Maraki News


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


Addisababa, Ethiopia🇪🇹
👇ማስታወቂያ ለማሰራት
@Adis_pro

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ዛሬ ሰኞ ማለዳ ሦስት አርሶአደሮች በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ገለፁ። አርሶ አደሮቹ ላይ ግድያው የተፈጸመው በዞኑ ጎርካ ወረዳ ኬሬዳ ቀበሌ ሸኮ በተባለ መንደር ውስጥ ነው።
ከሟቾቹ የአንዱ ቤተሰብ መሆናቸውን ለዶቼ ቬለ የተናገሩ አስተያየት ሰጪ «ሟቾቹ ግድያው የተፈጸመባቸው ማለዳ ወደ ማሳ በመውረድ ላይ እንዳሉ ነው። ገዳዮቹ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ተሻግረው የገቡ ናቸው። ሦስቱንም በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ደብድበው ነው የገደሏቸው። የሟቾቹን አስክሬን ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተቀበልን ሲሆን ሥረዓተ ቀብራቸውም ነገ ይፈጸማል» ብለዋል።
ዶቼ ቬለ በአርሶአደሮቹ ግድያ ላይ የኮሬ ዞን አስተዳዳሪንም ሆነ የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የሥራ ሀላፊዎችን አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም በኮሬ ዞን በተደጋጋሚ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን አስመልክቶ ዶቼ ቬለ በቅርቡ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የኮሬ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴ ዶክተር አወቀ ሀምዛዬ መፍትሄው ሁለት ነው ይላሉ። አንድም የፀጥታ ኃይሉ ጠንካራ ዘመቻ በማድረግ ታጣቂዎችን ማጽዳት ወይም ሕዝብ ራሱን እንዲከላከል በሕጋዊ መንገድ ማስታጠቅ።
@marakinews


በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ፈጽመዋል በተባሉት ድርጊት የተከሰሱት የእነ ጆን ዳንኤል ጠበቆች የደንበኞቻቸው የክስ ዝርዝሩ እንዲሻሻል የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ በጽሁፍ ዛሬ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች በኩል በቀረበው የክስ መቃወሚያን በሚመለከት ዐቃቤ ሕግ ከቀጠሮ በፊት መልሱን በሬጅስትራር በኩል እንዲያቀርብ በማለት በአጠቃላይ በመቃወሚያው ላይ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስተቱ ተገልጿል።

ተከሳሾቹ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ መሆናቸው ይታወቃል።
@marakinews


ቀን:-03/02/2017 ዓ/ም
የቅጥር ማስታወቂያ
------------------------
ሜድስኬፕ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ እንጅባራ ካምፓስ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች ከስራ ፈላጊዎች መካከል መስፈርቱን የሚያሟሉ አሰልጣኝ መምህራኖችን እና አስተዳደር ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም
➫ Pharmacy  ብዛት  01
  ➫ Nursing    ብዛት  01 
  ➫Web Development and Database administration(IT,CS)  ብዛት  01
➫አካዉንታንት  ብዛት  01
ዝቅተኛ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ
➫ለአሰልጣኝ መምህራን የመጀመሪያ  Degree ሁኖ  COC ያለዉ፣ Teaching Methodology (የማሰልጠን ስነ-ዘዴ) ፣የካይዘንና ኢንተርፕረነርሽፕ ስልጠና የወሰደ
➫ ለአካዉንታት ሙያ ዲፕሎማ/ዲግሪ
➫ የቅጥር ሁኔታ፡- በቋሚነት
➫ የስራ ቦታ፡- እንጅባራ
➫ ደመወዝ፡- በጣም ማራኪ ሁኖ በስምምነት
መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች የማይመለስ የትምህርት ማስረጃ ኮፒ በመያዝ  ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን  03/02/2017 ዓ/ም  ጀምሮ እስከ ቀን 08/02/2017 ዓ/ም
የፈተና ቀን ፡-  በስልክ፣በማስታወቂያ፣በኮሌጁ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የምናሳዉቅ ይሆናል፡፡
ለምዝገባ ስትመጡ ወይም ዶክመንት ስትልኩ ከ 8ኛ ክፍል ጀምሮ ያለዉን ሙሉ ዶክመንት፣የስራ አጥ ማስረጃ፣ስራ ያላቸዉ ከሆነ የስራ መልቀቂያ ፣ከግል ተቋማት የሰሩ ከሆነ የስራ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ፣ ከማይመለስ ፎቶኮፒ ጋር በማቅረብ ሜድስኬፕ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ እንጅባራ ካምፓስ የሰዉ ሃይል ቢሮ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ ፡- 09 62 79 18 08   / 09 95 22 22 94 / 09 42 03 64 54


