ይኸውላችሁ…
"…ከዛሬ ጀምሮ አልፎ አልፎ ቢሆን የምተገብረው በቴሌግራም የድምፅ መልእክትም ማስተላለፍም እጀምራለሁ። በሥራ ላይ ያሉ ሁሉ ሥራቸውን ሳያስተጓጉሉ በጆሮአቸው እየሰሙ እንዲከታተሉኝ። ቤተሰቦች፣ ጓደኛማቾችም ሰብሰብ ብለው እንዲያዳምጡት በድምፅም እመጣለሁ። አሁን በ45 ደቂቃ ከ33 ሰከንድ መልእክት እጀምራለሁ። ጠብቁኝ።
"…ከድምጽ መልእክቱ ቀጥሎ በጎጃም የተፈጸመ አሰቃቂ ታሪክ አስነብባችኋለሁ። እኔ አልቅሼ አልቅሼ ራሴን የታመምኩበትን አሰቃቂ ወንጀል እጽፍላችኋለሁ። አሰቃቂ ወንጀሉን ካነበባችሁ በኋላ ጥያቄም ይኖረኛል። ለመመለስ ተዘጋጁ።
"…ዛሬ በቲክቶክ ከቻልኩ እመጣለሁ ካልቻልኩ ግን ዛሬ ባልመጣም ሐሙስ ግን እንደምንም ለመምጣት እሞክራለሁ። እናንተም ተዘጋጅታችሁ ትጠብቁኛላችሁ።
"…የጎጃም ዐማራን ተብትቦ የያዘውን ዘንዶ ብቻዬን እጨፈልቀዋለሁ። በጎጃም የገባውን አራጅ፣ ደም አፍሳሽ ብቻዬን አፈር ከደቼ አበላዋለሁ። አዛኜን እውነቴን ነው።
"…እህሳ የድምፅ ቅጂውን ለመስማት፣ ሰምታችሁም ሓሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…?