ISLAMIC SCHOOL️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ኢስላም በትምህርት ቤት

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


⇛የደከመችን ነፍስ በቶሎ የማከም እምቅ ሀይል ያላት ከቃል በላይ የሆነች የተስፋ ቃል..♥
( إِنَّ مَعَ ٱلْعُسْرِ يُسْرًۭا )
ከችግርም ጋር ምቾት አልለ!

@islam_in_school


መጀመሪያው እዝነት፣ ...”
~
ረመዳን ላይ በየመሳጂዱ እንዲህ የሚል ተደጋግሞ የሚነገር ሐዲሥ አለ:-
أولُ رمضانَ رحمةٌ، وأوسطُه مغفرةٌ، وآخرُه عتقٌ من النارِ
“የረመዳን ወር መጀመሪያው እዝነት ነው። መካከሉ ምህረት ነው። መጨረሻው ደግሞ ከእሳት ነፃ መውጫ ነው።”

ሐዲሥ ደካማ (ዶዒፍ) ነው። ለማስረጃነት የሚያበቃ ጥንካሬ የለውም።

@islam_in_school


ኧረ ተውው ይሄ ቻናል አንድ ቀን ያስደስታችሃል ተንከባክቡት😂

ዱዓ አርጉበት እስኪ


Someone said...
" ጭቃ ውስጥ ሆነህ ከአሳማ ጋር ትግል አታድርግ። አንተ ትቆሽሻለህ እሱ ግን ይዝናናል። ቆሻሻን መዝናኛው እና መዋያው ያደረገን ሰው በተቻለን አቅም እንራቅ!"

...100% true.

@islam_in_school


እያንቀላፉ ሶላት መስገድ፣ ቁርኣን መቅራት እና ዱዓእ ማድረግ አይገባም።

@islam_in_school


ፆም ከእስልምና መሰረቶች ውስጥ 4ተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ሶላት ደግሞ 2ተኛው ደረጃ ላይ ናት… ከሶላትህ ተኝተህ በፆምህ ከመኩራት ተጠንቀቅ!


የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) ስለ ስሁር እንዲህ ብለዋል።

« ስሁር ከአላህ የተሰጣችሁ ረድዔት ነውና እንዳትተውት።»


@islam_in_school


ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

«አማኝ ማለት ጎረቤቱ ከጎኑ እየተራበ የሚጠግብ ሰው አይደለም።»

@islam_in_school


የረመዷንን ሌቦች ተጠንቀቁ!
|•|
አንደኛው ሌባ፦
ቴሌቭዥን ለሥጋም ሆነ ለመንፈስ ከፍታ አጋዥ ካልሆኑ ነገራቶች ውስጥ አንዱ ነው። በተለይ ደሞ የረመዷን ሙሰልሰላቶችን እና አዘናጊ ድራማዎችን ተጠንቀቁ፤ የረመዷን ዉድ ጊዜያት ለዉድ ነገሮች መዋል አለባቸው፡፡

ሁለተኛው ሌባ
ስልክ ብዙ ማውራት ለብዙ ስህተት ያጋልጣል፣ ትርፍ ንግግር ወደ ሀሜትና ያልታሰቡ ወንጀሎች ይመራል፤ለተሻለ ምንዳ በረመዷን በንግግር ጭምር ቁጥብ መሆን ያስፈልጋል፡፡

ሦስተኛ ሌባ፦
ወጣ ገባ ማብዛት/መዞር፡፡ በረመዷን ከመስጊድ እና ከቤት የበለጠ ማረፊያ የለም፡፡ ወደ ከተማም ይሁን ወደ ገበያ ያለበቂ ምክንያት ወጣገባ ማብዛት ዐይንንም ሆነ ጆሮን ያልሆነ ነገር ይጥላል፡፡ፆምን ይሰርቃል፤ ምንዳዉንም ያጓድላል፡፡ 

አራተኛ ሌባ፦
ማምሸት፡ ያለምክንያት ማምሸት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለዉም፡፡ የረመዷን ምሽቶች ምርጥና ዉብ ናቸው፡፡ በቁርኣን፣ ዚክር እና በተለያዩ ዒባዳዎች መዋብ አለባቸው፡፡

አምስተኛ ሌባ፦
ኩሽና:በተለይ ለሴቶች፡፡ሙሉዉን ረመዷን ማዕድ ቤት የሚያሳልፉ ቁርኣንን፣ ሶላትና ዚክርን የረሱ ብዙ ናቸው፡፡ ረመዷን የፆም ወር ነው፡፡ ትልቁን ትኩረት ለሆድ መስጠት ዓላማዉን መሳት ነው የሚሆነው፡፡

ስድስተኛው ሌባ፦
ሶሻል ሚዲያ፡፡ ዛሬ ላይ የብዙዎቻችን ችግር ሆኗል፡፡በቤትም ሆነ በመስጊድ ሳይቀር ትልቅ ትኩረት ሰጥተነው ጊዜያችንን እየጨረስንበት ነው፡፡ በዚህም ከዚክር፣ ከቁርኣን፣ ከዱዓ እንዳንጠቀም ሆነናል፡፡ እንጠንቀቅ፡፡