በጣም እየዘነበ ነው: መሽቷል: ወደ 3 ሰአት ገደማ ከዋናው አስፋልት ተገንጥሎ የሚያስገባውን ኮብልስቶን ይዤ ወደ ቤት እየገባሁ

በጣም እየዘነበ ነው: መሽቷል: ወደ 3 ሰአት ገደማ ከዋናው አስፋልት ተገንጥሎ የሚያስገባውን ኮብልስቶን ይዤ ወደ ቤት እየገባሁኝ ነው አንድ ሱፍ ዝንጥ ብሎ የለበሰ ሰውዬ በዝናብ ውስጥ በፍጥነት ይራመዳል: ዝናብ እየደበደበው ነው: መጀመርያ አለፍኩት ካለፍኩት በኃላ ቆም አልኩኝና ወደ ኃላ ተመልሼ ቆምኩኝ ከዚያም መስኮቱን ወረድ አድርጌ “ና ግባ: ልሸኝህ ጨለማ ነው” አልኩት ፍርሃት ይታይበታል “አይ ይቅርብኝ” አለኝ “ኧረ ና ግዴለህም: ዝናብ አይደብድብህ” አልኩት “አይ ግዴለም ይሁን” ብሎ መራመዱን ቀጠለ የእውነት አዘንኩኝ: though I understand his concern and fear 👇🏾 ክፉ ጊዜ: ክፉዎች የጫሩብን ፍርሃት አብሮ ከመሄድ እና ከመደጋገፍ ይልቅ ዝናብ እና ጨለማ የሚያስመርጥ ፍርሃት
Via: ዘመላዕክ እንድሪያስ

@marakinews


የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ዳግም መሰማቱን ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ አረጋገጡ!!

በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝርት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን ዶክተር ኤሊያስ ሊዌ ለኢቢሲ አረጋግጠዋል።

ዛሬ ጠዋት 1:37 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሊ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።
@maraki_news
@maraki_news


መረጃ፡

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዙሪያ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት እየተሰራጨ ያለው ደብዳቤ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጠናል።
@marakinews


ከ25 ዓመት እድሜ በላይ ተገልጋዮች የሚታተሙ ፓስፖርቶች የእድሳት ጊዜያቸው ወደ 10 ዓመት ከፍ ተደረገ::

የእድሳት አገልግሎት ቁጥርን ለመቀነስ ከ25 ዓመት እድሜ በላይ ተገልጋዮች የሚታተሙ ፓስፖርቶች የእድሳት ጊዜያቸው ከአምስት ዓመት ወደ አስር ዓመት ጊዜ ገደብ እንደሚደረግ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አስታወቀ።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የ2017 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት አፈፃፀሙን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ በየብስ እና በአየር ኬላዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ምቹና ቀልጣፋ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎች ተመሰራታቸውን ገልጸዋል።

በያዝነው በጀት ዓመት በ3 ወር ውስጥ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን ማስተናገዱንም ጠቁመዋል።

በተቋሙ የሚስተዋሉ የአቅም ውስንነቶችን ከመቅረፍ አኳያ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ የሰው ኃይል አደረጃጀቱን የተሻለ ለማድረግ 125 ለሚሆኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአንድ ወር ስልጠና መሰጠቱን አመልክተዋል።

በሩብ ዓመቱ 478 ሺሕ ቡክሌቶች ውስጥ 357 ሺሕ ፓስፖርቶች ተሰራጨ ሲሆን በዚህም 97 ነጥብ 2 በመቶ አፈፃፀም ተመዝግቧልም ነው ያሉት።

በሩብ በጀት ዓመቱ በኢ ቪዛ 259 ሺሕ 705 ደንበኞች አገልግሎት ማግኘታቸውን አንስተው በቀጣይ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን ለመተግበር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም ጠቁመዋል።

ከመጪው ጥር ጀምሮ የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ተቋሙ አስታውቋል።
@maraki_news
@maraki_news


#Remedial #grade_12

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በ 'Remedial' ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ ሞልተው እንዲጨርሱ መገለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ " አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻችንን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርስቲ ምርጫ መሙላት ተቸግረናል " ባሉት መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር የምርጫ መሙያ ጊዜውን እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
@maraki_news
@maraki_news


