ከሌሎች ጋር እየተጣመራችሁ ላላችሁ እህቶች
~
ሙስሊም ካልሆነ አካል ጋር "ትዳር" መመስረት ለማይረባ የዱንያ ህይወት ዘላለማዊውን ኣኺራ ማጨለም ነው የሚሆነው። በተለይ እህቶች ቆራጥ ሁኑ። በእሳት አትጫወቱ። ኣኺራ ቀልድ አይደለም። ጀሀነም ቧልት አይደለም። እነዚያ የነቢዩ ﷺ ምርጥ ሶሐቢያት ትዳራቸውን በትነው ረጅም ጊዜ የሚወስድ አደገኛ መንገድ አቆራርጠው ሂጅራ ያደረጉት በትዳር ላይ ሸፍተው አልነበረም። አነሰም በዛ ትዳር የራሱ ጣእም አለው። ግና ኢማን ከሌለበት በኩ- ፍ- ር ውስጥ ካለ ትዳር እምቧይና እሬት ይጣፍጣል። ይህንን ስለተረዱም ነው ግፋ ቢል የጠዋት ጤዛ የሆነችዋን የዱንያ ደስታ ጥለው መከራውን በመጋፈጥ ወደ ኢማን የተጓዙት። "ዱንያ ለሙእሚን ወህኒ ቤት፣ ለከ -ሃዲ ደግሞ ጀነቱ ናት" ይላሉ ውዱ ነብይ ﷺ። ኣኺራ ደግሞ በተቃራኒው። የትኛው ጀነት ይሻልሻል? የዱንያው ወይስ የኣኺራው? የዱንያውን ስትመርጪ በኣኺራሽ ላይ ወስነሻል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor