✔ 🌺የባል አይነቶች🌺 ✔
┉┉✽̶»̶̥🌸✿🌸»̶̥✽̶┉┉
⏮ከባለፈው⏺የቀጠለ⏭
5⃣💐ጥገኛ ተውሳክ ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸✿🌸»̶̥✽̶┉┉
ሰነፍ ነው። ሚስቱን የሚያፈቅረው ለገንዘብ ሲል ነው። የሚስቱን ብር ኢንቨስት የሚያደርገው ለሌሎች ሴቶች ነው። ሐሳብ የማመንጨት ችሎታው ተሰልቧል። በቤት
ውስጥ ያሉ የጋራ ኋላፊነቶችን በሙሉ ጠቅልሎ ያስረከበው ለሚስቱ ነው። እርሷን ማገዝ
የሚባል አይታሰብም። ተቀላቢ ወንበዴ ነው።
💐6⃣ህጻን ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸✿🌸»̶̥✽̶┉┉
ኃላፊነት አይሰማውም። የጨቅላነት ባህሪ ያጠቃዋል። ቤተሰቦቹን አሊያም ዘመዶቹን
ሳያማክር በራሱ ውሳኔ መስጠት አይችልም። ልፍስፍስ ነው። ብዙውን ጊዜ ውሳኔ
ለመውሰድ የሚያማክረው ከሚስቱ ቤተሰቦች ይልቅ ቤተሰቦቹን ነው። ግና አላስፈላጊ
ችግር ሲፈጠር ሁሌም ጣቱን የሚቀስረው ወደ ሚስቱ ቤተሰቦች ነው።
💐7⃣እንግዳ ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸✿🌸»̶̥✽̶┉┉
ውሎው ሁሌም ከቤት ውጭ ነው። ወደ ቤት ሲመጣም እንደ እንግዳ ነው። ለቤተሰቦቹ
አስፈላጊውን ቁሳቁስ ያቀርባል። ግና ለነርሱ የሚሰጠው ሽራፊ ጊዜ የለውም። ቀኑን ሙሉ
ከተማውን ሰልሎ ለአዳር ወደ ጫካ እንደሚገባ ሽምቅ ተዋጊ ነው።
💐8⃣ተንከባካቢ ባል💐
┉┉✽̶»̶̥🌸✿🌸»̶̥✽̶┉┉
አፍቃሪ እና ተንከባካቢ ነው። ለቤተሰቡ ጊዜ ይሰጣል። ከቁሳዊ አቅርቦት ባሻገር ስሜታዊ
ፍላጎቶችን ያሟላል። ቤቱን በመንፈሳዊ ስርዓት ይመራል። ኃላፊነቱን በጥንቃቄ ይወጣል።
ለሚስቱ ደጋፊ እና አጋርም ጭምር ነው።
🎴የባል አይነቶች በዚሁ ተጠናቀቀ አንተ ከየትኛው ነህ ወይም የአንቺ ባል ከየትኛው ነው ?
♥️ፈጣሪ ለሁሉም ሰው የሚመኘውን ሳይሆን በልቡ የሚያፈቅረውን ይስጠው !!!
📨ሼር ማድረግ እንዳትረሱ
💞💞💞💞ፍቅር ያሸንፋል💞💞💞💞
@ethiopian_spy 💚💛❤
@ethiopian_spy 💚💛❤