ዘጠኝ ኪሎ ግራም ወርቅ ከሴቶቹ ብልት ተገኘ።

በስድስት ሴቶች ብልት ውስጥ ተሰፍቶ ሊያልፍ የነበረ ከ9 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ በኡዝቤክ ተወላጆች ወደ ቱርክ በድብቅ ሊገባ ሲል ተያዘ።

የቱርክ የጸጥታ አካላት ስለ ህገወጥ የወርቅ ዝውውሩ አስቀድሞ የሚያውቁ ሲሆን ከሳምንት በፊት ከአረብ ኤምሬትስ የመጡ 6 ሴቶችን እና ሊቀበላቸው የመጣውን ሹፌር መያዝቸዉን ገልፀዋል::

በፍተሻውም እያንዳንዳቸው 110 ግራም የያዙ 82 የወርቅ ባርዶች፣ 18 የፕሌይስ ስቴሽን ኮንሶሎች እና 3 ስማርት ስልኮች ተይዘዋል። ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያሳየው ተጨማሪ 84 የወርቅ ባርዶች በሴቶች ብልት ውስጥ ተሰፍተዉ ተገኝተዋል::

የቱርክ ፍርድ ቤት ቀዶ ጥገናን የፈቀደ ሲሆን በድምሩ ከ9 ኪሎ ግራም ከሴቶቹ ብልት ውስጥ ተገኝተዋል::
@maraki_news
@maraki_news


ቤንዚን እና ነጭ ናፍጣ ምን ያህል ጨመረ ?

በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተደርጎ የነበረው ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር 2016 ዓ/ም ነበር።

በወቅቱ ቤንዚን በሊትር 82.60 ብር ፤  ነጭ ናፍጣ በሊትር 83.74 ብር በሊትር ፤ ኬሮሲን በሊትር 83.74 ብር ፤ ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 65.48 ብር እንዲሁም ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 64.22 ብር ተደርጎ ነበር።

ከዛ በኃላ ባሉት ወራት የነዳጅ ዋጋ ባለበት ቀጥሏል።

ዛሬ ግን ጭማሪ ተደርጓል።

በቤንዚን ላይ ከ8 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጎ 1 ሊትር ቤንዚን 91 ብር ከ14 ሳንቲም ሆኗል።

በነጭ ናፍጣ ላይ ከ6 ብር በላይ ጭማሪ  ተደርጎበት አሁን አንዱ ሊትር 90 ብር ከ28 ሳንቲም ገብቷል።
@maraki_news
@maraki_news


የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ!

በያዝነው አመት በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመማር የ12ኛ ክፍል ውጤት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች የሪሚዲያል መግቢያ ውጤት 204 ሲሆን ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች የሪሚዲያል መግቢያ ውጤት 192 ነው።

ሙሉ መረጃው ከላይ ተያይዟል።
@maraki_news


ሰበር ዜና 🇪🇹 ሀገራችን ኢትዮጲያ አዲስ ፕሬዚዳንት አግኝታለች!

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾዋል።

በመሆኑም የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አዲስ ለተሾሙት ፕሬዜዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ህገመንግስቱን አስረክበዋል።
@maraki_news


በመሬት መንቀጥቀጡ ድንጋጤ ቤታቸውን ለቀው የወጡ የአንዳንድ ሰዎች መኖሪያ ቤት መዘረፉ Maraki News አረጋግጧል።
@maraki_news

6k 0 31 1 52

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ? መደረግ ያለበት ጥንቃቄስ ምንድነው ?

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ምን አሉ ?

" ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ወይ ? የሚባለው ሰሞኑን በሙሉ ይሄን አይነት ንዝረቶች ነበሩ።

መሬት መንቀጥቀጥ መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን መተንበይ አይቻልም።

ስለዚህ ሊከሰት ይችላል ሊመጣ ይችላል። ይሄ ሁል ጊዜ በተለይ አዲስ አበባ የምንኖር ሰዎች ነቅተን የምንጠብቀው ነገር መሆን አለበት።

ስምጥ ሸለቆና የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነቅተን የምንጠብቀው ነገር ነው መሆን ያለበት።

ለጊዜው መናገር የምችለው ከበድ ያለ ነገር ከመጣ አይመጣም ብለን ነው የምንገምተው ከመጣ ግን ምን መደረግ ስለለበት ጥንቃቄ ነው።

