መረጃ‼️
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ የኢላሙ ቀበሌ አሥተዳዳሪ ክፍያለው ነጋሽ አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ትናንት በቢሯቸው አካባቢ በፈጸመው ጥቃት መገደላቸውን ዋዜማ ሰምታለች።
ከአሥተዳዳሪው ጋር የነበሩ በርካታ የጸጥታ ኃይል አባላት ቆስለው ለሕክምና ወደ ፍቼ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የዓይን እማኞች አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ በደገም ወረዳ ሐምቢሶ ከተማ አማጺ ቡድኑ ትናንት ሌሊት በፈጸመው ጥቃት አንድ የሚሊሻ አባል ሕይወቱ ሲያልፍ፣ ሌሎች በርካቶች ታፍነው መወሰዳቸውን ዋዜማ ተረድታለች።
በገርበ ጉራቻ ወረዳ ኩዩ ከተማም በተመሳሳይ ሰዓት ቡድኑ የአፈና ድርጊት መፈጸሙን ዋዜማ ተረድታለች።
ቡድኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠረ ግድያና ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛል።
@Sheger_press