በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የቢሾፍቱ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዙሪያ ተነሺ አርሶ አደሮች ተቃውሞ እያሰሙ መኾኑን አፍሪካን ኢንተለጀንስ ድረገጽ ዘግቧል።
አርሶ አደሮቹ ቅሬታ ያሰሙት፣ ከካሳ እና ከሠፈራ ዕቅድ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።
መንግሥት ለማስፋፊያው የቀጠረው የሊባኖሱ አማካሪ ኩባንያ፣ አርሶ አደሮች ይነሱባቸዋል ወደተባሉት ቦታዎች ቅድመ-ጥናት የሚያካሄድ የባለሙያዎች ቡድን መላኩንም ዘገባው አመልክቷል።
አኹን ከሚኖሩበት ቀያቸው 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንዲሠፍሩ ይደረጋሉ የተባሉት አርሶ አደሮች እስከ 2 ሺሕ 500 ይደርሳሉ ተብሏል።
ተነሺዎቹ አርሶ አደሮች፣ በአንድ ስኩዌር ሜትር 322 ነጥብ 5 ብር ካሳ እንዲከፈላቸው እንደታሰነ ከአርሶ አደሮቹና ከአንድ ደብዳቤ ላይ መመልከቱንም የዜና ምንጩ አውስቷል።
@sheger_press