሰይሚን (መጅሙዓል ፈታዋ ወረሳኢል ፥ 20/57) ላይ የዐረፋ የዓሹራ እና መሰል ፆሞች የቅዳሜን ቀን ቢገጥሙ መፆም ችግር የለውም ምክንያቱም አንድ ሰው እነዚህን ቀናቶች የሚፆመው መፆማቸው የተደነገጉ ፆሞች ስለሆኑ ነው በማለት አስቀምጠዋል። የዐሹራ ቀን የጁሙዓ ቀንን ቢገጥምም ተመሳሳይ ብይን እንደሚሰጠው ዑለማዎች ተናግረዋል።
°
🔻ስለዚህም ወንድሞቼ እና እህቶቼ አሏሁ ተዓላ ለኛ የሚፈጥርልን የኸይር አጋጣሚዎች ችላ በማለት ልናሳልፍ አይገባንም። ራሳችንም ፁመን ሰዎችንም ማነሳሳት ይጠበቅብናል። ወሏሁ አዕለም.
_
❶.ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን በሌላ ቦታ ላይ ደግሞ የመጀመሪያው ደረጃ 3ቱንም ቀን መፆም ነው በማለት የኢብኑልቀይዪምን ንግግር የሚያጠናክር አባባል አላቸው። ያሉበትን ንግግር ለመስማት ፦ https://youtu.be/HGouMgc7oLg
_
✍️ አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን የሕያ @ Ibn Yahya Ahmed.
📆ሐሙስ ሙሐረም 1/1442ሂ. # ነኀሴ 14/ 2012 # Aug 20/2020.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 
📣ጆይን ያድርጉ፦ https://telegram.me/ibnyahya777
✅ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya7777


Репост из: Ibn Yahya Ahmed
▪️ከሸይኽ ኢልያስ ንግግሮች 13.

🔻> (ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ~ በ2001 አብነት መርከዝ ከታዳሚ ለቀረበ ጥያቄ ምላሽ ላይ)
~~~
📣https://t.me/ibnyahya777


Репост из: Ibn Yahya Ahmed
▪️ከሸይኽ ኢልያስ ንግግሮች 13.

🔻> (ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ~ በ2001 አብነት መርከዝ ከታዳሚ ለቀረበ ጥያቄ ምላሽ ላይ)
~~~
📣https://t.me/ibnyahya777




Репост из: Ibn Yahya Ahmed
▪️የለይለተል ቀድር ዱዓ

🔻በነዚህ በረመዷን የመጨረሻዎቹ 10ለሊቶች ላይ ለይለተል ቀድር ስለሚከጀል ይህን ነብዩ -ﷺ- ለአዒሻ -ረዲየሏሁዓንሃ - ያስተማሯትን እና በሶሒሕ የሐዲስ መዛግብት ላይ የተዘገበውን ዱዓ ማድረግን እናብዛ ፦

{ اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّى }
በአማርኛ ሲነበብ ፡ "አልሏሁመ ኢንነከ ዐፉውዉን ቱሒብቡል ዐፍወ ፈዕፉ-ዓንኒ"
°
ትርጉሙም ፡ ´´አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህና ይቅር በለኝ።´´
➖➖➖➖➖➖➖➖
📣https://telegram.me/ibnyahya777

Показано 20 последних публикаций.

258

подписчиков
Статистика канала