@islam_in_school

900 0 14 1 15

ረመዳን ቀን 2️⃣

ረሱል () እንዲህ ብለዋል፦

﴿ثلاثٌ من أخلاقِ النُّبوةِ: تَعجيلُ الإفطارِ، وتأخيرُ السُّحورَ، ووضْعُ اليمينِ على الشِّمالِ في الصلاةِ﴾

“ሶስት ነገሮች የነቢያት ባህሪ (መገለጫ) ነው። ፍጡሩን አቻኩሎ መመገብ፣ ሱህርን አዘግይቶ መመገብና በሶላት ግዜ ቀኝ እጅን በግራ እጅ ላይ አድርጎ በደረት ላይ ማስቀመጥ።”

ሶሂህ አልጃሚ: 3038


@islam_in_school


"ስሁርን ተመገቡ ስሁር መብላት በረካ አለው።"

የአላህ መልክተኛው ﷺ


#ኢና_ሊላህ_ወኢና_ኢለይሂ_ራሂዑን💔😢

ሰሞኑን ያጋራናቹህ የካንሰር ተጠቂ የ18 አመቱ ሃፊዝ #አነስ ወደ አኼራ ሄዷል

ገና በ10 አመቱ የመስጅድ ኢማም ነበር የዛሬ ሳምንት ተወዳጁ ሼኽ #መንሱር_ሳሊሚ ወደ ቤቱ በማምራት አነስን ዘይረውት ነበር በጣም ተደስቶ ነበር ።

#አነስ ከትላንት ወዲያ ኡምራ አድርጎ ወደ ቤቱ ተመለሰ ትንሽ ጋደም ልበል ብሎ አረፍ አለ ዳይግመኛ ግን አልነቃም ከጌታው ጋ ተገናኛ። አላህ ይዘንለት 🤲

ሁላቹሁም በዱአቹህ አስቡት
اللهم ارحمه واغفر له ووسع مدخله، واجعل عمله الصالح وابتسامته وطيبته نورًا له في قبره، واجمعه مع الصالحين والأبرار في فردوسك الأعلى🤲🤲

©️Hijra Tube ኢስላማዊ ድህረ ገፅ


ዜና፡ የ #አክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ሂጃብ ባገዱ ትምህርት ቤቶች ላይ የተመሰረተውን ክስ ውድቅ አደረገ፤ ተማሪዎች ውሳኔውን አወገዙ

የ #ትግራይ እስላምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ በከለከሉ ትምህርት ቤቶች ላይ የተከፈተውን ክስ የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት መዝጋቱን አስታወቀ።

ፍርድ ቤቱ ክሱን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የማስተላለፍ 'ሥልጣን እንደሌለ' በመግለጽ ጉዳዩ 'ሽምግልና ወይም በአስተዳደር ሂደት' መፈታት እንዳለበት መወሰኑን የክልሉ እስላምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ አስታውቋል።

የምክር ቤት ፀሐፊ ሀጂ መሐመድ ካህሳይ ውሳኔው የተላለፈው ቀደም ሲል በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሂጃብ መልበስ እንዳይከለከል የወሰነው ዳኛ ከኃላፊነቱ ተነስቶ በሌላ ሰው መተካቱን ተከትሎ ነው ብለዋል።

@islam_in_school


ከ አምሥት ደቂቃ የበለጠ ጊዜ አይወስድም። ኃጢአትን ግን በብዙ ያስምራል። እንዘክረው:–

® ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "በቀን ውስጥ ለመቶ ጊዜ ያህል ‹‹ሱብሐነላሂ ወቢ ሐምዲሂ ሱብሐነላሂል ዐዚም›› ያለ ሰው፡ ኃጢአቱ እንደ ባሕር ዐረፋ የበዛ ቢኾንም ይሰረዛል" (ቡኻሪይ 6042)፡፡


ካላንደር ለሌላችሁ!

የኢፍጣር፣ የሰሑር፣ እና የሶላት ወቅቶች ሰዓት ለአዲስ አበባና ዙሪያዋ!


Credit: የመጅሊሱ ጠቅላይ ም/ቤት

ለሌሎችም አሰራጩት።

@islam_in_school


የቁርአን_መርሀ_ግብር_240310_102958 (1).pdf
2.1Мб
በረመዳን ቁርዓንን እስከፈለጋቹ ለማኽተም የሚረዱ ፕሮግራሞች ናቸው ተጠቀሙበት

@islam_in_school


ሄደ.. ሸይጣኑ ሄደ..😂😂😂

@islam_in_school


ሰበር

በሳኡዲ ዛሬ ጨረቃ በመታየቱ ነገ ቅዳሜ የረመዳን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል። ዛሬ ተራዊህ ይጀመራል።

@islam_in_school


በሳኡዲ አረቢያ ጨረቃን ለማየት በፍለጋ ላይ!

21/6/2017 
29 ሻዕባን 1446

@islam_in_school


እጅግ የሚገርም ነው ለማመን የሚከብድ ነው! ባለፈው ሳምንት ብቻ 5 ሚልየን አማኞች የረሱላችንን(ሰዓወ) ሀገር መዲናን ጎብኝተዋል!
ያረብ እኛንም ይህንን የተከበረ ቦታ ለመዘየር ያብቃን ።

@islam_in_school

Показано 20 последних публикаций.