Репост из: Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
ሥዕለት ሲደርስ
"…በድጋሚ የአሜሪካ መሪ ሆኖ ለመመረጥ ከወራት በፊት ከጆ ባይደን ጋር ሲወዳደሩ የነበሩት የዛሬው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት እንዲህ ብለው ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሥዕለት ተስለው በትዊተር ገጻቸው ላይ ለጥፈው ነበር።
"…ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ በጦርነቱ ጠብቀን። ከዲያብሎስ ክፋትና ወጥመዶች ጠብቀን። እግዚአብሔር ይገስጸው፣ በትህትና እንጸልያለን፣ እናም አንተ የሰማይ ሠራዊት አለቃ ሆይ፣ በእግዚአብሔር ኃይል፣ የነፍስን ጥፋት እየፈለጉ በዓለም ላይ የሚንከራተቱትን ሰይጣናትንና ርኩሳን መናፍስትን ሁሉ ወደ ሲኦል ጣላቸው። አሜን።
"…ለትራንፕ ሥዕለቱ ደርሷል። ጸሎቱም ተሰምቷል። የትራምፕ ሃይማኖት ጴንጤ ይሁን ካቶሊክ ዐላውቅም። ኢየሱስ ብቻ ከሚሉት ከጴንጤዎች ወገን ነው እንዳይባል ደግሞ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ለመፈለግ አይደክምም ነበር። ካቶሊክም አይመስለኝም። ኦርቶዶክስ ባይሆንም ግን የሆነ ለኦርቶዶክስነት የቀረበ ነገር እንዳለው ከእንቅስቃሴዎቹ ማየት ይቻላል።
"…የሆነው ሆኖ ፕሬዘዳንቱ የተሣለው ሥዕለት ሰምሮለት፣ የቅዱስ ሚካኤል ምልጃም አግዞት፣ ከብዙ የሞት ወጥመዶችም አምልጦ በዛሬው ዕለት ጥር 12/2017 ዓም በቃና ዘገሊላ ዕለት አሜሪካንን በቀጥታ፣ ዓለምን በተዘዋዋሪ ለመምራት መንበረ ሥልጣኑን በይፋ ይረከባል። ግጥምጥሞሹ ገርሞኝ ነው። ውስጡን እግዚአብሔር ይመርምረው እንጂ ፕሬዘዳንቱ በሆኑ ነገሮቹ ከሚገባው በላይ እያንጫጫም ነው።
"…ከጃንሆይ ጊዜ ጀምሮ በትምህርት፣ በሥራ፣ በጋብቻ በተለይ በዲቪና በሜክሲኮም ወደ አሜሪካ የጎረፉ ኢትዮጵያውያን በተለይ ኦርቶዶክሳውያኑ ለሆዳቸው መሮጡን ገታ አድርገው ለማንኛውም የሚሆነው አይታወቅምና የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ይዘው ሄደው ስለ ኢትዮጵያ ቢያናግሩት ብዬ ተመኘሁ።
• ስደቡኝ አሏችሁ ደግሞ። 😂😂