الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه أما بعد
እንደሚታወቀው ነቢልና ጓደኞቹ ሰሞኑን ወደ ሸገር ለደዕዋና ዚያራ በሚል የክተት ጥሪ ተንቀሳቅሰው ነበረ ።እውነታው ግን ከዚህ ተቃራኒ ነው ። ትተዋቸው ሊሔዱ ያሉትን ሰዎችና መሀል ሰፈሮችን ማፅናኛ እንድሁም ከወትሮው እነሱን ያልደገፉ አካላትን ለመውቀስ ፣የረመዷን መፆሚያ ለመረበጥ መሆኑን ንግግሩ ጠቁሞናል ።
ድምፁን እያለሰለሰ ለማስረዳትና እባብ የሆነው ማንነቱን ለመደበቅ ቢሞክርም በሚገባ የሚያውቁት ፣የሱን ግፍና ገፈት የቀመሱት ሰዎች እንደ አጉሎ መነፀር ይመለከቱታል ። አንተን የጠላንህ በሙስጠፋ ምክኒያት ሳይሆን እልልም ያልክ አስመሳይና መሰሪ ስለሆንክ ነው ።ብዙ ወንድሞችም በዚሁ መጥፎ ባህሪክ እንደጠሉህ ተናግረዋል ። ሲጀምር አንተ ውስጥ ለውስጥ ገለልተኛ መስለህ ስትዶልት ሙስጦፋ አንድ የተናገረው ነገር አልነበረም ። እራስህ ባጠመድከው ወጥመድ ውስጥ ገብተህ ብትንገራገጥ አንሰማህም ። ወላ ኡስታዝ ያኔ ኧረ ምንድነው ዝምታህ በዛ የሆነ ነገር በለን ስንለው ራሱ መልስ አይሰጠንም ነበረ ።
እስከዛሬም ድረስ ስለናንተ በሆነ አጋጣሚና መናገር ሲኖርበት ብቻ እንጂ አያነሳችሁም ።
አዲስ አበባ ሔደክ የአዞ እንባ ብታዘንብ የምትቀይረው እውነታ እና የምታተርፈው ቅንጣት ያክል ትርፍ የለህም ።
ይሔ አስመሳይ ጠቅስ በተልቢስ ካለፋቸው ነጥቦች የገንዘብ ጉዳይ ነው ። የዚህም ነገር እውነታው እንዴት እንደሆነና በምን አይነት መንገድ እንደተዘረፈ ወንድማችን #አቡ _ማሒ አብድል ከሪም በሁለት ተከታታይ ኦድዩ ገልፆታል ።ወይም ገንዘቡን መልስ ወይ ደግሞ ለንግግሩ መልስ ስጥ ።ደጋ ሲነቃብህ ወደ ቆላ ሔደህ ጎጆ መቀለስ ከወንድሞች የሰላ ብዕር አያተርፍህም ።
ከዚያም ከመሻይኽ ተብየዎቹ የነበረውንም ነገር ለመግለፅ ሞከረ ግን አልተሳካለትም
~
። ጉዳዩ ግልፅ ነው ፣መሻይኽ ተብዬዎቹም ለነሱ ጭፍን ተከታዩች በደንብ ወግነዋሉ ።የነቢዩን ሰፊ የደዕዋ አድማስ የራሳቸው ሳሎን አስመስለውታል ። እነሱጋ ሚዛን ሸይኻቸው ማወደስና ለሸይኻቸው ታዛዥ መሆን ብቻና ብቻ ነው ።ኣይ ካልክ በቅፅበት ውስጥ የታፔላ ካርድ ነው የሚመዘዝልክ ።በጣም ጠባቦችም ናቸው ። እንድህ አይነት የትልቅ ህፃኖች ምንም አይነት ክብር የላቸውም ። እንደመጣላው የሚናገሩ ፣ እንደሰሙ የሚያስተላልፉ ለንግግራቸው ሚዛን የሌላቸው አካላት ናቸው ።እንድህ አይነቶቹን ጉደኞች ሰዎችን ኢምቲሓን ማድረጊያ አድርጎ ማስቀመጥ ትልቅ የሆነ በደልና ግፍ ነው ።
ደዕዋና አንድነት የሚያሳስባቸው ቢሆኑ ሙስጠፋ ለምን እኛን አክብሮ አልመጣም ብለው ባልተናገሩ ነበረ ። እኒህ ለክብራቸው የቆሙ እንጂ ሌላ ምንም አይደሉም ። ታላቅ ናቸውኮ ፣ልጅ ሲያጠፋ መምከር አንዳንዴ ዝቅ ብሎ ማስተማር ያለ ነው ግን… ……
