Репост из: 🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
አዲስ ግጥም
መርከዙ ተከፍቷል
ገብታችሁ ሸምቱ‼️
የደማጅ ትውስታ ናፍቆት የገደለህ
በሱንዮች መርከዝ መጠለል ያማረህ
በቂልጦ ጎሞሮ በውብ ተገንብቶ
እየጠበቀህ ነው መንገድ በሩን ከፍቶ።
ደማጅ አፈረስናት ብለው ቢደሰቱም
የአላህ ጥበቡ ግን ሚሰራው አያውቁም።
የደማጅ ግድግዳ ጣራውም ቢፈርስም
ዒልሙ ግን ይፈሳል መቼም አይገደብም።
የጀሊሉ ጥበብ ገርሞ ያስገርማል
ደማጅ ሲያወድሙት ዳዕዋው ግን አብቧል
በጊዜው አዝነናል ዐይናችን አንብቷል
ዛሬ ግን በደስታ ልባችን ረክቷል።
የደማጅ ዑለሞች ለአለም ተበትነው
ምድርን አስዋቧት በሱና ተጊጠው።
እኛም ወጉ ደርሶን መቋደስ ችለናል
ከደማጅ ፍሬዎች ድርሻችን ወስደናል።
ቢድዓ ተደምስሶ ጅህልና ሊወገድ
ለአላህ ሊሰገድ ለአላህ ሊታረድ
የተውሒድ ባንዲራ ይውለበለብ ዘንዳ
መርከዙ ተከፍቷል በአቡ ቀታዳ።
የልጅ አዋቂ ነው ዕውቀት ያተለቀው
ከምቀኞች ሴራ አላህ ይጠብቀው።
ዐቂዳው የነፃ ፊቅሁ የረቀቀ
ኹጥባ ሙሀደራው ደሊል የታጠቀ
"ቃለ خدثنا ብሎ ከጀመረው
የደርሱ ፋኢዳ ፅፈህ አትጨርሰው።
አስቤ ነበረ ብዙ ለመዘርዘር
እሱ ግን አይወድም ስለሱ ሊነገር።
ያሳለፍነው ይብቃን በሆነ ባልሆነው
ከእንግዲህ እንማር መንገዱ ክፍት ነው።
ጥርት ያለች ሱና ከጫፍ እስከ ጠረፍ
ለማድረስ ተዘጋጅ አትድከም አትስነፍ
ወዴት ሄጄ ልማር? የሚለው እሮሮ
ከእንግዲህ አብቅቷል ተከፍቷል ጎሞሮ!
ከጥንት ከጠዋቱ ከሙስሊሞች ሀገር
ተውሂድን ለማንገስ በጋር ሰቦች መንደር
ባይገኝም ነዳጁ ቢበዛም ትችቱ
መርከዙ ተከፍቷል ገብታችሁ ሸምቱ
✍🏿ሐምዱ ቋንጤ
ለጊዜው👇
☔ከቂልጦ ሰማይ ስር
📱ለመከታተል👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAENJn9-WekBJmow0AQ
📨አስታያየት ለመስጠት👇👇👇
http://telegram.me/hamdquante_bot
መርከዙ ተከፍቷል
ገብታችሁ ሸምቱ‼️
የደማጅ ትውስታ ናፍቆት የገደለህ
በሱንዮች መርከዝ መጠለል ያማረህ
በቂልጦ ጎሞሮ በውብ ተገንብቶ
እየጠበቀህ ነው መንገድ በሩን ከፍቶ።
ደማጅ አፈረስናት ብለው ቢደሰቱም
የአላህ ጥበቡ ግን ሚሰራው አያውቁም።
የደማጅ ግድግዳ ጣራውም ቢፈርስም
ዒልሙ ግን ይፈሳል መቼም አይገደብም።
የጀሊሉ ጥበብ ገርሞ ያስገርማል
ደማጅ ሲያወድሙት ዳዕዋው ግን አብቧል
በጊዜው አዝነናል ዐይናችን አንብቷል
ዛሬ ግን በደስታ ልባችን ረክቷል።
የደማጅ ዑለሞች ለአለም ተበትነው
ምድርን አስዋቧት በሱና ተጊጠው።
እኛም ወጉ ደርሶን መቋደስ ችለናል
ከደማጅ ፍሬዎች ድርሻችን ወስደናል።
ቢድዓ ተደምስሶ ጅህልና ሊወገድ
ለአላህ ሊሰገድ ለአላህ ሊታረድ
የተውሒድ ባንዲራ ይውለበለብ ዘንዳ
መርከዙ ተከፍቷል በአቡ ቀታዳ።
የልጅ አዋቂ ነው ዕውቀት ያተለቀው
ከምቀኞች ሴራ አላህ ይጠብቀው።
ዐቂዳው የነፃ ፊቅሁ የረቀቀ
ኹጥባ ሙሀደራው ደሊል የታጠቀ
"ቃለ خدثنا ብሎ ከጀመረው
የደርሱ ፋኢዳ ፅፈህ አትጨርሰው።
አስቤ ነበረ ብዙ ለመዘርዘር
እሱ ግን አይወድም ስለሱ ሊነገር።
ያሳለፍነው ይብቃን በሆነ ባልሆነው
ከእንግዲህ እንማር መንገዱ ክፍት ነው።
ጥርት ያለች ሱና ከጫፍ እስከ ጠረፍ
ለማድረስ ተዘጋጅ አትድከም አትስነፍ
ወዴት ሄጄ ልማር? የሚለው እሮሮ
ከእንግዲህ አብቅቷል ተከፍቷል ጎሞሮ!
ከጥንት ከጠዋቱ ከሙስሊሞች ሀገር
ተውሂድን ለማንገስ በጋር ሰቦች መንደር
ባይገኝም ነዳጁ ቢበዛም ትችቱ
መርከዙ ተከፍቷል ገብታችሁ ሸምቱ
✍🏿ሐምዱ ቋንጤ
ለጊዜው👇
☔ከቂልጦ ሰማይ ስር
📱ለመከታተል👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAENJn9-WekBJmow0AQ
📨አስታያየት ለመስጠት👇👇👇
http://telegram.me/hamdquante_bot