➡️ የቤት ቋሚዎች በተለይ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ ያሉ ሰዎች ኮለኖች አካባቢ መጠጋት ለምን መውረድ ሊከብድ ይችላል ቁልፍ ማክፈትም ሊከብድ ይችላል። ስለዚህ ኮለኖች አካባቢ መጠጋት።

➡️ ከተቻለ ጠረጴዛ ስር መግባት።

➡️ ሊፍት አትጠቀሙ። ማንም ሰው በሊፍት ለመውረድ እንዳይሞክር። ያን እንዳትጠቀሙ።

ይሄን ይሄን ጥንቃቄ ማደርግ ያስፈልጋል። ነገር ግን አሁን ባለው እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ከባድ ነገር አለ ብለን አንገምትም። "
@maraki_news


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ስለ መሬት መንቀጥቀጡ እና ከዚህ በሁዋላ ከተከሰተም መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች የሰጡትን መግለጫ ከላይ ባለው ድምፅ ቅጂ መከታተል ትችላላችሁ !
@maraki_news


#Update ማብራሪያ ከዶክተር ኤልያስ ሌዊ

" እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።

ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።

ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።

ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።

በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ።

ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ህንጻቸው ሲንቀጠቀጥ እንደነበር ገልጸውልናል። በዚህ ምክንያት ከቤታቸው ወጥተው መሬት ላይ ወርደው ተሰባስበዋል።
@maraki_news


ሰበር ከደቂቃዎች በፊት (ከምሽቱ 2:10) ላይ በአዲስ አበባ፣ መስቀል አደባባይ፣ ካዛንቺስ እና ሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች የተከሰተው አነስተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የፈጠረው ንዝረት ህንጻዎችን ለተወሰኑ ሰከንዶች አንቀጥቅጦ ነበር።

Did you notice that?
@maraki_news


አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ
---------------
በ ICT ወይም በ Secretary ሙያ ተመርቃ ልምድ ያላት ወይም በ 0 ዓመት ፀሐፊ የሚፈልግ ተቋም አለ !!
የስራ ቦታ :- እንጅባራ

ዝርዝር መረጃ በዉስጥ ማናገር ይቻላል

ሼር አድርጉት !!
@marakinews


በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

► የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
► ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
► የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
► አራት 3X4 ፎቶግራፍ።

(የዩኒቨርሲቲው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)
@maraki_news


ሰበር ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በርዕሰ ብሄርነት እንደማይቀጥሉ ታወቀ !

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥቅምት ላይ የሚጠናቀቀውን የስራ ዘመናቸውን ተከትሎ በርዕሰ ብሄርነት መቀጠል እንደማይፈልጉ መሠረት ሚድያ ከምንጮቹ ሰምቷል።

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ለበርካታ ወራት በስራ ድርሻቸው ዙርያ በሚፈፀሙ አንዳንድ ድርጊቶች እና ከስራ አስፈፃሚው አካል ጋር ባላቸው ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ደስተኛ እንዳልነበሩ ሰምተናል።

በመጪው ሳምንት የመጀመርያ ቀናት ይህን ያለመቀጠል ውሳኔያቸውን ለስራ አስፈፃሚው አካል ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዛሬው እለት በኤክስ (ትዊተር) አካውንታቸው ላይ "እነ ጥላሁን ገሠሠ: ቴዲ አፍሮ: አሊ ቢራ:ማህሙድ አህመድ..ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው::"የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው:መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው"ይላል ማህሙድ "ዝምታ ነው መልሴ"ን ሲያዜም::ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" የሚል ፅሁፍ አስፍረው ነበር።

ይህን ተከትሎ የፕሬዝደንት ፅ/ቤት ሀላፊው አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ "የፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ኦፊሴላዊ አካውንት አለ፣ እኛ አስተያየት መስጠት የምንችለው በእሱ ዙርያ ነው። የተባለው ፅሁፍ በግል አካውንት ላይ ስለተለጠፈ ቢሯችንን አይመለከትም" በማለት ለኢትዮጵያ ቼክ ምላሽ ሰጥተው ነበር።

ይህ ፅሁፍ አሁን ድረስ የፕሬዝደንቷ የኤክክስ አካውንት ላይ ይገኛል።
©Meseret media
@maraki_news

Показано 20 последних публикаций.