ከዚያም እሱ ምንም እንዳልተናገረ ለማስረዳት ሞከረ ።
~~
አንደኛ በገሃድ ዝም ብትልም ውስጥ ለውስጥ እንደ ኢብኑ ሰሉል ስትቆፍር ነበረ ። ሁለተኛ ደግሞ እንደጀማል ደቃቅ አይነቶቹ ግንፍልተኛ ግብዞች ያንተን የውጪ ጩኸት ሸፍነውልካል ። እነሱን ለሚድያ ዘመቻ መድበህ አንተ ውስጥ ለውስጥ ለጉድ ዘምተካል ።
ደቃቅ የተባለው መሐይም በሚድያ ስንት እንደቀላበደ ፣ በኡስታዝ ላይ እንዴት እንደዘመተ ሁላችንም እናውቀዋለን ። ያሳምምልኛል ያላቸውን ቃላቶች በሙሉ ተጠቅሟል ።ነገር ግን ኡስታዝ ለትንኝ ቦታ የለውምና አንድ ቀን መልስ ሰጥቶት አያውቅም ። እሱም ጩኸቱ ሲሰለቸው፣ ብዕሩ ሲደርቅ ድራሹ ጠፍቷል ።
ከዚያም ብዙ ሰው እንዳተረፉ ለማሳየትም ሞከረ
~~
ይሔም ማብራሪያ የሚያስፈልገው ነገር አልነበረም ግን የተወሰነ ልበል ።እውነታው ነገሩ ተገልብጦባቸዋል ።ኣዎ እነሱ እንዳሰቡት አልሆነላቸውም ። ሙስጠፋን ብቻውን አስቀርተው ጀመዓው ለመጥረግ ነበረ አላማው ግን ከጓደኞቻቸው እና ከአማቾቻው በስተቀረ ማንም የተከተላቸው የለም ። እስከ ሰባ የሚሆኑ እያለ የሚቆጥራቸውም ያኔ ጀለብያ መልበስ አቅቷቸው ሲወዛወዙ የነበሩ ፍሬሾችን እንድሁም ከሶስት ሚስት የወለዳቸውን ልጆች ጨምሮ ነው ። እነኚህ በሰዓቱ አይደለም የናንተን ፊትና ሊረዱ ይቅርና መንሀጁ ራሱ በደንብ ያልገባቸው እንጭጮች ናቸው ። ከዚያም ለተወሰኑት ሀላፍትና ተሰጠና ሙሉ በሙሉ የነሱን አይዶሎጂ አራማጅ አደረጓቸው፣እንደ ቁጥር ማባዣም ተጠቀሙባቸው ። ከዚያ ያለፈ እሱ እንደሚለው እውነታው ገብቷቸው ? ክክክክ አብዛኽኛው የወያላ ባህሪ ያልለቀቃቸው ፣ስራቸው ቀፋፊ የሆኑ ሰዎች ናቸው ።
እኛ ነን ያስተዋወቅነው
~~~
መሀይም ሲናገር ከአፉ የሚወጣውን አያውቅም ። ሰውዬ ሰውን ከፍም ሆነ ዝቅ የሚያደርገው አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው ። እንድሁም መልካም ስራውና ለአሏህ ዲን የሚያደርገው ልፋት ነው ። አንተ ሳትሆን ጡሩ ስራውና ቂርዓቱ ደዕዋው ነው ያስተዋወቀው ። ባይሆን አንተና መሰሎችህ በሱ ምክኒያት ታወቃችሁ ቢባል ያስኬዳል ።
ደግሞምኮ የሰጣችሁትን ውዳሴ ሁሉ ነጥቃችሁታል ። እኛ አስተዋወቅነው እያልክ አታላዝንብን ። የሚወደድበትን ነገር ፈፀምክ ከዚያም ያንን ነገር ነጥቀህ ስሙን አጠልሽተሃል ። ስለዚህ ጩኸትክ ሁሉ ከንቱ ነው ። ሙስጠፋ አልጋው ላይ ተኝቶ አንተ በየከተማው ዞረክ ሙስጠፋ የሚባል ጡሩ ሰው አለ ብለህ ያስተዋወቅክው አስመሰልከውሳ ሸሁ?
https://t.me/qenat_mohammed_surur_dessie